Thursday, 5 February 2015

መንግስት በፌስ ቡክና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰማራቸው ሰዎች የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አልቻሉም ተባለ።

ማህበራዊ ድረገጾች ላይ የመንግስትን መልካም ገጽታ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊደርጉ ይችላሉ በሚል ተከታታይ ስልጠና ተሰጥቷቸው የነበሩት የህዝብ ግንኑነት ባለሙያዎች (ኮምኒኬተሮች) እና የመንግስት ባለስልጣናት፤የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አልቻሉም መባላቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖ ጠቆሙ፡፡ ለመንግስት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችና ለካድሬዎች በአቶ ሬድዋን ሁሴን በሚመራው የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት አማካይነት ከአራት ወር በፊት በማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀምና በመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ተከታታይ ስልጠና መሰጠቱ ይታወቃል። ሰልጣኞቹ ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ የመንግስትን አዎንታዊ ሚና አጉልተው በመጫወት የገጽታ ግንባታ ሥራ እንዲያከናውኑ የተሰማሩ ቢሆንም፤ እንደታሰበው ውጤት ሊያስገኙ አለመቻላቸው ተመልክቷል። ጉዳዩን በቅርበት የኒያውቁ አካላት እንደሚሉት፦ውጤት ላለመገኘቱ ዋነኛው ምክንያት ብዙዎቹ “ኮምኒኬተሮች” በአቶ በረከት ስምኦን የሚኒስትርነት ዘመን ከየክልሉ በፖለቲካ ብቃት ብቻ ተመልምለው፣ በለብለብ ሥልጠና ወደሕዝብ ግንኙነት ሙያ የገቡከ መሆናቸው አኳያ ከፍተኛ የአቅም ችግር ስላለባቸው ነው። ቀሪዎቹም በቤት አሰጣጥ፣ በደመወዝ ጭማሪና እና በመሳሰሉት ጉዳዮች በሚስተዋሉ አድሎአዊ የጥቅማጥቅም አሰጣጥ ያኮረፉ መሆናቸው ተገልጿል። <<ኮምኒኬተሮቹ>> ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በየመስሪያ ቤቱ ሲመደቡ ፤ ቀደም ሲል በየመስሪያ ቤቶቹ ከነበሩ ብቃት ካላቸው የኮምኒኬሽን ባለሙያዎች አንዳንዶቹ ከቦታቸው እንዲነሱ ሲደረግ ፤የተቀሩት በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡ አብዛኛዎቹ<<ኮምኒኬተሮች>> ከተሰጣቸው ሥልጠና በሁዋላ እንደፌስቡክ ባሉ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ የራሳቸውን ወይንም የድርጅታቸውን አካውንት ለመክፈት ሙከራ ከማድረግ በዘለለ ምንም ማከናወን ሳይችሉ መቅረታቸው፤ የአቶ ሬድዋንን ቢሮ ማበሳጨቱ ተጠቁሟል፡፡ በተለይ በፌስቡክ የሚሳተፈውን ዲያስፖራ እና የተቃውሞ ሃይሉን በአንድ ላይ በመጨፍለቅ «አክራሪ ሃይሎች» በሚል የፈረጀው ኢህአዴግ ፤ይህን ሃይል ቢቻል ጸጥ ለማሰኘት ካሰማራቸው ስልጣኞች ባሻገር ከ25 በላይ የሚሆኑ ሚኒስትሮች ሳ ማህበራዊ ድረገጾችንእንዲጠቀሙ ሲወተውት ቆይቷል። ይሁንና እስካሁን በግልጽ የራሳቸው አካውንት ያላቸው ባለስልጣናት በጣት የሚቆጠሩ ከመሆናቸው አኳያ ለኢህአዴግ እንቅፋት የሆነውን ሃይል የሚገዳደሩ አለመሆናቸው ቢሮውንና ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ከኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ source,-ethsat.com

አቶ ሲሳይ ዘርፉ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈበት

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ ለነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት ሲበትን ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ሲሳይ ዘርፉ ዛሬ ጥር 28/2007 ዓ.ም የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላፈበት፡፡ ታህሳስ 14/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ቆርቦ የነበረው አቶ ሲሳይ ዘርፉ ‹‹…‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ› ለመላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ….ተብሎ የተጻፈበት በራሪ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ሲያከፋፍል እጅ ከፈንጅ በመያዙ በፈጸመው የሐሰት ወሬን በማውራት ህዝቡን ማነሳሳት ወንጀል…›› በሚል በፌደራል አቃቤ ህግ ለቀረበበት ክስ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል፡፡ ከዚህም ባሻገር አቶ ሲሳይ ዘርፉ ጥር 7/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር የሆኑትን ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና አቶ ስለሺ ፈይሳ እንዲሁም የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኦህዴህ) ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለን በመከላከያ ምስክርነት አቅርቦ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ‹‹ምስክሮቹ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ምስክርነት ሳይሆን የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ ነው ያቀረቡት፡፡›› በሚል ምስክሮቹ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ውድቅ አድርጓል፡፡ አቃቤ ህግም በተሰጠው የጥፋት ውሳኔ ላይ ‹‹ተከሰሽ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 82(ሀ) 1/ መሰረት ማቅለያው ታይቶለት ከዚህ ቀደም የወንጀል ድርጊት ያልፈጸመ ስለሆነ የምንጠይቀው የቅጣት ማክበጃ የለንም፡፡ ሆኖም ግን በሰራው የወንጀል ድርጊት የመጨረሻው ጣሪያ ውሳኔ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡›› ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለካቲት 3/2007 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት በመናገሻ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡ አቶ ሲሳይ ዘርፉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ዋስትናው ተነፍጎ ቀደም ብሎ በፖሊስ ጣቢያና አሁን ደግሞ ቂሊንጦ እስር ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡

Wednesday, 4 February 2015

ጸጉሯን ተላጭታ ፍርድ ቤት ቀረበች የዞን ዘጠኟ ጋዜጠኛ ኤዶም

የዞን ዘጠኟ ጋዜጠኛ ኤዶም ጸጉሯን ተላጭታ ፍርድ ቤት ቀረበች – “የእምነት ክህደት ቃላችንን ከመስጠታችን በፊት ዳኛው ይነሱልን” – ዞን ዘጠኞች
>በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ፡፡ ጥር 26/2007 ዓ.ም ለ17ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሆኑት አቶ ሸለመ በቀለ ‹‹የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታችንን አላስከበሩልንም›› በሚል ከችሎት እንዲነሱ በጽሑፍ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተሰየመው ተሻሽሎ ቀርቧል በተባለው የአቃቤ ህግ ክስ ላይ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት እንደነበር ዳኞቹ ቢናገሩም፣ ተከሳሾች አቤቱታ እንዳላቸው በመግለጽ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁዎች አለመሆናቸውን ለችሎቱ ማስረዳት ችለዋል፡፡ ተከሳሾች ‹‹እኛ በሰብሳቢ ዳኛው ላይ አቤቱታ አለን፤ ፍርድ ቤቱ የራሱን ውሳኔ እንኳ አላከበረም፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን የእምነት ክህደት ቃላችንን ለመስጠት ዝግጁዎች አይደለንም›› በሚል ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን እንዲቀበል ጠይቀዋል፡፡ ዳኛ ሸለመ በቀለ ‹‹ፍርድ ቤቱ ቃሉን አላከበረም›› በሚለው ጉዳይ ላይ መልስ ሲሰጡ ‹‹የእኛን ውሳኔ የማትቀበሉ ከሆነ ጉዳዩን በይግባኝ እንዲታይ ማድረግ ይቻላል›› ብለዋል፡፡ ‹‹ላለፉት ስድስት ወራት በነበረው የክርክሩ ሂደት የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ሸለመ በቀለ ሂደቱን በአግባቡ በመምራት የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታችንን አላስጠበቁልንም፡፡ በተለያየ ጊዜም ሐሳባችን ለመግለጽ ስንሞክር ክልከላ አድርገውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ችሎቱ ራሱ የሰጠውን ትዕዛዝ ራሱ ሽሮ ፈጽሞ ልንረዳው በማንችለውና የመከላከል መብታችንን በሚያጣብብ የክስ ሁኔታ ክርክሩን እንድንቀጥል ሲበየንብን የችሎቱ ሰብሳቢ ወሳኝ ሚና ነበራቸው›› ሲሉ ተከሳሾች በሰብሳቢ ዳኛው ላይ ቅሬታቸውን በአቤቱታቸው ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ሸለመ በቀለ ከችሎት እንዲነሱ የሚጠይቀውን አቤቱታ አይቶ ነገ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
............SOURCE,- http://www.zehabesha.com/

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እስር ቤት ውስጥ በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እኚህ ነበሩ የህዳር 27/28 የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የጠራው የአዳር ሰልፍ ወቅት ተይዘው በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ እና ለሶስት ቀን የስኳር በሽታ መድሃኒት እንዳይገባላቸው በመከልከላቸው ለህመም የተዳረጉት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ምክትል ፀኃፊ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ ከእስር ከተፈቱበት ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ወር ሆስፒታል ከቆዩ በኋላ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በአዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ለአምስት ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ይዘውት የነበረውን የስኳር በሽታ መድሃኒታቸውን በመቀማታቸው፣ እንዳይገባላቸው በመከልከላቸውና በወቅቱም ህክምናም ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ህመም በመዳረጋቸው ለሁለት ወር ያህል ዘውዲቱ ሆስፒታል ቆይተዋል፡፡ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ዘውዲቱ ሆስፒታል ከገቡበት ታህሳስ 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ጥር 27/2007 ዓ.ም በቦሌ ሚካኤል እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል፡፡ source,-http://ethioforum.org/amharic/

Tuesday, 3 February 2015

35 ሰዎች ቀይ ባህር ውስጥ ጠፉ * የ9 ኢትዮጵያውያንን ሰውነት አግኝተዋል

35 ሰዎች ቀይ ባህር ውስጥ ጠፉ * የየመን ነብስ አድን ሰራተኞች የ9 ኢትዮጵያውያንን ሰውነት አግኝተዋል
ዘ-ሐበሻ) ዜግነታቸው ከኢትዮጵያ ሶማሊያና አካባቢው ሃገራት እንደሆነ የሚገመት 35 አፍሪካውያን ቀይ ባህር ውስጥ ይጓዙበት የነበረችው ትንሽዬ ጀልባ ሰጥማ የት እንደደረሱ ሊታወቅ አለመቻሉን የየመን ባለስልጣናት አስታወቁ:: በደቡባማው የየመን ክፍል ቲያዝ አቅራቢያ በሚገኘው የቀይባህር ውስጥ ሰጥመዋል ስለተባሉት አፍሪካውያን የየመኑ ባለስልጣን ጀነራል ሰኢድ ስባሪ ሲናገሩ እነዚህ ሰደተኞች በባህር ላይ ይጓዙ የነበረው 49 ሆነው ሲሆን በነበረው መጥፎ አየር የተነሳ ሊሰጥሙ ችለዋል:: እንደ ጀነራሉ ገለጻ የየመን መንግስት የ13 ሰዎችን ሰውነት ያተረፈ ሲሆን 9ኙ የኢትዮጵያውያን እንዲሁም 5ቱ የሶማሊያውያን ነው ተብሏል:: እንዲህ ያለው አሰቃቂ አደጋ በየመን አካባቢ ሲደርስ በ6 ወር ጊዜያት ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን ባለፈው ዲሴምበር 12 የየመን መንግስት የ24 ኢትዮጵያውያንን አስከሬን ከባህር እንዳወጣ; እንዲሁም በጁላይ 12 70 ኢትዮጵያውያን እንዲሁ በቀይ ባህር ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት መግለጫ በዚሁ በቀይባህር በኩል ተሻገረው ወደ የመን ከሚሄዱ አፍሪክውያን መካከል በሺህዎች የሚቆጠሩት ሕይወታቸው በአንድ ዓመት ውስጥ ያልፋል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/

ሰበር ዜና – የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

(ሰማያዊ ፓርቲ) ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡ በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡ ‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡ በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
.......................... source,-http://ecadforum.com/

Monday, 2 February 2015

አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን ተከናነቡ

አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን ተከናነቡ (በሬስቶራንት ውስጥ የደረሰባቸውን የውርደት ቪድዮ ይዘናል) aba dula
(ዘ-ሐበሻ) በምሽትና በድብቅ ሀሙስ ምሽት ሚኒሶታ የገቡት የሕወሓት ተላላኪው ባለስልጣን አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን መከናነብ የጀመሩት ገና ከአውሮፕላን ከወረዱ ጀምሮ ነበር:: አባዱላ የሕወሓት ተላላኪ ሆነው የኢትዮጵያን እመራታለሁ እያሉ ከኤርፖርት የተቀበሏቸው ጥቂት ሶማሊያውያን የታክሲ ሾፌሮች ናቸው:: እነዚህ የሱማሊያ ታክሲ ሾፌሮች አባዱላን ከተቀበሉ በኋላ ብሎሚንገተን በተሰኘው የሚኒሶታ ከተማ ሂልተን ሆቴል ያሳረፏቸው ሲሆን እንደዚህ ቀደሙ የወያኔ ተላላኪዎች ሲመጡ ፖስተር ተለጥፎ ስብሰባ እንደሚጠራው ለአባዱላ የወያኔ ተላላኪዎች ያደረጉት ነገር የለም:: ይልቁንስ በቴክስት መልክት ብቻ በስልክ የወያኔ ኔትወርኮች ብቻ እንዲጠራሩ የተደረገና ሌላው ሕዝብ የአባዱላን ስብሰባ እንዳይሰማ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም ይህ ቴክስት መልዕክት ለኢትዮጵያን ደረሰ:: ኢትዮጵያውያኑ ልክ እንደሕወሓት ተላላኪዎች ድምፃቸውን ሳያሰሙ በቴክስት መልዕክት የተጠራሩ ሲሆን ስብሰባው የሚደረግበት ሂልተን ሆቴል ተገኝተዋል:: አባዱላ ገመዳ ከአንዲት ሴት ጋር ሁለተኛ ፎቅ ላይ ቁጭ ብለው ወደታች በአንደኛው ፎቅ በኩል የሚገቡትን ሰው እየተመለከቱ; አጠገባቸው ያለችው የትግራይ ተወላጅ የሆነች ሴት የሰውን ማንነት የምትነግር ይመስል ለባለስልጣኑ ትጠቁማለች:: በዚህ መሃል የዘ-ሐበሻ አዘጋጆችም ሲገቡ ሴትየዋ ለአባዱላ በጥቆማ ስታሳይ የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች ተመልክተዋል:: የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች ወደ ስብሰባው ሊገቡ ሲሉ እንደተለመደው የተከለከሉ ሲሆን ስብሰባውን ያዘጋጀው አካል ከ30 በላይ የሚቆጠሩ ፖሊሶችን በመቅጠር ተቃዋሚ የሆኑ ሰዎች እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: አንድ ፖሊስን በሚኒሶታ ለአንድ ዝግጅት በሰዓት መንግስት ከሚከፍለው በተጨማሪ ዝግጅት አዘጋጁ ከ$50 ዶላር ያላነሰ የሚከፍል ሲሆን የሕወሓት መንግስት ለነዚህ የአሜሪካ ፖሊሶች ለ6 ሰዓታት ለ እያንዳዳቸው $300 ዶላር በአጠቃላይም ለፖሊስ 9 ሺህ ዶላር አውጥቷል:: ይህም በኢትዮጵያ ብር ሲመነዝር 180 ሺህ ብር መሆኑ ነው:: ለአዳራሽ በትንሹ ከ2 ሺህ ዶላር በላይ, ለሶማሌ ታክሲ ሾፌሮች በሰዓት ከ60 ዶላር በላይ እንዲሁም ለአባዱላ እና ለተላላኪዎቻቸው የሆቴል አዳር ከ150 ዶላር በላይ የወጣበት ይኸው የሚኒሶታ ስብሰባ ካለስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን በስበባው የተገኘው ሕዝብም ከ45 ሰው እንደማይበልጥ በውስጥ ጉዳዩን እንዲከታተሉ የላክናቸው ምንጮች አስታውቀዋል:: የሕወሃት መንግስት ተላላኪው አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ስብሰባ እንዲያደርግ ግማሽ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ያጠፋ ሲሆን ያተረፈው ጥፋትን ብቻ ሳይሆን አባዱላ ገመዳ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ስድበንም ጭምር ነው:: በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን በሂልተን ሆቴልና በተለያዩ አባዱላ በሄዱባቸው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች በመገኘት አባዱላን በሰብ አዊ መብት ረገጣ, በአፋኝነት, በአምባገነንነት, በሙስና እና በግድያ ወንጀሎች ሲናገሯቸውና በርሳቸው ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲያሰሙባቸው ውለዋል:: በአጠቃላይ የሕወሓት መንግስት የዲያስፖራ ሳምንት በኦሮሚያ አከብራለሁ ብሎ ስብሰባ የጠራበት የአባዱላ ስብሰባ ከትርፉ ኪሳራው አመዝኗል:: ኢትዮጵያውያኑም በሚኒሶታ በተቃውሞ ሲያሸብሩት ውለዋል:: አባዱላ ገመዳ ዛሬ በሚኒሶታ የደረሰባቸው ቅሌት ነገ በሲያትል እንደሚደገም ይጠበቃል:: በሲያትል ያሉ ኢትዮጵያውያን የአባዱላን የህወሃት ተልኮ ለማክሸፍ እየተጠባበቁ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: አባዱላ በሬስቶራንት ውስጥ የደረሰባቸውን የተቃውሞ ውርደት ቭዲዮ ይመልከቱ:: - .....See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38630#sthash.EKn2EcYu.xbNHJn76.dpuf