Netsanet Online Samuel adem
Freedom and Justice for oppressed people.
Monday, 16 March 2015
ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው
ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው
• የሶዶ ፖሊስ 8 የሰማያዊ ዕጩዎችን በማሰር ቅስቀሳውን አስተጓጉሏል........
• የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተዘርፏል
..........• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ ሆን ተብሎ የተቀየሰ ስልት ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ
ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም›› ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት ‹‹ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ›› አድርጋችኋል በሚል ሌላ ክስ 8 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችንና ሌሎች አባላትን በማሰር ቅስቀሳውን እንዳደናቀፈ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ታደመ ፈቃዱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በባህርዳር ከተማ ፖሊስ ‹‹በሞንታርቮ ለመቀስቀስ ፈቃድ ስላላመጣችሁ መቀስቀስ አትችሉም፡፡›› በሚል ፓርቲው ሊያደርገው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ እንዳደናቀፈ የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ‹ለምን ትከለክሏቸዋላችሁ?› በሚል ህዝቡ ፖሊሶቹን በማፋጠጡ በድምፅ መቀስቀስ ባንችልም በህዝቡ ድጋፍ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማሰራጨት የተሳካ ቅስቀሳ አድርገናል›› ሲሉ አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ ምንም አይነት ፈቃድ እንደማያስፈልግ የገለፁት አቶ ስለሽ ፖሊስ የሚፈጥረው እንቅፋት ሆን ተብሎ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ የተቀየሰ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን በመሰረዝ ፓርቲው ምርጫው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥረዋል፡፡ ይህ አልበቃ ሲልም የቅስቀሳ መልዕክቶቻችን በተደጋጋሚ በሚዲያ እንዳይተላለፉ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ማስቆም ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡
በሌላ ዜና የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ባልታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በ02/07/07 ሁለት ሰዓት ላይ አራት ግለሰቦች ጽ/ቤቱን በመስበርና የጽ/ቤቱን ጥበቃ አስፈራርተው በማባረር ለቅስቀሳ የተላከ 6 ሺህ ኦሮምኛ በራሪ ወረቀት እንዲሁም 3 ሺህ አማርኛ በራሪ ወረቀት፣ አንድ የፎቶ ካሜራ፣ አንድ ባነር፣ ለሸካ ዞን ሊላክ የተዘጋጀ 5 ሺህ በራሪ ወረቀት፣ 50 ፖስተር፣ አንድ የእጅ ሜጋ ፎን፣ ሁለት ባነር፣ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲዘርፉ የጽ/ቤቱን ኮምፒውተርም ሰብረዋል›› ..........ሲሉ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Monday, 9 March 2015
የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለአራተኛ ጊዜ በሚዲያ እንዳይተላለፍ ተከለከለ
ኢቢሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አላስተላልፍም›› ብሎ መልሷል
• ‹‹ኢቢሲ ከገዥው ፓርቲ ጋር ወግኗል›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አላስተላልፍም›› ብሎ መመለሱን ዛሬ የካቲት 29/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኢቢሲ በደብዳቤው ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልዕክታችሁ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው ሰንደቅ አላማ ምስል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክልና ህገ መንግስቱን…. የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል ‹‹ይህ የኢቢሲ ተግባር የሰማያዊን ፕሮግራም ላለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተሰጠ ሰበብ ነው›› ያለው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ በህገ መንግስት የተከለከለውን ቅድመ ምርመራ ኢቢሲ እየተገበረው ነው ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
‹‹ህግ ተጥሷል ከተባለ እንኳን ፕሮግራሙ ከተላለፈ በኋላ እንከሰስ ነበር እንጅ ባልረባ ምክንያት አላስተላልፍም ብለው መመለስ አልነበረባቸውም›› ያለው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ሰንደቅ አላማ የሚውለበለበውን እንጅ ከዛ ውጭ ያለን ማናቸውንም ነገር የሚመለከት አይደለም ሲል ኢቢሲ የፓርቲውን መልዕክት ላለማስተላለፍ ያቀረበውን ሰበብ ተችቷል፡፡ አቶ ዮናታን አክሎም ‹‹በአዋጅ 654/201 ላይ የሰፈረው ህግ አንድም ቦታ ተሰቅሎ ስለሚውለበለብ፣ ከመኪና ከሚውለበለብ እና በአደባባይ ከሚያዝ ሰንደቅ አላማ ውጭ ስለ ሌላ አንዳችም የሚከለክለው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ኢቲቪ ለገዥው ፓርቲ በመወገን ፕሮግራማችን እንዳይተላለፍ እያደረገ ነው›› ሲል ወቅሷል፡፡
በተያያዘ ዜና ፓርቲው ነገ የካቲት 30 በሬድዮ ፋና ከአንድ ሰዓት ዜና በኋላ ለሚተላለፈው ፕሮግራም ትናንት ስድስት ሰዓት መልዕክቱን ለራዲዮ ጣቢያው ለማስገባት ቢሞክርም ‹‹ዘግተው ወጥተዋል፣ ሰኞ ነው የሚገቡት፡፡ ሰኞ አስገቡ›› በሚል የሰማያዊ ፓርቲን መልዕክት መልሰዋል፡፡የፓርቲዎች መልዕክት ከሚተላለፍበት 36 ሰዓት ቀድሞ እንዲገባ እንደተባለ የገለጸው አቶ ዮናታን ሰኞ ጠዋት የሚተላለፍን መልዕክት ‹‹ሰኞ ጠዋት አምጡ›› ብሎ መመለስ ላለማስተላለፍ እንደወሰኑ ያሳያል ብሏል፡፡
ከአሁን ቀደም ኤፍ ኤም 96.3 ሁለት ጊዜ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ አገልግሎት አንድ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት የመለሰ ሲሆን ይህኛው ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
Monday, 2 March 2015
በአዲስ አበባ የመኪና አደጋው በፎቶ ግራፍ
ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰቱ ስላሉ የመኪና አደጋዎች እርምት እንዲወሰድ ከሚል አንፃር ስትዘግብ ቆይታለች:: በኢትዮጵያ ባፈለው ዓመት ብቻ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያጡ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 331 ሰዎች በአደጋው ህይወታቸውን ሲያጡ ከ11 ሺህ በላይ ደግሞ ለከባድና ለቀላል የአካል ጉዳት መዳረጋቸው ተዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ትራፊክ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ደግሞ በኢኮኖሚው ላይ እያሳደረ ያለው ጉዳት ከባድ ነው ይላል;; ዝርዝሩን ያንብቡ
ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በየቀኑ እየደረሱ ያሉ የመኪና አደጋዎች ቁጥር ከ እለት ወደ እለት እየጨመረ መሄዱ ነዋሪዎችን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ይናገራሉ:: በዚህ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እንኳ በጊዜው ስለመኪና አደጋዎችና ስለሚወድመው የሰው ሕይወትና ንብረት በተደጋጋሚ ጽፈናል:: አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው አራት ኪሎ የድል ሐውልት አደባባይ አካባቢ ከስድስት ኪሎ መስመር ወደ ለገሀር ይጓዝ የነበረ የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ባገጠመው የፍሬን ችግር ከአንድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የሁለቱም ተሽከርካሪ ሹፌሮች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል::
በዚህ የመኪና አደጋ በተሳፋሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም አደጋው በፎቶ ግራፍ ላይ እንደምትመለከትት በጣም አሰቃቂ ነበር:: ከስድስት ኪሎ ከሚገኘው ቤታቸው ሃገር አማን ብለው ወደ ሥራቸው በማሽከርከር ላይ የነበሩትና ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ግርም ጎርፉ የተባሉ ግለሰብ የአንበሳ አውቶቡሱ ድንገት መስመሩን ስቶ በመምጣት እንደገጫቸው ገልጸዋል::
....በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶቡሱ መንገድ ስቶ የቤት መኪናውን ገጨ...
ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊትለፊት ረዥም ድልድይ ውስጥ ገባ፤ በዚህ አሰቃቂ አደጋ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ይፋ ሆነ። አውቶቡሱ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቁ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲያስታውቅ የአውቶቡሱ ቁጥር 66 እንደሆነ ታውቋል። ካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በገባው አውቶቡስ የተነሳ በአደጋው እስካሁን አንድ እግረኛን ጨምሮ አራት ወንድ እና አራት ሴት ተሳፋሪዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሲገለጽ 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። የአውቶቡሱ ሹፌር እና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት ተርፈዋል። የአውቶቡሱ አደጋው መንስኤ ላይ መሆኑ ሲታወቅ በአውቶቡሱ ድልድይ ውስጥ መግባት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ዘ-ሐበሻ ጨምሮ የደረሳት ዜና ያስረዳል።
....ዘነበወርቅ ድልድልይ የገባው አውቶቡስ ሲወጣ
Tuesday, 24 February 2015
የኬንያ ፖሊስ 101 ኢትዮጵያዉያንን አሠሩ
ናይሮቢ፤ የኬንያ ፖሊስ 101 ኢትዮጵያዉያንን ማሠሩ
የኬንያ ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ወደደቡብ አፍሪቃ ሊጓዙ ነበር ያላቸዉን ከመቶ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያንን ትናንት ማምሻዉን ማሠሩን አሶሲየትድ ፕረስ ከናይሮቢ ዘገበ። የኬንያ ልዩ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኖህ ካቱሞ ለዜና ወኪሉ ዛሬ እንደገለፁት የታሠሩት 101 ወንዶች ኢትዮጵያዉያንና እነሱን በኬንያ ድንበር በኩል ሊያሾልኩ በመሞከር የተጠረጠሩ ሶስት ኬንያዉያን ናቸዉ። ካቶሙ እንዳሉት ኢትዮጵያዉያኑ ወደደቡብ አፍሪቃ ጉዟቸዉን ከመቀጠላቸዉ በፊት በቡድን በቡድን ሆነዉ ኬንያ መዲና ናይሮቢ በሚገኝ አንድ ቤት ዉስጥ አርፈዉ ነበር። ታሳሪዎቹ ዳኛ ፊት ቢቀርቡም እንግሊዝኛ ስለማይረዱና በአማርኛም የሚያስተረጉምላቸዉ ባለመገኘቱ ምክንያት ለጊዜ ክስ አልተመሠረተባቸዉም። እንደዘገባዉ ዳኛዉ ቪክቶር ዋኩሜሌ አስተርጓሚ እስኪገኝ ጉዳዩን ለነገ ቀጥረዋል። ከዚህ ቀደምም ለተመሳሳይ ጉዞ የተዘጋጁ 95 ኢትዮጵዉያን በኬንያና ታንዛንያ ድንበር አቅራቢያ መታሠራቸዉ ተዘግቧል። የኬንያ ፖሊስ ከአፍሪቃ ቀንዷ ሀገር ሰዎችን የሚያሸጋግሩት ወገኖች ኢትዮጵያዉያኑን በሕገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋዉሩት የጦር መሣሪያ፣ አደንዛዥ እፆች፣ የዝሆን ጥርስና የመሳሰሉትን ነገሮች አስርገዉ በሚያስገቡበትና በሚያወጡበት መስመር እንደሆነ ገልጿል። ...... source.-www.dw.amharic
ከሜድትራኒያን ሞት ፊት የቆሙት ስደተኞች
ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ አመት የሜድትራኒያን ባህርን በጀልባ ለማቋረጥ ከሞከሩ 218,000 ሰዎች መካከል 3,500 መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታውቋል። በዚህ በተመሳሳይ መንገድ ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ በመጨመር ላይ ነው።
ሰለሞን መንግስቴ በሊቢያዋ የቤንጋዚ ከተማ ባለቤቶቹ ጥለውት የሄዱትን ቤት ይንከባከባል።አትክልት ይኮተኩታል። ግቢውን ያጸዳል። ሰለሞን በቤንጋዚ ብቻውን አይደለም። ባለቤቱ የዝና እዘዘው ቀን ቀን ከሰው ቤት ትሰራለች። ሰለሞን ስለ ወርሃዊ ደሞዙ ሲጠየቅ ፈገግ እያለ «በእውነት መቼ እንደሚከፍሉኝም አላወኩም።» ሲል ይመልሳል።
ሰለሞን ተወልዶ ካደገበት የጎንደር አካባቢ ወደ ሱዳን ገዳሪፍ የተጓዘው ለደላሎች አምስት ሺ የኢትዮጵያ ብር ከፍሎ በአስቸጋሪ የሌሊት ጉዞ ነበር። ጉዞውን ያመቻቹለት የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህገ-ወጥ ደላሎች ነበሩ። «ጉዞው የሚጀመረው ለሊት ሰው በሌለበት ሰዓት በእግር ነው። የሚለው ሰለሞን መንገዱ ከሶስት እስከ ሰባት ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ይናገራል። ከገዳሪፍ በኋላ በመኪና የሚደረገው ጉዞ «ሰው በሰው ላይ ጭነው ስለተጓዝን በእግር ከተደረገው የበለጠ ያስከፋል።»ሲል ያስታውሳል።
በተመሳሳይ መንገድ ከኢትዮጵያ ከወጣችው ከባለቤቱ የዝና እዘዘው ጋር የተዋወቁት በሱዳን በቤተ-ክርስቲያን ነበር። ሁለቱ ስደተኛ ወጣቶች መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ሶስት ጉልቻ መሰረቱ። ከ2003-2006 ዓ.ም. የዝና በሰው ቤት ሰለሞን ተመላላሽ ስራ እየሰሩ ቢቆዩም ሃገሩ አልተመቻቸውም። እንደገና ሌላ መንገድ-ሌላ ጉዞ አሁንም በህገ-ወጥ መንገድ
ከሱዳን ወደ ሊቢያ ለመጓዝ ለህገ-ወጥ ደላሎች በነፍስ ወከፍ ስድስት ሺ በአጠቃላይ አስራ ሁለት ሺ የሱዳን ፓውንድ ከፍለዋል። ሰለሞን ከባለቤቱ ጋር ከሱዳን ተነስተው የሰሐራ በርሃን ሲቋርጡ ጉዞውን ያመቻቹትን ሰዎች «አይን ያወጡ ደላሎች » ሲል ይገልጻቸዋል። 9.4 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሰፋውን የሐራ በርሃ ማቋረጥ ለጥንዶቹ መራር ነበር። «አንዲት ዛፍ ለውርርድ የማታይበት» ይለዋል ሰለሞን የሰሐራ በርሃን። የዝና እዘዘው ከሱዳን ወደ ሊቢያ ላደረጉት ጉዞ ዋንኛ ምክንያታቸው «ዞሬ ወደ አገሬ ብመለስ ምን ይዤ ልመለስ? » የሚለው ጥያቄ ትልቅ ቦታ እንደነበረው ታስታውሳለች። ስምንት ቀናት የፈጀውን ጉዞ ስታስታውስ ሲቃ ይተናነቃታል። ከበርሐው ንዳድ እና ውሃ ጥም ባሻገር ከውስጧ ሃዘን የቀበረ ትዝታ አላት። « ስንት እህቶቻችንን በበርሐ ጥለናቸው መጥተናል። እህቴ ወንድሜ አትልም። እህቴ ተኝታ ብትቀር አትቀሰቅስም።» ስትል ስለተሻገረችው የበርሐ ሞት ትናገራለች። ከሱዳን ወደ ሊቢያ በነበረው ጉዞ ስደተኞችን ከጫኑ ሶስት መኪኖች መካከል አንዱ ተገልብጦ ብዙዎች ማለቃቸውን ሰለሞን ያስታውሳል።
ሰለሞን እና እዝና የሰሐራ በርሃን አቋርጠው ሊቢያ ሲገቡ ከለበሱት ልብስ በቀር በእጃቸው አንዳች ነገር አልነበረም። ውስን ምግብ፤አልባሳት እና የግል ንበረቶች የያዙባቸው ሻንጣዎች መንገድ መቅረታቸውን እዝና ተናግራለች። እናም ሁለቱ ወጣት ጥንዶች ሊቢያ ሲደርሱ ፓስፖርትም ይሁን የጉዞ ሰነድ በእጃቸው አልነበረም።
የሊቢያ ሁለተኛ ከተማ የሆነችው ቤንጋዚ እንደ ቀድሞ ሰላም እና መረጋጋት ርቋታል። ነዋሪዎቿ የመኖሪያ ቤታቸውን ጥለው ተሰደዋል።ሰለሞን እና የዝና በቤንጋዚ የበረከተው የጥይት ተኩስ እና ሞት ስጋት ፈጥሮባቸዋል። እናም ሜድትራኒያን ባህርን ተሻግረው አውሮጳ ሊገቡ ቆርጠዋል።ሰለሞን «አሁን ካለንበት ቢንጋዚ የእቃ መርከብ ይመጣል ይባላል። ግን አይገኝም። እሱ 1,500 ዶላር ነው። ከደላላው ጋር ተነጋግረናል። በመጣ ጊዜ እነግራችኋለሁ ብሎናል።» ሲል የመጀመሪያ አማራጫቸውን ያስረዳል። ሁለተኛ አማራጫቸው አሁን ካሉበት ቤንጋዚ ከሊቢያዋ ዋና ከተማ 50 ኪ.ሜ. ወደ ምትርቀው ጋሪቡሊ መጓዝ ይኖርባቸዋል።«ከጋሪቡሊ ትልቅ የሚባለው እስከ 1,500 ዶላር የሚከፈልበት ነው። መካከለኛ የሚባለው ከ900-1100 ዶላር የሚከፈልበት ሲሆን አነስተኛ የሚባለው እና ብዙ ጊዜ አደጋ ደረሰባት የሚባለው ጀልባ ጉዞ ሰባት መቶ እና ስምንት መቶ ዶላር ያስከፍላሉ።» የሚለው ሰለሞን ጉዞው አስራ ስምንት ሰዓታት እንደሚወስድም መረዳታቸውን ተናግሯል።
ሰለሞንም ሆነ እዝና በጉዞው ስለሚገጥማቸው መከራ ጠንቅቀው ያውቃሉ። እዝና ከለቅሶዋ ጋር እየታገለች ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌላቸው ታስረዳለች። «ምን ይዤ?» ከሚለው የኢኮኖሚ ጥያቄ ባሻገር በእጃቸው የጉዞ ሰነድ ባለመኖሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቢያስቡ እንኳ ያለፉበትን መራራ ጉዞ መድገም ይኖርባቸዋል።ሰለሞን «አቅጣጫ የመሳት፤የመናወጥ፤ብርድ፤የመገልበጥ እና የመዋጥ ችግር እንዳለ እንሰማለን። እንዲህ አይነት እጣም የሚደርሳቸው ሰዎች እንዳሉ እንያወቅን ነው። ከሞት ጋር እየተነጋገርን ነው ማለት ትችላለህ።» ሲል ተናግሯል።
በዚህ ወር ብቻ ከሊቢያ ወደብ ተነስተው የሜድትራኒያን ባህርን በማቋረጥ ወደ ጣሊያን ለመሻገር የሞከሩ 300 ስደተኞች ለሞት ሳይደረጉ እንዳልቀረ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታውቋል። ባለፈው አመት ብቻ 218,000 ሰዎች የሜድትራኒያን ባህርን በጀልባ አቋርጠዋል። 3,500 ያህሉ ግን ከጉዞው መጨረሻ መድረስ ሳይችሉ በባህሩ ላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። ሰለሞን እና የዝና በጉዞው ሊገጥማቸው የሚችለውን ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ቢሆንም ፓስፖርትም ይሁን ህጋዊ የጉዞ ሰነድ በእጃቸው ባይኖርም ጉዞ ለመጀመር ዝግጅት ላይ ናቸው።
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ
Saturday, 21 February 2015
ሰበር ዜና – የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ
‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል:: ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/

Thursday, 12 February 2015
አቶ ጸጋዬ አላምረው የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አገር ለቀው ተሰደዱ
የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አቶ ጸጋዬ አላምረው አገር ለቀው ተሰደዱ
የአንድነት ፓርቲ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑትና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀሉት አቶ ጸጋዬ አላምረው፣ ከወያኔ የፀረ-ሽብር ግብረ ኅይል እንዲታሰሩ የማዘዣ ወረቀት በመዉጣቱ፣ ለተወሰነ ቀናት አገር ቤት ራሳቸውን ሰዉረውከቆዩ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
አቶ ጸጋዬ የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው ከታሰሩ በኋላ የመኢአድ አመቻች ኮሚቴ ዋሃ ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል።፣ ሕወሃቶች መሰናክል ፈጠርበት እንጂ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ዉህደቱ ጫፍፍ እንዲደርስ፣ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱ የአመራር አባላት መካከል አንዱ ነበሩ። የአንድነት ፓርቲ ያደርግ በነበረው የምርጫ ዘመቻም፣ የምርጫ ኮሚቴ አባል በመሆን ትልቅድርጅታዊ ሥራ ይሰሩም ነበር።
የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ፣ የሕወሃት ታጥቂዎች በሰላማዊ ዜጎችን ላይ ኢሰባአዊ የሆነ ከፍተኛ ድብደባ በፈጸሙበት ወቅት፣ በአካል ከተጎዱት ወገኖች መካከል አንዱ አቶ ጸጋዬ ነበሩ። ከስድስት ወራት በፊትም በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም፣ አንድነት እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ በፈረሙበት ጊዜም፣ የአገዛዙ ካድሬዎች ስብሰባዉ ለመረበሽ በሞከሩበት ወቅት ተፈንክተው ትልቅ ጉዳት ደሮባቸውም ነበር።
ሕወሃቶች በአቶ ጸጋዬ ላይ ያነጣጠሩት፣ በርካታ የአንድነት አባላትን ይዘው አቶ ፀጋዬ ሰማያዊን ከተቀላቀሉ በኋላ ሲሆን፣ ዋና ክስ አድርገው የወሰዱትም “አንድነት ፓርቲ የገንዘብ እርዳታ ከሽብርተኞች ይቀበላል፣ የሚቀበለዉም በአቶ ጸጋዬ አላምረው በኩል ነበር” የሚል እንደሆነ ታውቋል። ሕወሃቶች በሚቆጣጠሩት ኢቲቪና ራዲዮ ፋና ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአንድነት ላአይ የጅመሩ ሲሆን፣ እነ ትግስቱ አወሉንም በሜዲያ፣ የአቶ ጸጋዬ አላምረዉን ስም እየጠሩ “ገንዘብ ተቀባይ እርሱ ነበር” እያሉም እንዲናገሩ እያደረጓቸው ነው።
የአንድነት ፓርቲ በዉጭ አገር ካሉ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያገኝ እንደነበረ ይታወቃል። በዉጭ ያሉ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶችም፣ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በሰማዊ ትግል የሚያምኑ እንደመሆናቸው፣ በነርሱ በኩል ተሰብስቦ የሚላክን ገንዘብ ከሽብርተኞች እንደመጣ አድርጎ መቁጠር በሕግ፣ በሞራልም በአሰራር ተቀበያነት እንደሌላው የድጋፍ ድርጅቱ አባላት ይናገራሉ።
- source,-www.zehabesha.com
Subscribe to:
Posts (Atom)