Saturday, 31 January 2015
ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣
ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ … ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡
ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ ቁራሽ ለሚሞላው ከርስ ራሳቸውንና ማንነታቸውን፣ ከዚያም አልፎ የትም የማይደበቁትን ኅሊናቸውን ያቆሸሹ፣ የአገር “እንግዴ ልጆች” ወይም “ውርጃዎች” ለህወሃት የማከሰምና የመግደል ሴራ ተላላኪ ሆነው የህዝብን ክብር ሰልበው ረክሰው ያረከሳሉ። ከዚህም በላይ ነገ እንደ ውዳቂ ላንቲካ መጣላቸውን እያወቁ፣ አሽከርነት፣ ከሃዲነት፣ ውርደት፣ መለያቸው እንዲሆን መርጠው ተሳቅቀው ይኖራሉ። እነሱን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባመነበት መንገድ እንዲጓዝ ለመታገል የሚውተረተሩትን ተኩላ ሆነው ያስበሏቸዋል።
ቅንጅትን በሉት። ቅንጅትን አሳረዱት። ተቀራመቱተ። የውስጥ ችግሩ እንዳለ ሆኖ እነርሱ ግን ዕጣ መድበው ተጣጣሉብት። አየለ ጫሚሶና ባልደረቦቻቸው “የክህደት ዋንጫ” ተሞላላቸው። ከዚያም ተጣሉ።
አሁን “ምርጫ” ደርሷል፤ ድንጋጤ ጨምሯል፤ የሕዝብ ሱናሚ አስፈርቷል፤ የህንጻውና የመንገዱ ሁኔታ አልበቃም፤ የሰዉ ህይወት ከመቅለሉ የተነሳ ለሚዛን አልበቃ ባለበት አገር ህይወቱ “በቀላል ባቡር ሊቀልል” ሽር ጉድ ይባላል፤ “ሥራ ላይ ነን፤ ምርጫ ደርሷላ”፤ አስተናጋጇ ህወሃት በለመደችው መንገድ ልታባብል ብዙ ትጥራለች፤ በየማዕዘኑም እያደባች ነው፤ እስከ “ምርጫ” ቤቷን አሳምራ ቄጠማ ጎዝጉዛ፣ ፈንዲሻ ነስንሳ፣ ዕጣኗን አጫጭሳ “እንኮምር” እያለች ነው፡፡ ግን አልበቃትም፤ አላመነችም፤ ተጠራጥራለች፤ ተጨንቃለች፤ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በተለይም አንድነትን ለማጥፋት “ቡና ጠጡ” በማለት የሚላላኩላት የቦርዱ “ምሁራን” ላይ ታች እያሉ ነው። ኃላፊው ለምን ይህንን የተላላኪነት ሥራ እንደፈለጉት ባይታወቁም የቦርዱ አሽከርካሪ ምክትላቸው ግን “የዜግነት” ድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ “ለወገን ደራሹ ወገን” አይደል የሚባለው! ስለዚህ ህወሃት የሰፈረውን “የሚያገለማ ጽዋ” ለመጋት ርኩቻው ደርቷል። ፕሮፌሰርነት ከሚሰጠው ክብር ይልቅ “ተላላኪነት” ኩራት ሆነ
በአገራችን ሶስት ዓይነት ባርነት እንዳለ ይነገራል፡፡ የእነዚህ ባሪያዎች (ባንዶች) ማንነት ገፍቶ የሚወጣው “ምርጫ” በደረሰ ጊዜ ነው፡፡ አንደኛውና የመጀመሪያው ባሪያ “ምርጫ ቦርድ” የሚባለውና ሌሎች መሰል “የተቋም ባሮች” ናቸው፡፡ ሁለተኛው ባሪያ ምርጫ ቦርድን እና ተመሳሳይ ተቋማትን የሚመሩ አመራሮች ናቸው፡፡ ሦስተኞቹ ባሮች ደግሞ ህዝባቸውን ለንዋይ ሲሉ የሚሸጡ አገልጋዮች ናቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ ህወሃት የጠፈጠፋቸው፣ ያቦካቸው፣ የሚነዳቸው፣ ሲፈልግ አዋርዶ የሚያባርራቸው ናቸው፡፡ የዘመንና የትውልድ ሁሉ ተጠያቂ ባንዳዎች!
ሰሞኑን ምርጫ ቦርድ የባርነቱን ዘመን ለማራዘም በለመደ እጁ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ላይ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ጡጫ ለማሳረፍ፣ ለመሰንጠቅ፣ ለማክሰምና ለማፍረስ ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል ቅንጅትን በማፍረስ ታማኝ ሎሌነቱን እንዳስመሰከረ ሁሉ አሁንም ለህዝብ የእንግዴ ልጅነቱን ለህወሃት/ኢህአዴግ ደግሞ ታማኝ አሽከርነቱን ለማረጋገጥ እየተባ ይገኛል፡፡
እኛም እንደ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የባንዳዎችን ጥርቅም እናወግዛለን፡፡ ታሪክና ትውልድም ይህንን እንዳይረሱት እናሳስባለን፤ እንመዘግባለን፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የሚዘርፉትን፣ እየዘረፉ ያሉትን፣ የተዘረፉትን፣ እየተዘረፉ ያሉትን፣ ዘርፈው የሚያደርጉት የጠፋባቸውን፣ በሃብት የናወዙትን፣ በደም የተጨማለቁትን፣ የራባቸውን፣ ምርጫ ቦርድን፣ የኢህአዴግን ሎሌዎች፣ አሽከሮች፣ ሁሉ ይዛ እየነጎደች ነው፡፡ የጥጋቡም የግፉም ማብቂያ መቼ እንደሆነ ባይታወቅም የከፋቸውና ጥርሳቸውን የነከሱ እንዳሉ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን፡፡ ንጹህ አገር ወዳዶችና እኛም ጎልጉሎች ያንን ቀን አንናፍቀውም፡፡ ባንዶች ግን ይህንን ቀን የማስቀረት አቅም አላችሁና ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ህዝብ ይምረጣቸው ወይም ይጥላቸው አንድነትንም ሆነ ሌሎቹን የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ከራሳቸው ችግር ጋር ለህዝብ ውሳኔ ብትተዋቸው ይሻል ነበር፡፡ ነገርግን ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ እናንተም ዳግመኛ ባንዳነታችሁን አስመሰከራችሁ፤ ባርነታችሁንም ቀጠላችሁበት፡፡
...........................source.-www.goolgule.com
Friday, 30 January 2015
ሼክ አላሙዲን ከባለስልጣናት ጋር ወደ 30 የሚጠጉትንና እጅግ አትራፊ የሆኑ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ ወደ ግል እንዲያዞሩ ረድቷቸዋል ተባለ
. . ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ከባለስልጣናት ጋር ባላቸው ቀረቤታ የህዝብ ሃብት የሆኑ ኩባንያዎችን ወደ ግል እንዲያዞሩ ረድቷቸዋል ተባለ iየፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መሸጥ ከጀመረበት ከ1997 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ከሸጣቸው 370 ድርጅቶች መካከል ሼህ አልአሙዲ ወደ 30 የሚጠጉትንና እጅግ አትራፊ የሆኑ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ መሰብሰብ መቻላቸው ስርአቱ ለተዘፈቀበት ሙስና ማሳያ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል።
ሼሁ የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን በአሁኑ ወቅት ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ እየተባለ የሚታወቀውን በ1989 ዓ.ም በብር 1 ቢሊዮን 128 ሚሊዮን 543 ሺ ከ28 ሳንቲም በመግዛት በእጃቸው አስገብተዋል፡፡ ኩባንያው በ2006 በጀት ዓመት ብቻ ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ በማስገባቱ ምክንያት ባለፈው ወር የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ሸልሞታል፡፡ ለኢህአዴግ ከፍተኛ ጥቂት አመራሮች ባላቸው ቅርበት የሚታወቁት ሼህ አልአሙዲ ባለፉት 17 ዓመታት
በፕራይቬታይዜሽን ስም በይስሙላ በሚወጡ ጨረታዎች ወሳኝ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችንና የእርሻ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ በእጃቸው ማስገባት እንደቻሉ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከነዚህ ድርጅቶች መካከል በቀድሞ ስማቸው የሚታወቁትን ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካዎች፣ ድል ቀለም ፋብሪካ ፣ዋንዛ የእንጨት ውጤቶች ድርጅት፣ ዪኒቨርሳል እና አዋሽ ቆዳ ሁለት ፋብሪካዎች፣ ጎንደር፣ ድሬዳዋ እና ኮምቦልቻ ሶስት የሥጋ ውጤቶች ፋብሪካዎች፣ ለገደንቢ ወርቅ ፋብሪካ፣ አዲስ ጎማ (ሆራይዘን) ፋብሪካ፣ ደብረዘይት ሆራ ራስሆቴል፣ ውሽውሽ ጉመሮ ሻይ ልማትና ገበያ ድርጅት ፣ጎጃም፣ጎንደር፣የላይኛውና የታችኛው ብር ሸለቆ እርሻ ልማት፣ጎጀብ እርሻ ልማት፣ ጥቁር አባይ ጫማ ፋብሪካ እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ሼህ አላሙዲን በተለይ ደብረዘይት ሆራ ራስ ሆቴልን እጅግ ርካሽ በሚባል በ9 ሚሊየን ብር በ1990 ዓ.ም ቢገዙም እስከአሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ አጥረው ከማስቀመጥ ውጪ ሊሰሩበት አልቻሉም፡፡
ሼህ አልአሙዲን በተለይ እንደእነአቶ በረከት ስምኦን የመሳሰሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመቀራረብ የግልና የቤተሰቦቻቸውን የህክምናና መዝናኛ እንዲሁም አንዳንድ ወጪዎችን በመሸፈን፣ እንደቤትና መኪና የመሳሰሉ ውድ ስጦታዎችን በመስጠት ግልጽ የሆነ ሙስና እንደሚፈጽሙ፣ለዚህ ወሮታቸውም የጠየቁትን የህዝብ ሐብት ያለአንዳች ችግር እንዲወስዱ እንደሚደረግ ምንቾች ገልጸዋል። ሼክ አላሙዲ ከ10 አመት በፊት ኢህአዴግን በመደገፍ በምርጫ ቅስቀሳ መሳተፋቸው ይታወቃል።
- See more at: http://satenaw.com/amharic/
የአንድነትና የመኢአድ ቢሮ በፖሊስ ተከቧል
የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊስና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል፡፡
(ኢ.ኤም.ኤፍ) በቅርቡ ምርጫ ቦርድ – የአንድነት እና መኢአድ ፓርቲን መሰረዙን ገልጿል። ምርጫ ቦርድ ይህን ያደረገበት ምክንያት ለብዙዎች ግልጽ ነው። እነዚህ ሁለት ትላልቅ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ ጋር ከጥቂት ወራት በኋላ ለህዝባዊ ምርጫ ይቀርባሉ። ምርጫውን ከተሳተፉ ደግሞ… ፓርቲዎቹ ለኢህአዴግ ስጋት ናቸው። በዚህም ምክንያት ምርጫ ቦርዱ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ ከከረመ በኋላ ሁለቱን ፓርቲዎች ከምርጫው በፊት ከጨዋታው እንዲወጡ አድርጓል።
ይህ ከመሆኑ በፊት ግን በተለይ አንድነት ፓርቲ፤ ከፓርላማው አፈ ጉባኤ ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ድረስ የተጻጻፋቸውን ደብዳቤዎች ኢ.ኤም.ኤፍ አግኝቷቸዋል። እነዚህ ደብዳቤዎች በማንበብ ወቅታዊውን የአገራችንን የምርጫ ሂደትት መገንዘብ ይቻላል። ከምንም በላይ ደግሞ ይህ ቀን ሲያልፍ ጥፋተኞች በህግ እና በታሪክ ፊት ማንነታቸው ይጋለጣል። እርስዎም ለታሪክ ምስክር ይሆንዎት ዘንድ እነዚህን መረጃዎች መጫን ወይም ለሌሎች ማካፈል ይችላሉ።
39ኙን ገጽ የደብዳቤ ልውውጥ ለማንበብ ወይም ለማውረድ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
..አንድነት እና ምርጫ ቦርድ ያደረጉት የደብዳቤ ልውውጦች
.......................http://ethioforum.org/amharic/wp-
Thursday, 29 January 2015
ለጋዜጠኞች ጥያቄ ዕድል የነፈገው ‹‹ታሪካዊው የምርጫ ››
.ለጋዜጠኞች ጥያቄ ዕድል የነፈገው ‹‹ታሪካዊው›› የዛሬ የምርጫ ቦርድ ጋዜጣዊ መግለጫ (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና )
በዛሬው ዕለት ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ በሂልተን ሆቴል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲንና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ በመግለጫውም የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና የቦርዱ ጸሐፊና የጽ/ቤቱ ዋና ኃላፊ አቶ ነጋ ዱሬሳ ተገኝተው የመግለጫውን ዓላማ እና ስምንት ገጽ የሆነውን መግለጫ አንብበዋል፡፡
‹‹የአንድነት የቦርድ ዕውቅና ያለው መተዳዳሪያ ደንብ የ2004 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ቦርዱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ ከዚሁ የቦርድ ዕውቅና ካለው ደንብ አንጻር ሲመረምር እንደቆየና አሁንም ከዚሁ አኳያ የመረመረ ስለመሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል›› የሚለው መግለጫ፣ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን በኩል የተፈጸሙ ዋና ዋና ጥሰቶች በሚል ሰባት ነጥቦችን ዘርዝሯል፡፡
በእነ ትፍስቱ አወሉን ቡድን በተመለከተ ደግሞ አምስት ነጥቦችን በመዘርዘር ሕግ ማክበራቸውን ይጠቅሳል፡፡
መግለጫው አንድነትን በተመለከተ በመጨረሻ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን ያካሄዱት የአመራር ምርጫ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና ከምርጫ ሕጉ ድንጋጌዎች ውጪ በመሆኑ ዕውቅና እንደማይሰጠው፤ በሌላ በኩል በእነ ትዕግሥቱ አወል ቡድን በቀን ጥር 16 ቀን 2007 ዓ›ም የተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቡርዱ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ቦርዱ የእነ አቶ ትዕግሥቱ ዓወሉ ሁድን ፓርቲውን በመምራት ወደምርጫው እንዲገቡ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ወስኗል››
መኢአድን አስመልክቶ መግለጫው አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ ማሙሸት አማረ ሁድን የተፈጸሙ የህግ ጥሰቶች በሚል አራት ነጥቦች ዘርዝሯል፡፡ በሌላ በኩል በእነ አቶ አበባው መሐሪ ቡድን በኩል ያለውን እንቅስቃሴ የፓርቲውን ደንብ ያከበረ መሆኑን ጠቅሶ ‹‹የእሳቸው የምርጫ ሂደትም ሆነ የተመረጡበት የጠቅላላ ጉባኤ ውጤት ሪፖርት በቦርዱ ዕውቅና ተሰጥቶታል›› ይላል፡፡
መግለጫው በማጠቃለያው፣ አንድነትን እነአቶ ትዕግሥቱ አወሉ እና መኢአድን ደግሞ እነአቶ አበባው መሐሪ ፓርቲውን በመምራት ወደምርጫው እንዲገቡ በአንድ ድምጽ መወሰኑን ይገልጻል፡፡
መግለጫውን ያነበቡት አቶ ነጋ ዱሬሳ ወደመጨረሻ ላይ በፊታቸው ላይ ፍርሃት አዘል ስሜት በግልጽ ይነብባቸው ነበር፡፡ ከመግለጫው ከኋላ በቦታው የተገኘን ከ10 በላይ ጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ብንነሳም ፕሮፌሰር መርጋ ‹‹ጥያቄ አትጠይቁን›› በማለት የቪ.ኦ.ኤ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሐ አንድ ጥያቄ በትግል ካቀረበላቸው በኋላ አጭር መልስ ሰጥተው ወዲያው ተነስተው ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡
መግለጫው እስር በእርስ የሚጋጩ ሀሳቦችን መያዙን የዚህ ዜና ዘጋቢ ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህንንና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ብናስብም እነፕሮፌሰር መርጋ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ጥያቄ ለማቅረብ ዕድል ማግኘት ሳንችል ቀርቷል፡፡
በስፍራው የነበሩ የግል ጋዜጠኞች ‹‹ዘንድሮ ምን አይነት ምርጫ ልናይ ነው?›› በማለት በሀዘኔታ ሲናገሩ ተስተውሏል፡፡
source,-http://ecadforum.com/
Wednesday, 28 January 2015
በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለጉ 3 አርቲስቶች
ከሮቤል ሔኖክ
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት ያለመግለጽ መብት አለመከበሩ ያጠቃው ጋዜጠኞችን ብቻ አይደለም። አርቲስቶችም ጋዜጠኞች ከሚከፍሉት መስዋእትነት ያልተናነሰ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ የሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በመገደቡ ዛሬ እንደ ታላቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ተመስገን ደሳለን ያሉ ጋዜጠኞች ያልሆነ ክስ ተልጠፎባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። የእነዚ ታላላቅ ጋዜጠኞች ‘ወንጀል’ መንግስት እንደሚለው ሳይሆን የሕዝብን በደልና ብሶት ማሰማታቸው ብቻ ነው።
ዛሬ ዛሬ ደግሞ ላለፉት 23 ዓመታት ሃሳባቸውን በነጻነት ከሚገልጹት ጋዜጠኞች ባልተናነሰ በመንግስት ጥርስ እየተነከሰባቸው የሚገኙት የጥበብ ባለሙያዎች እየሆኑ ነው።
እንደሚታወቀው በስደት ዓለም ከ150 በላይ ጋዜጠኞች እንዳሉ ሁሉ ዛሬ ቁጥራቸው በዛ ያሉ አርቲስቶችም በስደት ይህንን ስርዓት በመሸሽ በስደት ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ መንግስት እንደታላቁ እስክንድር ነጋ አስሮ ለማሰቃየት ከሚፈልጋቸው ታላላቅ አርቲስቶች መካከል 3ቱ ዋነኞቹ ሲሆኑ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ገና መንግስት እያጎበጎበባቸው በመሆኑ የ3ቱን ገድል አሳይቻችሁ የሁለቱን እንስት አርቲስቶችን ማንነት አስተዋውቃችኋለሁ።
............1ኛ. ታማኝ በየነ
ብዙዎች እንደስሙ ነው ይሉታል። አክቲቪስት ሆኗል ከአርቲስትነቱ በተጨማሪ። አላሙዲ ካደረገለት በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረገልኝ ይበልጣል በሚል ዛሬም ድረስ የያዘውን አቋም ባለማዋዠቅ ይህን ተራ መንግስት ማንነቱን በማጋለጥ ላይ ይገኛል። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ “የሕዝብ ልጅ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ታማኝ በየነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አንባገነን ስርዓት ከዚህ አርቲስት ጎን ፎቶ የተነሳ፣ የታየ፣ ሻይ የጠጣ አሸባሪ ነው የሚል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል። ታማኝ በየነ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ክብርን ያገኘ በመሆኑና ክብሩንም ለገንዘብም ይሁን ለታይታ ያልቀየረ በመሆኑ ብዙዎች የሚያከብሩት ሲሆን የሕወሓት መንግስት ይህን ታላቅ አርቲስት በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የማፈነቅለው ድንጋይ የለም።
ታማኝ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሳይሆን በግሉ በሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በነፃነት እያጋለጠ ዘረኛውን ስርዓት እርቃኑን እያስቀረው ሲሆን በተለይም መንግስትን የሚያጋልጠው ራሳቸው የመንግስት ባለስልጣናት በሚሰጡት እርስ በእርሱ በሚጣረስ በቪድዮ የታጀበ ቃለምልል መሆኑ በብዙሃን ዘንድ ተወዳጅነትን በሥርዓቱ ዘንድ ደግሞ ለመታሰር ከሚፈለጉ 3ቱ አርቲስቶች መካከል አንዱ ሆኗል።
.................2ኛ. ፋሲል ደመወዝ
አርቲስት ፋሲል ደመወዝን የማውቀው አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሚባል ሰፈር በተለምዶው ሸለቆ የሚባል አካባቢ ነው። በሸለቆ አካባቢ ሲራመዱ ፋሲል ሙዚቃ በመለማመድ ላይ እያለ የሚያሰማውን እንጉርጉሮ ማድመጥ የተለመደ ነው። ይህ ታላቅ ድምፃዊ የጎንደር መሬት ለሱዳን ተላልፎ በሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት በተሰጠበት ወቅት “አረሱት” የሚል ዘፈን ካወጣ በኋላ በስር ዓቱ ሰዎች ወፌ ላላ ተገርፏል። ፋሲል ታዝሎ እስኪሄድ ድረስ በዚህ ፋሽስት መንግስት የተገረፈ ከመሆኑም በላይ የዳነው በህክምና ብቻ ሳይሆን በጸበልም ጭምር ነው።
ፋሲል ደመወዝ አሁን ሰሜን አሜሪካ ከመጣ በኋላ ‘እንቆልሽ” በሚለው አልበሙ ‘ያውላችሁ’ የሚል ዘፈን ያወጣ ሲሆን በዚህም ዘፈኑ ሃገሪቱን ካለምንም ተቀናቃኝ በአፓርታይድ ስርዓት ለሚመሩት ሰዎች “ሰው አስተዳደራችሁን እና በደላችሁን ጥሎ ጥሏችሁ እየሄደ ነው” ሲል ነግሯቸዋል። ፋሲል ደሞዝ በአሁኑ ሰዓት በሕወሓት አስተዳደር ከሚፈለጉ ዋና አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው።
....................3ኛ. ክበበው ገዳ
ኮሜዲያን ነው። በጣም ይወደዳል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያም ይቀልዳል – ክበበው ገዳ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እሱን የሚያል ኮሜዲያን አለ ብሎ ለመናገርም ይከብዳል ይላሉ በሙያው ውስጥ ያሉ ሰዎች እና ባለሙያዎች። ክበበው ገዳ በማንኛውም ማህበራዊ ሕይወት ዙሪያ በመቀልድ ይታውቃል። ይህ ኮሜዲያን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በመመላለስ የተለያዩ የኮሜዲ ሥራዎችን አቅርቦ ተመልሷል። የዘንድሮው ግን ለጉድ ነው። የሥርዓቱን ሰዎች በእጅጉ እስቆትቷል።
ባለፈው ኦገስት 2014 ላይ ክበበው ገዳ በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ በዓል አስተናጋጅነት ትልቅ በዓል ላይ ተገኝቶ ነበር። ይህ ኮሜዲያን አሁን ባለው የኢትዮጵያውያን ነባራዊ ሁኔታ ዙሪያ በርካታ ቀልዶችን አቀረበ። በተለይም አሁን ባለው ስርዓት ዙሪያ ልክ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ኮሜዲያን በመሪዎቻቸው እንደሚቀልዱት ሁሉ ቀለደ። የሕዝቡን ብሶትም በቀልዱ አሰማ። ስለሟቹ ጠ/ሚ/ር፣ ስለሟቹ ፓትሪያሪክ፣ አሁን ስላለው የመንግስት አካሄድ በቀልድ አዋዝቶ አቀረበ። ለዚህ ኮሜዲያን ከሕዝብ የቀረበለት አድናቆትን ቢሆንም ከ ስርዓቱ ግን የቀረበለት ማስፈራሪያና ዛቻ ነው። እንደውም ‘ሃገርህ ትገባታለህ” የሚሉ ዛቻዎች ከስርዓቱ ደርሶታል። ክበበው ሙያውን ተጠቅሞ ባስተላለፈው መልዕክት ከኢትዮጵያ መንግስት ተላላኪዎች የሚደርስበት ማስፈራሪያ ሃገርህ ብትገባ አለቀልህ የሚል ብቻ ሳይሆን አሁን ባለበት ሃገር ሳይቀር እንደማይለቁት የሚገልጹ ናቸው።
...............ማነህ ባለሳምንት?
ሜሮን ጌትነትና አስቴር በዳኔ።
ሁለቱም ሴት አርቲስቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደርሰውን የሴት ልጅ ተጽ ዕኖ ተቋቁመው አደባባይ የወጡ ሴቶች። ሁለቱም ያመኑመትን ይናገራሉ። ሁለቱም በተለይ ሃገር ቤት ካሉ አርርቲስቶች የሚለዩበት ነገር አላቸው። እነዚህ አርቲስቶች ስለ እውነት እውነትን ስለመሰከሩ ዛሬ በ ሥ ር ዓቱ ሰዎች እየተነከሰባቸው ያለውን ነገር አብረን እያየነው ነው።
source.-http://www.zehabesha.com/amharic/?p=38449
Monday, 26 January 2015
የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር በእስር ላይ ይገኛል
የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው አቶ ፍቃዱ ማህተመወርቅ፤ የሃገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ‹‹ተገቢውን ግብር ለመንግሥት ገቢ አላደረክም›› በሚል ክስ ከጥር 13 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውል አድርጎታል።
. አቶ ፍቃዱ ማህተመወርቅ
የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር በእስር ላይ ይገኛል
አቶ ፈቃዱ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የቀድሞ ጉምሩክ መ/ቤት ወይም በአሁኑ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀጥታና የሕግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ቅጽር ግቢ በሚገኘው እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን ፖሊስ ሐሙስ ጥር 14 2007 ዓ.ም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ከሠላሳ አራዳ ጊዮርጊስ ፍ/ቤት ያቀረበው ቢሆንም የዋስትና መብቱ ሳይጠበቅ ለጥር 21 ቀን ከቀትር በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶት ወደ እስር ቤት ተመልሷል።
አቶ ፍቃዱን ያሳሰረው የሃገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰቢያ መ/ቤት ‹‹የዕንቁ መጽሔት እየታተመች በነበረችበት ጊዜ የመጽሔቷ አሳታሚና ባለቤት ለመንግሥት ገቢ ማድረግ የሚገባቸውን 600 ሺኅ ብር አስቀርተዋል›› የሚል ሲሆን ፍ/ቤት ቀርቦም ‹‹ግለሰቡን በሕግ የምጠይቅበትን ሠነድ አሰባስቤ ያልጨረስኩ በመሆኑ ለሰባት ቀናት በእስር ላይ ይቆዩልኝ…›› የሚል ጥያቄ አቅርቦ ለጊዜው በፍርድ ቤቱ በኩል ተቀባይነት አግኝቷል።
የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው አቶ ፈቃዱ ማህተመ ወርቅ ‹‹ፖሊስ የመሰረተብኝ ክስ እኔን የሚመለከት አይደለም ›› ያሉ ሲሆን፤ በሕግ የሚጠየቁበት ጉዳይ ካለም የዋስትና መብታቸውን ሊያስነፍግ እንደማይችል፣ ሕጉም በአግባቡ የሚተረጎም ከሆነ ከእስር ነጻ የመሆን ዕድል እንዳላቸው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=4118#sthash.2CpcMnqj.dpuf
አርቲስት አስቴር በዳኔ ከዚያ ሁሉ መንጋ ተነጥላ። ‘እውነት ነጻ ያወጣችኋል!’
የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። “ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።…”
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ “ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።…”
ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች ትእዛዝ መሆንዋ ነው። አጭር፣ ግልጽ እና ቀጭን መልዕክት ነበረች።
የስርዓቱ ደጋፊ ሳይሆን ይልቁንም ተደጋፊ የሆኑት ሁሉ የዘመቻውን ጥሪ በደስታ ተቀበሉ። ወደ ደደቢትም አመሩ። የታዘቡትንም ነገር ሲናገሩ ሰማን።
ልብ እንበል! እነዚህ የጥበብ ሰዎች ናቸው። ጥበብ ደግሞ የሕዝብ አገልጋይ ናት። ጥበብ ለእውነት የምትቆም ዘብ ናት። ጥበብ አንድን ህብረተሰብ የመቅረጽ እና የመለወጥ ሃይል አላት።
በአለማችን የጥበብ ሰዎች ሚና ጎልቶ የሚታየው ተፈጥሮ ባደላቸው የጥበብ ስራ ብቻ ሳይሆን፤ እነዚህ ሰዎች በጥበብ ስራቸው ውስጥ ለህዝብ በሚያስተላልፉት እውነተኛ መልእክትም ጭምር ነው።
አርቲስቶች አክቲቪስቶች መሆን አለባቸው ብሎ መከራከር አይቻልም። ይህ የራሳቸው ምርጫ ነው። መሆን ካለባቸው ግን የህዝብን እንባ ማበስ ነው የሚገባቸው። ወቅቱን ጠብቆ እንደሚቀየር ድሪቶ መንግስት ሳይሆን ከህዝብ ጎን መቆም ያስከብራቸዋል።
ጥበብ ቆራጥነትን ትጠይቃለች። መስዋዕትነትን ልታስከፍልም ትችላለች። ፍሬዋ ግን ሁል ጊዜ ጣፋጭ ነው። እውቁ ቻይናዊ አርቲስት አይ ዌዊ እዚህ ላይ ይጠቀሳል። አሜሪካዊቷ ጁዲ ችካጎም እንዲሁ። ጃማይካዊው ቦብ ማርሌይ እና የናይጄርው ፌላ ኩቲ በአለማችን ላይ ለውጥ ያመጡ የጥበብ ጀግኖች ናቸው። የኛዋ አርቲስት አስቴር በዳኔም ለዚህ ዋቢ ነች። ማህበራዊ ድረ-ገጾች ይህንን አስረግጠውልናል።
aster“ህዝቡ አጎብዳጆች ይለናል።” አለች አርቲስት አስቴር በዳኔ ከዚያ ሁሉ መንጋ ተነጥላ። ‘እውነት ነጻ ያወጣችኋል!’ የሚለው ክርስቶሳዊ አባባል የተዋሃዳት ወጣት። እውነትን ተናግራ ራስዋን ነጻ አወጣች። እርግጥም የህሊና ነጻነትዋን ለማወጅ መድፈር ነበረባት። ማማጥም ነበረባት። አርቲስትዋ እንደጦር የፈራችው ከፊትዋ ተደርድረው የነበሩ ጉምቱ ባለግዜዎች አልነበሩም። ምክንያቱም ጉዳዩን ለነሱ አስቀድማ ተናግራ ነበርና። ይልቁንም ከአጠገብዋ የነበሩ የስራ ባልደረቦችዋ እና የሙያ አጋሮችዋ እንደጦር ያስፈራሉ። እንደ ይሁዳ አሳልፈው ሊሰጧትም ይችላሉ። ደደቢት ላይ ሲደርሱ ሁሉም በአንድ ማሰብ ጀመሩ። ደደቡ… አንድ ግዜ ተኑሮ ለሚሞትበት አለም ሁሉም ከራሱ ተጣላ። ሁሉም ከህሊናው ሸሸ። ሁሉም ለማደር አጎብዳጅ ሆነ። በመጨረሻም ሁሉም አስቴርን በአርባ ክንድ ራቁዋት። ግና እርሷ ጣርያ ስትነካ እነሱ ደግሞ ሲዘቅጡ አየን።
የኪነ-ጥበብ ሰዎቻችንን መፈተኛ ግዜ ብቅ አለ። ግን ይህ ሁሉ ወጪ እና ሽርጉድ ለምን አስፈለገ?
ጉዞውን ከመጪው ምርጫ ጋር የሚያያይዙ ወገኖች አሉ። ጉዞውን እንደምርጫ ዘመቻነት ለመጠቀም…። ይህ የዋህነት ይመስላል። ምክንያቱም ህወሃት አንድም ግዜ በምርጫ ዘመቻና ግልጽ በሆነ ውድድር ምርጫ አሸንፎ አያውቅም። ነብሳቸውን ይማርና አቶ መለስ ከነ ስዬ ቡድን ጋር በተለያዩ ግዜ ተናግረውታል። “ህወሃት በስብሷል!” ነበር ያሉት። ላለፉት ፪፫ አመታት ይህ የበሰበሰ ስርዓት ነው ሃገሪቱን እየገዛ ያለው። ይህ የበሰበሰ ስርዓት በምርጫ ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በመስረቅ ነው እስካሁን ያለው።
ከምናከብራቸውና ከየምናደንቃቸው የኪነጥበብ ስዎች ውዳሴዎች ሰማን። ንዋይ ደበበም እጅግ አድርጎ ሲረግመው በነበረው ደደቢት ላይ ዘፈነ። እንዲያውም በስሜት ዘፈነ። “የሃገር ነቀርሳዎች” ሲላቸው የነበሩትን እነ ሳሞራን፣ እነ አባዱላን፣ … እያቀፈ … አልረሳም እያለ አቀነቀነ።neway serawit
በዚያ የቀውጢ ወቅት ከሰለሞን ተካልኝ ከተቃዋሚ ወገን ወጥቶ ህወሃትን ሲቀላቀል ድምጻዊው ነዋይ ደበበ እንደ እብድ ነበር ያደረገው። ያዙኝ፤ ልቀቁኝ አለ። የንዴት ቃላትን ሁሉ በዘፋኙ ላይ አዥጎደጎደው። “ማሰብ የማይችል ደደብ ሰው!” አለ ነዋይ። ቀጠለናም “ሰለሞን ተካልኝ ስጋ የሚበላ በሬ ነው።” ሲል ድምጻዊውን ከሰብአዊ ፍጡርነት ወደ እንስሣነት ጎራ መድቦት ነበር።
ዛሬ በዚያው መድረክ ላይ አዲስ ትእይንት እያየን ነው። የግዜ ሃዲድ ላይ ሆኖ የሚመለከተው ሁሉ በትዝብት የሚያስቆዝም አሳዛኝ ድራማ፤ አርቲስት ብለን የምንጠራቸው ወገኖቻችን የሚፈጽሙት የፖለቲካ ዝሙት። ነዋይ ደበበ በግዙፉ የሰለሞን ተካልኝን ትከሻው ላይ ለመጠምጠም እጆቹ በጣም ሲረዝሙ በመገናኛ ብዙሃን ተመለከትን። … አጃኢብ አለ ያገሬ ሰው!
አዕምሮ ማሰብ ሲያቆም፣ አንገታቸው አዙሮ ማየት ሲሳነው፣ ልቦናችን የቅርቡን ክስተት ሲዘነጋ፣ የስነ-ልቦና ችግር ነው ከማለት ውጭ ምን ይባላል?
የሰራዊት ፍቅሬ ማጎብደድ ደግሞ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም። ይህ ሰው በ፩፱፹ዎቹ በነበረው የርስ በርስ ውግያ ወታደር ሆኖ ከደርግ ወገን ነበር የተሰለፈው። ዛሬ በሽሬ ሽንፈቱ ላይ ጥሎት የሸሸው የጦር ታንክ ላይ ቆሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጆቹን እያወጣ ደግም ቀለደ። ለካስ ደርግ እንደዚህም አይነት ወታደር ይዞ ነበር ህወሃትን ይፋለም የነበረ? ሰራዊት ፍቅሬ ዛሬ ዝናው ሳይሆን ሃብቱ ጣርያ ነክቷል። አሰልቺ ድምጹና ምስሉ እጅ-እጅ እስኪል በቴሌቪዥን እንዲቀርብ በገዢው ፓርቲ ተፈቅዶለታል። ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውሉ የስርዓቱ በዓላት ቁጥር እጅግ በዝተዋል። የብሄር ብሄረሰቦች ቀን፣ የከተሞች ቀን፣ የአርሶ አደሮች ቀን፣ የአርብቶ አደሮች ቀን፣ … ባዛር ለልማት ወዘተ። የማስታወቂያ ወጪው ከዝግጅቱ ወጪ አይተናነስም። ሁሉንም የማስታወቂያ ስራ ለሰራዊት ፍቅሬ ሰጥተውታል። ታዲያ እሱም ገሚሱን ለባለስልጣናቱ ማካፈሉ የግድ ነው። የዚህ ሰው መንቀልቀል ምስጢር ይህ ብቻ ነው። ሰራዊት ፍቅሬ በዚህ ሁኔታ የማስታወቂያ ስራውን በሙስና መስመር ውስጥ አዝልቆታል።
አንደኛው ተደጋፊም ተነስቶ ”ይህ ነገር በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፊት ለፊት ሃውልት ሊሰራለት ይገባል።” ሲል ተደመጠ። ሰውዬው ይህንን አምኖበት እንዳልተናገረ ሰዎቹም ይገምታሉ። መቼም ለእለት ጉርስ ሲባል እንደዚህ አይነት ለህሊና የሚጎረብጥ ነገር እያደረጉ ከመኖር፤ በልመና መተዳደር ክብር ነው።
ከጅምሩ የስርዓቱን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሂደት ለመገምገም ወደ ደደቢት በረሃ መሄድም አያስፈልግም። ኢትዮጵያ ዛሬ ከገባችበት መከራ ለማውጣት የህወሃት አነሳስን ማጥናት ምንም ፋይዳ የለውም። መነሻው ጥሩም ይሁን መጥፎ፣ መድረሻው ግን አላማረም። ይህ ስርዓት ሃገሪቱን ባህር አልባ አገር አድርጓታል። የባህር በር የአንድ ሃገር ምስጢርም ነው። ኢትዮጵያ እንደ ማንኛውም ሉአላዊ ሃገር ምስጢር እንኳን የላትም።
ህዝቧም ከአፈናው ሰንሰለት ገና አልወጣም።
በአመለካከት ልዩነታቸው ብቻ ወገኖቻችን እንደ ጥጃ ሲታሰሩ የደደቢት ተጓዦቹ ይመለከታሉ። ሃሳባቸውን በነጻ የገለጹ ዜጎች የሽብርተኛነት ታርጋ ተለጥፎላቸው በግፍ ሲፈረድባቸው ይሰማሉ። ኢትዮጵያውያን እንደ ምጽዓት ሲሰደዱ በአይናቸው ይመለከታሉ። ለነጻነትና ለእኩልነት ታግለን መጣን የሚሉን ደግሞ በአንዲት ጀንበር ሚሊየነር ሲሆኑ ይታዘባሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እንደሙያቸው አንዲት ቃል እንኳን ተንፍሰው አያውቁም። ወደ በረሃው መጓዙ እንደ ሲሲሊው የማፍያ ቡድን ከደደቢት ምሽግ ውስጥ ቃል-ኪዳን ለመግባባት ካልሆነ በቀር ፋይዳው አይታይም።
“ህዝቡ አጎብዳጆች ይለናል።” አለች አስቴር በዳኔ። ህዝብ ምን እንደሚላቸው የምትሰማው እርሷ ብቻ አይደለችም። ጆሮ ያለው ሁሉ ይሰማዋል። ይህን እያወቁ ግን አጎብዳጅ ምሆናቸውን ጭራሽ በብሄራዊ ቴሌቭዥን ወጥተው አሳዩን።
ህዝቡ ብቻ አይደለም። በእርግጠኝነት ለመናገር እነዚያ ባለ-ስልጣናትም አድርባዮቹን ይንቋቸዋል። በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ህወሃት እንደሆነ ተናግረው ነበር። “አድርባይነት” ስርዓቱን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱን ከመግለጻቸውም በላይ አድርባዮቹን እንዴት እንደሚበቀሏቸውም ባህርዳር ላይ መክረዋል።
ደብረጽዮን ትእዛዙን ሲሰጡ ትንሽም ቢሆን ዲፕሎማት ነበሩ። ከትእዛዞቻቸው መሃል እንዲት እንዲህ የምትል መልእክት ነበረች። “…ችግሮቻችንንም ንገሩን።”
ይህች ሃረግ የኪነ-ጥበብ ሰዎቹ የህዝብን ብሶት በአደባባይ እንዲናገሩ በር ከፋች ነበረች። እነ አበበ ባልቻ ይህችን እድል ተጠቅመው ስለ-ኪነጥበብ መውደቅ እንኳን ትንሽ መልእክት ከማስተላለፍ ይልቅ ልወደድ ባይነትን መረጡ። ይህን ጥሬ ሃቅ የመናገር ድፍረት ያለው አንድ ሰው ጠፋ። ሁሉም ምስጋናና ውዳሴውን አበዛ። ለማደር የሚደረግ ካንገት በላይ ውዳሴ … መቼም ያሳዝናል።
በጭምጭምታም እንደሰማነው፤ በደደቢት አንዳች የተለወጠ ነገር የለም። ደደቢት ድሮም በረሃ – አሁንም በረሃ ነው። የአካባቢው ህዝብ ላይም ምንም የሚታይ ለውጥ የለም። ይህ ህዝብ ከሃያ አመታት በፊት የመናገር መብት አልነበረውም። ይህ መብት አሁን ብሶበት ሕዝቡ የመናገር ብቻ ሳይሆን የውጭ ራዲዮ እንኳን የመስማት መብቱን ተነፍጓል።
ይህችን ሃቅ የጎበኘ አንድ የኪነ-ጥበብ ባለሞያ እንዴት አስችሎት ዝም ይላል? ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነበር። “ስለ እውነት የቆመ አንድ ሰው ይጥፋ?” የሚለው ጥያቄ በህዝብ ዘንድ እየተብላላ እያለ ነበር አስቴር በዳኔ ብቅ ያለችው። ይህች አርቲስት የህዝቡን ጥያቄ ይዛ በድፍረት ወረወረችው። መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ገጾችም በዚሁ ጉዳይ ተጨናንቀው ከረሙ።
ለድቅድቅ ጨለማ ትንሽ የብርሃን ፍንጣቂ ትበቃለች እንዲሉ የዚያን ሁሉ የውሸት ክምር አንድ እውነት አፈራረሰው። ህዝብ ያከብራቸው የነበሩ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ሁሉ ወረዱ። የማያልፈውን የህዝብ ፍቅር በሚያልፍ ነገር ቀየሩት።
ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶች ሁለት አማራጮች ነበራቸው። ጥሪውን ተቀብሎ ሄዶ እውነትን መመስከር አሊያም እንደ ገጣሚ ታገል ሰይፉ ጥሪውን አለመቀበል። ገጣሚ ታገል ሰይፉ በኤፍ ኤም ፱፯ ራዲዮ ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው።
“ባለፈው የመቀሌ ጉዞ ላይ እኔ አልሄድኩም። አርቲስቶች ሲሄዱ ጥሪ ተደርጎልኛል። ነገር ግን የደደቢቱን ጉዞ ስላላመንኩበት ቀርቻለሁ። ስለማልፈልገው ማለት ነው። … ለነሱም የምለው ነው። በተለይ ባለፉት 15 አመታት ብዙ ነገር አልተሰራም። ለስነ ጽሁፍ የሚመች ግዜ አይደለም። ስነጽሁፍን ትኩረት አልሰጡትም። እያየን ነው።“
ታገል ሰይፉ ቀደም ሲልም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሃሳቡን ተቆርጦ እንዳስቀረበት ተናግሯል። ደደቢት ድረስ ሄዶ ሃሳቡን የማያስተላልፉለት ከሆነ መቅረቱ አይነተኛ አማራጭ ነው። አበበ ባልቻን፤ ሙሉ አለምን፣ ነዋይ ደበበን፣ … አርቲስቶች እና የኪነጥበብ ሰዎች ብለን ጠርተን፤ አስቴርንና ታገል ሰይፉን ምን ልንላቸው ይሆን? … ማህበራዊ ፍርዱን ከህዝቡ ያገኙታል።
ህወሃት ግን አንድ መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር አርቲስቶቹን ወደ ደደቢት የወሰዳቸው። እዚህ ተነስተን፣ አፈር ለብሰን፣ አፈር በልተን፣ የፈረስ ሽንት ጠጥተን የያዝናት ስልጣን ናት። ይህችን ስልጣን በምርጫ እንደማናስረክብ እናንተም አረጋግጡልን … እንዲሁ ተቃጥላችሁ ታልቃላችሁ እንጂ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ አታስቡ … የሚል መልዕክት።
እኔም በዚህች ቀልድ ጽሁፌን ልቋጭ። አንድ የህንድ ኢንቨስተር አዲስ አበባ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያንን የቀብር ስፍራ አይቶ በሊዝ ሊገዛ ፈለገ። የአዲስ አበባ ባለስልጣናትን ጠርቶ እንዲሸጡለት ጠየቀ። ባለስልጣናቱም መልሰው ሌሎች ቦታዎች ሳያልቁ የቀብር ስፍራ ለግዜው እንደማይሸጡለት ነገሩት። ህንዱ መለሰና መከራቸው። “እኛ አገር ሰው ሲሞት እናቃጥላለን እንጂ አንቀብርም። ለምን ይህን ለም ቦታ ታባክናላችሁ?” ባለስልጣናቱ መለሱ፣ “እኛ አገር ደግሞ ሰውን በቁሙ ነው እንጂ ሲሞት አናቃጥልም!”
SOURCE,-http://www.goolgule.com/trip-to-dedebit-serawit-to-tagel/
የደም አኬልዳማ
ወያኔ ዛሬም መግደል ማሰርን ህዝብን ማሰቃየቱን ቀጥሏል ጩቁኑ ህዝብ በወያኔ ቅልብተኞች ድብደባ እየተፈፀመበት ነው ።ወዴት ነው ጉዞው ፍታዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በእውነት በኢትዮጲያ አለ? ዲሞክራሲን ህዝብ ከሻታ ቆየ ወያኔ ግን ህዝቡን እንደ አህያ መርገጡን አላቆመም።ቀን አንድነት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከባድ የሆነ እርምጃ ወስዷል ምርጫ ከማን ጋር ነው ፉክክሩ? ወያኔ እራሱ ብቻውን ተወዳድሮ ብቻውን ለማሸነፍ ይመስል ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማሰር እና ማሰቃየቱን ቀጥሏል ።አንዱ ለአንዱ መተማመን ቀርቷል እንደ አሸን በፈሉ ጆሮ ጠቢዎች (ደህንነቶች) ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ እንኳ አልተቻለም ።
ምርጫ ተባለ ማነው የሚወዳደረው ሁሉም በእስር ናቸው ።ዲሞክራሲን ምርጫ መናፈቅ ማለት በሬን ውለድ እንደማለት ነው ወያኔ ህዝብን እያሰቃየ መግዛት እንጂ በዲሞክራሲ ምርጫ ይወርዳል ብሎ ማሰብ የዛሬን የቀን, , ,የአንድነትን ሰልፍ በቀላሉ እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል።
bostd by samuel adem
Friday, 23 January 2015
“ለልጆቼ የማይሆን ተስፋ አልነግራቸውም” የነፃነቱ ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ
ከልጅ አያሌው
ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ትግል እስከወዲያኛው ከዳር ለማድረስ ቆርጦ ልጆቼን ቤተሰቦቼን ሳይል ከራሱ በላይ በሀገሩ ፍቅር ተበልጦ የተሻለ ነው የሚለውን፣ አማራጭ የሌለውን፣ የኤርትራን ጫካ መርጦ የማይቻል የሚመስለውን ችሎ ብዙዎች ፈቀቅ ማድረግ ያቃታቸውን የመተባበር የመያያዝ በአንድ ገብቶ ለአንድ አላማ የመታገልና ኢትዮጵያን እንደቀደመው ታላቅ ሀገር የማድረግ ውጥን የተሻለና የሚያግባባ ሀሳብ በመሸከፍ ከሚመራው ንቅናቄ ከግንቦት 7 ጋር እጅግ እውነት የማይመስሉ ድንቅ ስራዋችን በመስራት ጠማማውን በማቅናት ኮረብታውን በመደልደል አንድ መሆን ሳይችሉ ለአመታት ሲኳትኑ የነበሩትን በኢትዮጵያዊነት እንዲተሳሰሩ በማድረግ ፍቅር የሰራ ትልቁን መሰረት የጣለ ምርጥ የኢትዮጵ የቁርጥ ልጅ አንዳርጋቸው ፅጌ።
ዛሬ እሱ በማረፍያው ሰዓት አግባብ ባልሆነ መንገድ ከአውሬዋች እጅ ወድቆ ይህን መልዕክት አስተላልፏል። ለልጆቼ የማይሆን ተስፋ አልነግራቸውም።
ይሄ መልዕክት ኢትዮጵያን ለሚወዱ ሁሉ እጅግ የሚያም ነው ምክንያቱም እየከፈለ ያለው መሰዋት ለኛ ለኢትዮጵያኖች ስለሆነ።
አንዳርጋቸውን ከግንቦት 7፣ ግንቦት 7ን ከአንዳርጋቸው መነጠሉ የማይሞከር ነው ምክንያቱም ሀቁ የሚነግረን እሱና እሱን ከሚመስሉ ወንድሞች ጋር ታላቅ የሆነ ኢትዮጵያን የማዳን ራዕይ ሰንቀው በግድ ሳይሆን በፍቅር ተሳስረው አንዳይነት አላማ አንግበው ማድረግ ከሚችሉት በላይ ሌተቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከማንም በላይ የየግል ህይወታቸውን መኖር እየቻሉ ያለመታከት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ታላቅ ለማድረግ የተሰለፉለት አላማ መሆኑ በግልፅ የሚታይ ሀቅ ስለሆነ።
ታድያ አንዳንዶች የኢትዮጵያዊነትን ካባ የለበሱ የሚመስሉ እየደረሰበት ያለውን ስቃይ በመኮነን ድንቅ ሰው ታላቅ ሰው መሆኑን አክለውበት ጀግናችን ነው ብለው ሲያበቁ አንዳርጋቸውና ንቅናቄው አምነውበት: በአሁን ሰአት ካለው የሀገራችን አንዲሁም የጎረቤት ሀገራት ሁኔታን በማጤን አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን በመረዳት በትግል የዘረጉትን ገመድ በጥሶ ለመጣል ያስችለናል የሚሉትን የሰነፍ ስንቅ በመሰነቅ እየተሄደበት ያለውን መልካም መንገድ ፈንጂ የተጠመደበት በማስመሰል አንዳንዴ በዛበኩል ትግል ለሚያደርጉት ከልብ ያዘኑ በመምሰል አልሆን ሲላቸው ደግሞ በዛ በኩል የሚደረግ ጉዞ ለሀገር አደጋ አለው በማለት ነጋ ጠባ ያለ ህፍረት መከራቸውን ሲያዩ ስምለከት ከሚቆረጥላቸው አበል ጥቂቱን እንኳን ደጉሜ ነፃ ሰው ባደርጋቸው እልና ፀረ ትግልና ፀረ ነፃነት መሆናቸው ሲታወሰኝ ከእንዲህ አይነቱ ሱስና አመል ማላቀቁ ከአቅሜ በላይ መሆኑን ሳውቀው አንድላይ ደባልቆ ማሸቱን እመርጥና እተወዋለው።
በነገራችን ላይ ይሄ አባዜ በነዚህ እኩይ ተግባር ባላቸው ጥቂት ሰዋች ብቻም አይቀነቀንም ይልቁንም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ያለምንም ማወላወል አንገታቸውን ሊሰጡ በሚችሉ ሰዋችም ወቅት አየጠበቀ እንደሚያጓራ ዛር ሲያወራጫቸው ይስተውላል ታድያ የችግሩን መንስኤ ሳጠናው ፍቅር ሆኖ አግኝቸዋለው ፍቅር ደሞ እዚ ውስጥ ምን ከተተው ትሉኝ ይሆናል? ይሄኛው ወዲህ ነው አትጣበቅ እንጂ አንዴ ከተጣበክ አትታጠር እንጂ አንዴ አጥር ከሰራህ ማየትም መስማትም የምትፈልገው ያፈቀርከውን ብቻ ነው ወገኖቼ በድርጅት ፍቅር እንዳታብዱ የትም ስለማያደርስ :አንዴ ግን ከተለከፋቹ የተሰራው እናንተ ካልሰራችሁት የተጀመረው እናንተ ካልጀመራችሁት የታሰበው መልካም ሀሳብ ከናንተ ቀድሞ ካልፈለቀ ገደል አፋፍ ላይ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ተይዛቹ እንኳን የማዳን እጅ ቢዘረጋ አይናቹ ማየት የለመደውና የምታፈቅሩት እጅ አለመሆኑን ስታውቁ መዳንን ትፀየፉታላቹ ገደል መግባቱን ትመርጣላቹ ስለዚ እውነት ሀገራችንን ማዳን ከፈለግን ሜዳው ሰፊ ነውና እኔ ካልባረኩት የሚለውን ፍሬ ከርስኪ ትተን ሌላውን ከመጎተት የተሻለ የምንለውን ሜዳ በመምረጥ ለሀገራችን አለኝታ እንሁን።
ሌላኛው ደግሞ እጅና እግሩ ተጠፍንጎ የታሰረበት ይመስል ከማሳየት ይልቅ ጥግ ይዞ የታላቹ፣ የት ገባቹ፣ ጦርነት የሆሊውድን ፊልም አይነት እየመሰው በከንቱ ምኞት መሬት ላይ ወርዶ ህይወቱን ለሀገሩ አሳልፎ ለመስጠት ነጋ ጠባ መከራውን የሚያየውን የነፃነቱን አርበኛ ከሶፋው ላይ ተደላድሎ ተቀምጦ እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ ቢራውን እየተጎነጨ ከኮንፒውተር ጀርባ ሆኖ ሲከተክተው ይውላል ደሞ እፍረትም የለውም ትግላችን፣ የኛ ትግል፣ እያለ እየደጋገመ ሲናገር ይደመጣል እኔ ግን እላለው: መጀመርያ እጃችንን ከኪሳችን ታግለን ነፃ እናውጣው። ሀገራችንን ለማዳን የሚደረገውን ትግል ለመደገፍ ሰበብ አንደርድር።
በመጨረሻም አንድ ወዳጄ ለጨዋታ ባወረዳት ቅኔ ለጠቅ አድርጌም የኔንም የመልስ ምት አክዬ ልደምድም፣
እኔ እናገራለሁ ቆሜ ከፊታቹ
ጠሀይ አልወጣ አለች ከሰሜን ወርዳቹ
መልስ
የጠሀይን መውጫ ልብህ እያወቀው
ብላ ተኛ ሆነህ የቆረጠውን ሰው
በየትኛው ወኔነው የምትጠይቀው
ቅኔው የወዳጄ ሆና እሱ ባያቀነቅናትም ይህቺን ዘፈን ብዙዋች ይዘፍኗታል እስኪ ካስተማረች በተን ላድርጋት፣
ለመሆኑ የጠሀይ መውጫ በሰሜን ሆነ እንዴ? የኔ ጥያቄ ነው ጠሀይ በምስራቅ ወጥታ በምዕራብ ትጠልቃለች የወዳጄ ጠሀይ ግን :ከወትሮው ለየት አለችብኘ ለነገሩ ራቅ አድርገው ካሰቡት ጠሀይ በእድሜም የጠገበች እንደመሆኗ ተወዳጅነቷ ዋዛ እንደማይሆን አልጠራጠርም።
ወዳጄም የመናፈቅ ብዛት ሳያናግረው አልቀረም ስለዚህ ወንድሜ ጠሀይን እኛ አላገድናትም መውጫዋም በምስራቅ ነው እኛ ግን መንደርደርያ የለንምና በሰሜን ከተናል ባይሆን ባገኘናት እድል ተጠቅመን ከሰሜን ተነስተን የጠፋችብህን ጠሀይ ከዚህ ሰፈር ሳይሆን ሰፈሯ ድረስ በመምጣት ብቅ እንድትል ማረጋችን እንደማይቀር ላረጋግጥልህ እወዳለሁ የምትቸኩል ትዕግስት የሌለህ ከሆነ ግን ጠሀይ ብቅ እንድትል ስትፈልግ በደቡብ፣ ስትፈልግ በምዕራብ፣ የሚያስጠጋህ ከገኘህ በዛ በኩል ሞክር።
ምስራቁ ቅርብ ነውና ባትደላደል እንኳን ጫፍ የሚያስይዝህ ካገኘህ ያው መደወል አትወድም ምልክት አድርግልኝ ያለህበት ድረስ መጥቼ እቀላቀልሀለው እውነቴነው የምልህ ጠሀይቱ እናቴ ጋር እስካደረሰኘ ድረስ የማልቆፍረው ገድጓድ የማልወጣበት ተራራ፣ የማልሞክረው አቋራጭ አይኖርም።
በሰሜን የከተቱት ብዙ ጊዜ ተጠይቀው ሲመልሱት ካደመጥኩት ቅንጭብ የተወሰደ ነው በሚል ይያዝልኝ።
ስለዚ መጠላለፉን ትተን የምንችለውን እናድርግ ያ ከሆነ ትግሉን መሬት ላይ አውርዶ እየሰራ ያለውም በአየር ላይ ያለውም በመጨረሻዋ ቀን የነፃነቷ ጠሀይ በሀገራችን ስትወጣ እኩል ይቋደሳሉና።
ይህንን ለመፃፍ ያነሳሳኝ “ለልጆቼ የማይሆን ተስፋ አልነግራቸውም” የሚለው የጀግናው ታጋይ የአንዳርጋቸው ንግግር መሆኑነ አሰምርበታለሁ።
በዘገየን መጠን የምናጣው ይበዛልና ባለመጠላለፍ ወደፊት እንሂድ፣ እኔ የሁሉም ነኝ የተሻለ አማራጭ ያለው ይገዛኛል።
ኢትዮጵያ ለዘላላም በክብር ትኑር!
እናቸንፋለን!
ልጅ አያሌው
source,-http://www.zehabesha.com/amharic/?p=38237
Thursday, 22 January 2015
አሳዛኝ ዜና ሳሪስ ቻይናዊ 3 ተማሪዎች ሕይወት ቀጠፈ
አሳዛኝ ዜና ሳሪስ የባቡር ፕሮጀክት ስራ የሚሰራ ቻይናዊ በሎደር ማሽን የፍሬ ሕይወት ት/ቤት አጥር በመደርመስ 3 ተማሪዎች ሕይወት ቀጠፈ
ዛሬ ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሳሪስ ካዲስኮ የባቡር ፕሮጀክት ስራ የሚሰራ ቻይናዊ በሎደር ማሽን የፍሬ ሕይወት ት/ቤት አጥር በመደርመስ በስፖርት ክፍለ ጊዜ ግቢ ውስጥ የነበሩ 3 ተማሪዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ በርካታ ተማሪዎች ከፍተኛና መካከለኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ቦታ ሄደዋል፡፡
በተጨማሪም በቅርብ እርቀት ቡና ቦርድ እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ቻይናው የጥበቃ ሰራተኛውን ሲመታው ለመከላከል ሲል በያዘው አጣና ሲመታው በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች ሁለቱንም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡
የሕፃናት ተማሪዎች ያለአግባብ መሞት የፍሬ ሕይወት ተማሪዎች በአስነሱት ከፍተኛ ቁጣ የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ በተማሪዎች ላይ አድርሷል፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው የሕፃናቶች ሞት ሳይታሰብ ቻይናውያንን የፌዴራል ፖሊስ በማጀብ በተዘጋጀላቸው መኪና ወደ ቤታቸው ሲሄዱ የህዝብ መገልገያ በሚመስል ታክሲ በርካታ ተማሪዎች ወደ እስር ቤት ተጉዘዋል፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡
.
source.-http://satenaw.com/amharic/archives/3902
የህወሓት ኣባል ኣልሆንም ያለ ኣስተማሪ በባለ ስልጣናት ከፍተኛ ድብደባ ደረሰበት
ፎቶው የምታዩት ሰውየ ገብረየሱስ ገብረሂወት የተባለ ኣስተማሪ ነው።
የምታዩት ፎቶ የህወሓት ኣባል ኣልሆንም ያለና በባለ ስልጣናት ከፍተኛ ድብደባ ደረሰበት ኣስተማሪ ነው።
መምህር ገብረየሱስ ገብረሂወት በደጉዓ ተምቤን ማሕበረስላሴ ትምህርት ቤት የሚያስተምር ነው።
የድብደባው መነሻ የህወሓት ኣባል ሆኖ መቀጠል ኣልፈልግም በማለቱ የመጣበት ጦስ ነው። ጦሱ ከደምወዙ በቀጥታ ለህወሓት ኣባልነት የሚል በየወሩ ሲቆረጥ ፍቃደኛ ባለ መሆኑና በተደጋጋሚ ሲቆረጥበት ወደ ፍርድ ቤት ሂዶ በመክሰስ ያለፍላጎቱ እንዳይቆረጥበት የሚል ፍርድ በመሰጠቱ የተበሳጩ የወረዳው ሃላፊዎች የወሰዱት ኣብዮታዊ እርምጃ ነው። ነፃ እርምጃ ማለት እንዲህ ኣይደለም..?
ህዝቡ ሳይወድ በግድ ኣባል ሁን ተብሎ የሚቆም መንግስት ምንያህል ዘለቄታ ይነሮዋል..? የደጉዓ ተምቤን የህወሓት ሃላፊዎች ግፋችሁ ለከት ብታበጁለት ይበጃቹሃል እንላለን። ገብረየሱስ ገብረሂወት ድብደባ ከደረሰበት በሗላ በከተማው ተጥሎ እስከ ለሊት ኣስር ሰዓት ተጥሎ ኣምሽተዋል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!
..........IT IS SO…! Amdom Gebreslasie
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3872#sthash.dFj1sFOX.RzQ0UBR2.dpuf
“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በኢትዮጵያ የመገናኛ-ብዙሃን ነጻነት ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰት
(Human Rights Watch) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ 99.6
በመቶ የፓርላማ መቀመጫን ካሸነፈ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና መረጃ
የማግኘት መብትን በመገደብ በግል መገናኛ-ብዙሃን ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አባብሶታል፡፡ እ.ኤ.አ.
ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 60 ጋዜጠኞች ሃገር ለቀው የተሰደዱ ሲሆን ሌሎች 19 ጋዜጠኞች ደግሞ በእስር ላይ
እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ መንግስት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ህትመቶችን ዘግቷል፤ እንዲሁም አብዛኛዎቹን የቴሌቪዥን
እና የሬድዮ ስርጭቶች በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ኢትዮጵየዊያን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ጉዳዮችን በተመለከተ ነጻ
መረጃ እና ትንታኔ የሚያገኙበትን እድል አጣቧል። በግንቦት 2007 በሚካሄደው ምርጫ መገናኛ-ብዙሃኑ ህዝቡን
በወሳኝ ጉዳዮች ላይ በማስተማርም ሆነ መረጃ በመስጠት ረገድ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችሉ ነበር፤ እንዲሁም
የመከራከሪያ መድረክ በመሆን ሊያገለግሉ ይችሉ ነበር፤ ይሁን እንጂ መንግስት በሃገሪቱ ላለው ብቸኛ የበላይነት
የግሉን መገናኛ-ብዙሃን እንደ ስጋት አድርጎ በመውሰድ የግሉን መገናኛ-ብዙሃን፣ ነጻ ጋዜተኝነትን እና ተቺ ትንታኔን
ለማጥፋት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም የከፋ ውጤት አስከትሏል።
የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ የሆነው የኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (Committee to protect Journalists)
መረጃ እና የሂዩማን ራይትስ ዎች ጥናት እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ከኢራን በመቀጠል በዓለም ላይ በርካታ
ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞችን ለስደት የምትዳርግ ሀገር ሆናለች። የመንግስት አካላት አፋኝ ህጎችን መሰረት አድርገው
ጋዜጠኞች በየወቅቱ ያሉ ክስተቶችን እና ጉዳዮችን አስመልከተው በሚሰሩት ዘገባ እና ትንታኔ ምክንያት
በተደጋጋሚ ክስ ይመሰርቱባቸዋል፤ ፍርድ ቤቶችም ክሱን ተከትለው የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ በአሁኑ
ወቅት እስክንድር ነጋን እና ርዕዮት ዓለሙን የመሰሉ ግለሰቦች በአዲስ አበባ እና በክልሎች የሚገኙ ተለይተው
የሚታወቁም ሆነ የማይታወቁ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ጋዜጠኞች እየደረሰባቸው የሚገኘውን ፈተና የሚያሳዩ
ምልክቶች ሆነዋል። ጋዜጠኞቹ በርካታ ስጋት ውስጥ የሚገኙ፣ ማስፈራሪያ የሚደርሳቸው፣ አልፎ አልፎም አካላዊ
ጥቃት የሚፈጸምባቸው እና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የወንጀል ወይንም የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው፡፡
የፍርድ ቤት ክርክራቸው ፍትሃዊ የፍርድ ሂደትን የሚጥሱ አሰራሮች የሚታዩበት ሲሆን ፍርድ ቤቶቹም
በያዟቸው ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው ውሳኔዎች ገለልተኛ እንዳልሆኑ የሚያሳይ ነው።
በኢትዮጵያ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የህትመት መገናኛ-ብዙሃን ከመግስት ጋር የቀረበ ትስስር አላቸው፤ በወሳኝ
ጉዳዮች ላይ ከመንግሰት የተለየ አቋም እምብዛም አያንጸባርቁም።የግል የህትመት መገናኛ-ብዙሃን በርካታ
ከቁጥጥር ጋር የተያያዙ ችግሮች ያጋጥማቸዋል እንዲሁም በደህንነት ሰራተኞች ተከታታይ ወከባ ይደርስባቸዋል፡፡
መንግስትን የሚተቹ የህትመት ውጤቶች በየጊዜው ይዘጋሉ፣ የበሰለ ትችት የሚያቀርቡ የህትመት ውጤቶችን
የሚያትሙ እና የሚያከፋፍሉ አሳታሚዎች እና አከፋፋዮችም ተዘግተዋል፡፡ የመንግስት ፖሊሲዎች ላይ ትችት
የሚሰነዝሩ ጋዜጠኞች እና የቤተሰብ አባሎቻቸው ጭምር የጥቃት፣ የመታሰር እና የገቢ ምንጫቸውን የማጣት
ዘላቂ ስጋት ላይ ይወድቃሉ፡፡ መንግስት አብዛኛውን የመገናኛ-ብዙሃን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ሲሆን የቀሩት ጥቂት
የግል መገናኛ-ብዙሃንም በተለይ ለአሳሳቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሚሰጡት ሽፋን ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ
የሚያደርጉ ያደርጋሉ ይህም እንዘጋለን ከሚል ፍርሃት የመነጨ ነው፡፡
Wednesday, 21 January 2015
Ethiopia’s new expressway left 11dead
Horrific car accident on Ethiopia’s new expressway left 11dead
...............(Addis Standard) An early morning major car accident on Sunday January 18th on the newly opened Addis-Adama expressway has left eleven people dead on impact and nine people wounded. Five of the wounded have received life threatening wounds and are in critical conditions, an investigating officer told Addis Standard.
car accindet
car accident
The accident happened early at around 6:00 am when a driver of a Sinotruk coming from Adama, the capital of Oromia regional state 100 kms South of Addis Abeba, lost its track and derailed into the separation fence of the six lane expressway. The Sinotruck then hit a minivan carrying 16 people and was speeding from Addis Abeba to Adama, reducing the minivan to a quarter of its original size and killing the eleven people on board on impact.
“We have no idea how this could possibly happen,” an investigating officer on the spot told Addis Standard, “we are unable to know whether the driver of the truck is amongst the dead or has left the accident scene.” The driver and the assistant on the minivan were among the dead. Most of the passengers on the minivan were people going to celebrate the Epiphany celebrations of the Ethiopian Orthodox Church with their loved ones, the investigating office who wants to remain anonymous told us.
Due to massive construction works throughout the country, Ethiopia has seen a sharp increase in the numbers of the Chinese made Sinotruks. However, many Ethiopians complain of horrific car accidents caused by these tucks as most of them are operated by poorly trained drivers.
The 84.5 km Addis-Adama expressway, the first for the country, opened for traffic on Sep. 14th 2014. The six-lane expressway was built by China Communications and Construction Co. (CCCC) and financed by the government in Ethiopia and Exim Bank of china, which provided a US$800 million. The expressway has seven toll stations between Tulu Dimtu on the outskirts of Addis Abeba, and the last point in the western part of Adama...............source,-http://www.zehabesha.com/
የሬድዋን የአሜሪካ ቅሌት በስዊድንም ተደገመ
ቀደም ሲል በስዊድን ለቦንድ ሽያጭ ወያኔ ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ቦታ ላይ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው የሽያጩን ዝግጅት በተቃወሙበት ግዜ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆነችው ወ ወይንሸት ታደሰ ድብደባ ደረሶብኛል በማለት ለፖሊስአመልከታ ክስ ለመመስረት ሙከራ አድርጋ ነበር ሆኖም የስዊድን ፖሊስ ሁኔታውን አጥንቶ ለክስ የተጠራችውን የስዊድን ኢትዮስዊድን ግብር ሃይል ሃላፊና አክቲቪስት ወ መቅደስ ወርቁና አቶ ሞላ የኢትዮጵያ ዴሞክራት መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ለፖሊስ የህውአትን ማንነተና አስረድተው የተደረገውም ተቃውሞ በኢትዮጵያ ውስት የሚደረገወን የሰባዊ መብት ጥሰትን በመቃወም በመሆኑና የስዊድን ህግም ይሄንን አይነት ተቃውሞ ማሰማት ህገወጥ ስላልሆነና ወ ወይንሸት ታደሰ ያቀረበችውን ክስ ሚዛን የማይደፋ በመሆኑና መረጃ ለማቅረብ የማይቻል በመሆኑ የስዊድን ፖሊስ ክሱን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ወ ወይንሸት ወደ ስብሰባው በመጣች ግዜ እንቁላልና በገማ አሳ ተቃውሞ እንደገጠማትና ከመኪና ለመውጣት አለመቻሏ የሚታወስ ነው።
በዚህ በያዝነው ሳምንት አቶ ሬድዋን ሁሴን የህውሃት ሚኒስቴር በ አሜሪካ ያደረገው ክስ በቂ እንዳልሆነ ተረጋግጦ ክሱ ውድቅ መሆኑ የታወሳል፡፡
የህውሃት ባለስልጣኖች በየሄዱበት ውርደትን ከመከናነብ በቀር እንደ ኢትዮጵያ የራሳቸው ህግ አይነት የአውሮፓም ሆነ የአሜሪካን ህግ ሊረዳቸው አልቻሉም
ትግሉ ይቀጥላል የህውሃትም የዲሞክራሲ ክስረት ይጋለጣል
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ................ source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38251
Tuesday, 20 January 2015
ምርጫ ቦርድ፣ ማጭበርበሩን ያቁም!
(አስገደ ገ/ስላሴ ከመቀሌ)
.......... በሕወሓት አመራርና አጃቢዎች የተፈበረከው ምርጫ ቦርድ ባለፉት 20 አመታት ለ4 ጊዜ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ምርጫ አካሂዷል። ሁሉም ምርጫዎች ግን የዴሞክራሲ መስፈርትን የሚያሟሉ እንዳልነበሩ ዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ጭምር አረጋግጠዋል።
በ2007 ዓ.ም የምርጫ ውድድርም ሕወሓቶች፣ በዚሁ አመት ሃቀኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ጭራሹን ላለማሳተፍ፣ ለአመታት ያህል የቤት ስራ እየሰሩ ቆይተዋል፡፡ ለዚሁ አላማ ግቡን ለመምታት አስቀድመው እጅግ ብዙ ብቁ ምሁራንን እና ወጣት የፖለቲካ አመራሮችን “ለስልጣናችን አስጊ ናቸው” በማላት በሀሰት ወንጅለው አስረው በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ። ብዙ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላት ላይም ስጋት ፈጥረዋል፤ ከትምህርትና ከስራም አፈናቅለዋል። ፓርቲዎችን ለመበታተን ብዙ ሰርጎ-ገቦችን በማስረፅ አለመተማመን በመፍጠር፣ እንዲከፋፈሉ ለማድረግ ብዙ ገንዘብ ረጭተዋል።
ተቃናቃኝ ፓርቲዎች፣ ሰርገው ከገቡ ባንዳዎች ውስጣቸውን ለማጥራት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም ለማሰናከል፤ ምርጫ ቦርዱ ከባንዳዎች ጋር በማበርና በመወገን ሃቀኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ስራቸውን እንዳይሰሩ በጭቅጭቅ እየጠመዳቸው ይገኛል።
ለዚሁ ለማስረጃነት የሕወሓት መንግስት የህዝብ ድጋፍ ያላቸው ተቀናቃኝ ፓርቲዎች፤ ህዝብ በስብሰባና በሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡን እንዳያነቁ ከመከልከል አልፎም ብዙ አባላት ተጨፍጭፈው ደማቸው በጎዳና ፈሷል። በአገር ውስጥ ያለውን ሁለ-ገብ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ፀሃፊዎች፣ አምደኞችና ከያኒያን ታስረዋል ተሰደዋል።
ይሄ ሁሉ አልበቃም ብሎ፣ በዚሁ በምርጫ ዋዜማ አሸንፈው በፓርላማ ከፍተኛ ወንበር ያገኛሉ ያሏቸውን አንድነት እና መኢአድን ከምርጫ ጨዋታው ለማስወጣት፣ ብሎም ለመሰረዝ የተለያዩ ደባዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡ ፓርቲዎቹ፣ ምንም ስህተት ሳይኖርባቸው ትዕዛዙን ለመፈፀምና ምክንያታቸውን ለማስጨረስ ተደጋጋሚ ጉባኤ አድርገዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ ጉባኤያቸውን እንዲታዘብ ጠርተውት፣ ሳይመጣ ቀርቶ ፓርቲዎችን ለማባረር ተዘጋጅተዋል ። ይህን ሁሉ ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ገጠር ከተማ ሳይለይ የምርጫ ቦርድን ሴራ ተረድቶት እየተመለከተው ይገኛል። ለውጥ ፈላጊ ነውና።
በሌላ በኩል፣ ምርጫ ቦርድ ህወሓቶች ባዋቀሯቸውና ምንም ተከታይ በሌላቸው፤ ለወደፊትም የህወሓት ተስፈኞች ከመሆን ውጭ ለህዝብና ሀገር ምንም ፋይዳ የሌላቸው ባንዳዎችን ወደፊት በማምጣት ገንዘብ ያገኛል። በሌላ በኩል ግን ጠንካራ ፓርቲዎችን ለማፍረስ ወጥመድ እየፈጠረ ይሰጣል። ምርጫ ቦርድም ሆነ ሕወሓት መረዳት ያለባቸው እነዚህ ፓርቲዎች ከምርጫ ጨዋታ ውጭ ከሆኑ፣ የሕወሓቶች ውድቀት የተቃናቃኝ ፓርቲዎች ድል መሆኑ የማይቀር እንደሆነ መረዳት አለባቸው።
እነዚህ ከምርጫ ጨዋታ ውጭ እንዲወጡ የሚፈለጉ ፓርቲዎች ህወሓት አስቀድሞ የወሰነው ስለሆነ ተደጋጋሚ ጉባኤ ማድረግ አቁመው ህወሓት ከሰራቸው ጥገኛ አጃቢዎቹ (ብቻው ማንጨብጨብ አለበት) የዚህ ኣፈና ውጤት ዳግም ህዝብ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄድ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደርገዋል፤ ለዚህ ተጠያቂ የሚሆኑት ህወሓትና ምርጫ ቦርድ ይሆናሉ።
ለሕወሓት መሪዎች የምለግሳላቸው ምክር ቢኖር፣ የዘንድሮውን ምርጫ የዓለም-አቀፉን ህብረተሰብ ለማታለልና ለተራ የፖለቲካ ፍጆታ ብለው በሸፍጥ ጊዜያቸው ከማባከን እንዲቆጠቡ ነው፡፡ ሕወሓት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም፣ ነፃነት ፍትህና መልካም አስተዳደር ሲል ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞችን መፍታት ይኖርበታል፡፡ ሁሉም በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፓርቲዎች፣ ነፍጥ አንስተው በረሃ እስከ ገቡ ሃይሎች ድረስ የሰላም መድረክ ከፍቶ የሰላም ድርድር ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በዚህች አገር ሰላም ሰፍኖ ሁሉም ዜጎች በመቻቻል፣ በመፈቃቀር ስለሀገር ጥቅም ሀሳባቸውን በነፃነት አንሸራሽረው በህዝብ የድምፅና ዳኝነት ትመራ ዘንድ ምህዳሩን ቢያሰፉት የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ራሱ ሕወሓት ጭምር እጅጉን ይጠቀማል። ይህ ካልሆነ ግን ይህች ሀገርና ህዝቦቿ፣ ለከፋ ችግር መጋለጣቸው አይቀሬ ነው። አሁንም መፍትሄው በሕወሓት መሪዎችና አጃቢዎቹ እጅ ነው።
ሕወሓት ምርጫ ቦርድን መሳሪያ አድርጎ፣ በተቃናቃኝ ፓርቲዎች ላይ እያካሄደ ያለውን ሴራ ህዝባችንና አለምም ከወዲሁ ጠንቅቆ አውቆታል።
እግዚአብሔር ለሕወሓት መሪዎች ልብ ይስጥልን። (ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት).................source./http://www.goolgule.com/enough-with-the-election-board/
ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?
የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ሥጋቱን ይፋ ሊያደርግ ነው!
ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡
ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዘገባው ከዚህ በፊት ከወጡት ዘገባዎች ለየት ባለ መልኩ በፕሬስ ሚዲያው ላይ የተሰማሩትን ክፍሎች በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡ በተለምዶው በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና በብዙ መልኩ የሚነገር ሲሆን በዚህ ዘገባ ግን ኢህአዴግ በአሳታሚነት፣ በአከፋፋይነት፣ በአታሚነት፣ በሻጭነት (አዟሪነት)፣ ወዘተ የተሰማሩትን እንዴት ስልታዊ በሆነ መልኩ እንደሚያዳክም፣ እንደሚያፍን፣ እንደሚያሰቃይና ባጠቃላይ ከሜዳው እንደሚያስወግድ የሚያስረዳ እንደሚሆን ጎልጉል ካገኘው መረጃ ለመገመት ተችሏል፡፡
በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በማያያዝ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ዘገባ በተለይ የኢህአዴግን ቋት የሚሞሉ ለጋሽ አገራት፣ ዓለምአቀፍ የፍትሕ አካላት፣ የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣ ወዘተ ከወዲሁ ግንዛቤ ይዘው ኢህአዴግ አደርገዋለሁ ለሚለው “ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ” ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተሳትፎ እንዴት ውጤት አልባ እንደሆነ የሚያስረዳና ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ምርጫ ባልተጠበቀና ለመቀበል በሚያስቸግር መልኩ የአውሮጳ ኅብረት “በጀት የለም” በሚል ምርጫውን አልታዘብምም ብሏል፡፡ በይፋ የተሰጠው ምክንያት ይህ ቢሆንም ጉዳዩ የበጀት ሳይሆን “ኢህአዴግ ከኢህአዴግ ጋር የሚያደርገውን የ99.6 በመቶ የምርጫ ውጤት መታዘብ በራሱ ያስታዝባል” በሚል ነው ኅብረቱ ምርጫ መታዘቡን በቅድሚያ ትዝብት የተወው በማለት የተሳለቁ መኖራቸው ተሰምቷል፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በበኩሉ “ባትታዘቡ ምን ገደደኝ” በማለት ኅብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ አለመፈለጉን በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ትዝብት አልፎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ስለ ሚዲያ ነጻነት በሚያትተው አዲስ ዘገባና በኅብረቱ ውሳኔ ዙሪያ ኢህአዴግ “ዓለምአቀፋዊ ሽልማት ባገኙ የዘርፉ ባለሙያዎቹ” ተጠቅሞ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ባለ “ነጻነት” የሚዲያ ሥራ እንደሚሠሩ በነዚሁ “ሚዲያዎች” ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
የአውሮጳ ኅብረትን “ምርጫ አልታዘብም” የማለት ውሳኔን በተመለከተ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ለጎልጉል እንደተናገሩት ኅብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከበጀት እጥረት ሳይሆን እየከረረና እየመረረ የመጣውን የኢህአዴግን አምባገነንነት፣ በቀደሙት “ምርጫዎች” የተከሰተውን ዓይንአውጣ ቅጥፈት እንዲሁም የኢህአዴግን የሞራል ዝቅጠት በማገናዘብና ከተሞክሮ በመነሳት የግንቦቱን ምርጫ አስቀድሞ በማጣጣል ዋጋ እንደማይሰጠው ከመናገር አኳያ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህንን አስደንጋጭ የአውሮጳ ኅብረት ማዕቀብ ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ ድርጅት በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ከምርጫው በፊት አስቀድሞ ማውጣቱ ታስቦና ታቅዶ የተደረገ ብቻ ሳይሆን የአውሮጳ ኅብረትን እነማን ይከተሉታል የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡
በግንቦት 2007 አካሂደዋለሁ ለሚለው ምርጫ ኢህአዴግ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የውጭ ምንዛሬ ኮሮጆውን እንዲሞሉለት ከአውሮጳ ኅብረት በተጨማሪ ሌሎች አገራትን በተናጠል መለመኑ ይታወቃል፡፡
..............source.-www.goolgule.com
Monday, 19 January 2015
በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ አልዳነም!”
“በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣
ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተናገረ፡፡
ዮሐን ፔርሶን ኦጋዴን በረሃ
አንድ ዓመት ከሁለት ወር (14 ወራት) ከሥራ ባልደረባው ዮሐን ፔርሶን ጋር ኢህአዴግ አስሮት የነበረው ጋዜጠኛ ሺብዬ ለጎልጉል የአውሮጳ ዘጋቢ ይህንን የተናገረው በዖጋዴን ክልል የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም መሰራጨቱን ተከትሎ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡
“በአካል ሰላም አለኝ፤ አእምሮዬ ግን አልዳነም፤ ሁሌም እረበሻለሁ፤ በዓይኔ ያየኋቸው፣ በጆሮዬ የሰማኋቸውና በበቂ ምስክሮች ያረጋገጥኳቸው ሁኔታዎች ዕረፍት ይነሱኛል” ሲል አስተያየቱን የጀመረው ሺብዬ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግፍ ከሙያው አስገዳጅነት በመነሣት ከተባባሪዎቹ ጋር በመሆን ለዓለም እንደሚያሳውቅ ግልጽ አድርጓል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ከፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ተገኘ” በሚል ዘወትር እሁድ በሚተላለፈው የፖሊስ ክፍለ ጊዜ የተላለፈውን ዘጋቢ ፊልም (ድርሰት) የኢህአዴግን ዓመታዊ ቋት የምትሞላውን አሜሪካ በእስረኞች አያያዝ የገሃነም ተምሳሌት አድርጎ ያቀረበ ነው፡፡ ኢህአዴግ በልማት ስም የሚያገኘውንና ለባለሥልጣኖቹ የግል ሃብት ማካበቻ እንዲሁም በየጎሬው ለተፈጠሩ እስር ቤቶች ግንባታ የሚደጉሙትን አገራት በሰብዓዊ መብት አያያዝ ከዜሮ በታች አድርጎ ያብጠለጠለ ነበር፡፡ ከተለያዩ ድረገጾችና የዩትዩብ ምስሎች በተለያዩ እስርቤት ያሉትን በማነጋገር ተገጣጥሞ የቀረበው “ድርሰት” (ዘጋቢ ፊልም) ተከትሎ ይሁን አይሁን በግልጽ ባይታወቅም የኢህአዴግ የልብ ወዳጅ ኖርዌይ እነ ሺብዬ ያዘጋጁትን ዘጋቢ ፊልም ይፋ አድርጋለች፡፡
Nrk2 በተሰኘው የኖርዌይ መንግሥታዊ ቴሌቪዥን ማስተባበል በማይቻልበት ደረጃ በዖጋዴን የተፈጸመውን ርኅራኄ የሌለውን ዘግናኝ ሰቆቃ ለመመልከት ተችሏል፡፡ (በተለይ በአውሮጳ የሚኖሩ ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይችላሉ)
አብዱላሂ ሁሴን
የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪና የሚዲያ ክፍል ኃላፊ የነበረው አቶ አብዱላሂ ሁሴን ከሱማሌ ክልል ይዞት ወደ አውሮጳ ባመጣው በራሱ በኢህአዴግ ባለሙያዎች የተቀዱ ማስረጃዎች፣ ሰለባዎችና የክልሉ (ምክትል) ፕሬዚዳንት በግልጽ ሰቆቃና ግፍን ሲያውጁ በሚሰማበት፤ ወታደሮች ሲገድሉ፤ በቢሮ ግምገማ ላይ ተቀምጠው ስለፈጸሙት የግፍ ጀብዱ ሲተርኩና የፈጸሙት ግፍ አልቃም ተብሎ ሲገመገሙ እንደወረደ በሚያሳየው በዚህ ዘጋቢ ፊልም የእነ ሺብዬ መከራ በውል ቀርቧል፡፡ (ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይቻላል) በተለይም ፎቶ አንሺው ዮሐን ፔርሶን የክንዱ አጥንት በጥይት ተሰብሮ፣ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ ቀብረው ስቃዩን ሲያዳምጡ የሚያሳየው ምስል እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ ኢህአዴግ በእስረኞች አያያዝ “ጻድቀ ጻድቃን” ነኝ ባለ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኖርዌይ ቴሌቪዥን ያሰራጨው ዘጋቢ ፊልም የኢህአዴግን አውሬነት ያሳየ ለመሆኑ አብዛኞች አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡
የኢህአዴግ የልብ ወዳጅና የልማት አጋር ኖርዌይ እንዲህ ዓይነት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን ሊነካካ በሚችል ጉዳይ ጣልቃ ስትገባ ይህ በመጀመሪነት የሚጠቀስ ነው፡፡ እንግዲህ ይህንን ተከትሎ ነበር ጋዜጠኛ ሺብዬ አስተያየት የሰጠው፡፡ እርሱ እንደሚለው ሙያዊ ኃላፊነቱ በዚህ በዖጋዴን የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ እንዲጋልጥ አነሳስቶታል፡፡ ለወትሮው ወደ ዖጋዴን አንድም ሚዲያ እና የሲቪክ ተቋማት ድርሽ እንዳይሉ በሩን ጠርቅሞ የዘጋው ኢህአዴግ ባላሰበውና ባልጠበቀው መንገድ እነ ጋዜጠኛ ሺብዬ ይህንኑ ለመዘገብ ክልሉን ዘልቀው ሊገቡ ችለው ነበር፡፡
ማርቲን ሺብዬ እና ዮሐን ፔርሶን በኦጋዴን በረሃ
“ያየነውን ለዓለም ማሳየት፣ የኢህአዴግን ፕሮፓጋንዳ ማጋለጥ ዓላማችን ነው” የሚለው ሺብዬ በፖሊስ ፕሮግራም ቀረበ ስለተባለው የኢህአዴግ “ድርሰት” የሰጠው ምላሽ (ኢህአዴግ ይህንን ያህል ከሚለፋ) ማዕከላዊን እና ቃሊቲን ለጋዜጠኞች፣ ለቀይ መስቀልና ለዓለምአቀፍ ተቋማት ክፍት በማድረግ ምስክር ማግኘት ብቻ ይበቃዋል ሲል ፕሮፓጋንዳውን አጣጥሎታል፡፡ በቃሊቲ እስረኞች እንደሚሞቱ፣ በቂ የሚባል መጸዳጃ እንኳን እንደሌለ የተናገረው ሺብዬ አሁን ያለሁበት ቦታ የፈለኩትን ማድረግ የምችልበት ቢሆንም እዚያ ያሉትን ንጹሃን መዘንጋት ግን አይቻለኝም፤ ዘወትር እረበሻለሁ” በማለት ተናግሯል፡፡ በማያያዝም ይህንኑ ኢህአዴግን የሚያጋልጥ በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሐፍ በሚቀጥለው ወር ለገበያ እንደሚበቃ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ለሚማቅቁ ወገኖች መልካም ቀን እንዲመጣ ምኞቱን ገልጾዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘጋቢ ፊልሙ ይፋ በሆነ ማግስት ዓለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ኮሚሽን በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ወሬራ እና በመመሪያ ሰጪዎቹ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት በጦር ወንጀለኝነት ለመክሰስ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩ ታውቋል፡፡
ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች በእስር በነበሩበት ወቅት አቶ መለስ “የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” በማለት ለፈጠሩት ፓርላማ ሲፈላሰፉና በህግ የበላይነት እንደሚያምኑ እያስጨበጨቡ ሲናገሩ ቢቆዩም የልመና ኮሮጃቸውን የሚሞሉት የምዕራባውያን ዜጎችን አስረው መቀጠል እንደማይችሉ ሲረዱ “በዕርቅ” መፍታታቸው መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
በሌላ በኩል ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዖጋዴን ዙሪያው ገባ ታጥሮ ሰሚና ተመልካች እንዳይኖር ተደርጎ የከፋ ወንጀል ሲካሄድ እንደነበር የስዊድን ጋዜጠኞች ዜና ሳይሰማ ያገባናል ለሚሉ ወገኖች ሁሉ የማሳሰቢያ ዜና መስራቱ ይታወሳል፡፡ በተለይም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቀጥታ ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም፡፡ ከመግለጫው የተወሰደው ቃል እንዲህ ይነበባል፡-
“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቀበሌ መኖር የማይችሉ ዘላኖች (አርብቶ አደሮች) ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ሰሞኑን የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ”
“… ኦጋዴን በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተድበስብሶ ቢከርምም ዛሬ በሶማሊያ የተከሰተውን አስፈሪ ርሃብ ተከትሎ ይፋ መሆን ጀምሯል። ድርጅታችን በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ ክልል፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈፀሙትን ጭፍጨፋዎች በመቃወም እንዳደረገው ሁሉ በኦጋዴን የተፈፀመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ነው። የኦጋዴን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመሆኑ ይህ መግለጫ የሚደርሳችሁ አካላት በሙሉ ድርጊቱን በመቃወም አግባብ ያለው ተፅዕኖ በማድረግ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ ትግላችሁን እንድትቀጥሉ አጥብቀን እናሳስባለን” ሲል ጥሪውን አስተላልፎ ነበር። (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
በዖጋዴን የደረሰውን በተመለከተ እንዲሁም የሁለቱን ጋዜጠኞች በተመለከተ እስካሁን የዘገብናቸውን ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
ኢትዮጵያ፡ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የማሰቃየት ድርጊት ይፈጸማል፤ ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።
በሚዲያ መረሳት ያስፈራል፤ “ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”
“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!! ኢህአዴግ ለመክሰስ ሲፈልግ ፊልም እንደሚደርስ ተረጋገጠ
.......source.-http://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2015/01/johan-persson.jpg
Saturday, 17 January 2015
በሰሜን አሜሪካ ከአንድነት ድጋፍ ማህበር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ጉዳዩ፡ ፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡
እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ ባያምንበትም ሕግ ለማክበርና የሠላማዊ ትግሉን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ስለሚረዳ በሌለ አቅሙ በ4 ቀን ውስጥ በአስቸኳይና በታላቁ በገና በዓል ሣምንት የጉባዔ አባላትን ከክ/ሃገር ጭምር ጉባዔ ጠርቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፋ በ4ቀን ጉባዔ እንዲጠራ ካዘዘ በኋላ በጉባዔው ተገኝቶ ምርጫውን ታዝቦ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጋብዞ ሣይገኝ ቀርቷል፡፡ ይህ ዓይነት የምርጫ ቦርድ ሕገ-ወጥነት በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ምርጫ ቦርድ አሁንም እጅግ በጣም በሚያሳፍርና ይሉኝታ በሌለው አካሄድ አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በድጋሜ ጉባዔ እንዲጠሩ ሕገ-ወጥ ትዐዛዝ ለማስተላለፍ ችሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ውስጥ ጉዳይ የመፈትፈት: ውሣኔ የመቀልበስ እንዲሁም የፓርቲዎችን አመራር የማፅደቅ ወይም ያለማጵደቅ መብት ጨርሶ ሊኖረው አይገባም፡፡ ምከንያቱም እንደዚህ ዓይነት ጣልቃ ገብነት ካለ የፓርቲዎች የበላይ አካል የሚሆነው የአባሎቻቸው ጠቅላላ ጉባዔ ትርጉም አልባ ይሆናልና፡፡
አንድነት ፓርቲ በምጫ ቦርድ በድጋሜ የተላለፈውን ጉባዔ የመጥራት ትዕዛዝ እንደማይቀበለው መግለፁን እኛም የሰሜን አሜረካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር ሙሉ በሙሉ እንደምንደግፍ እናረናገግጣለን፡፡ ምርጫ ቦርድ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ለአገዛዙ ወገናዊነት በማረጋገጥ በአስተዳደሩ ኃላፊዎች በመታዘዝ በአንድነት ፓርቲና በሌሎች ተቃዋሚ አጋር ፓርቲዎች የሚያደርገውን ሕገ-ወጥነት አስተዳደራዊ ክፋ ሰራ እንቃወማለን! አንቀበለውም:: አገዛዙ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ከፈለገ ህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎችን በህገ-ወጥነት ሣይሆን በስርዓት :በአግባቡ የጨዋታ ሜዳውን ክፍት ማድረግ አለበት፡፡ የምርጫ ቦርድ የተደጋጋሚ ጉባዔ ጥሩ ትዕዛዝ ህገወጥነት ነው፡፡ ተቀባይነት የለውም አገዛዙ እንደዚህ ዓይነት እጅግ የዘቀጠ ፀያፍ ስራ ውስጥ ተነክሮ ያለው መጪውን ብሔራዊ ምርጫ ያለተቀናቃኝ ብቻዉን ተወዳድሮ ለማሸነፍ ካለው ጭፍን ፍላጐት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሆኖም ግን ይህ አካሄዱ ሃገሪቱን ወደ ባሰ ምስቅልቅል ይወስዳታል እንጅ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡
በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ማለትም መኢአድ: ሰማያዊ: መድረክና ሌሎችም ፓርቲዎች ተቀራርበው ትግሉን በጋራ እንዲመሩት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ፓርቲዎቹ አገዛዙን በመቃወም ለሚያደርጓቸው ማንኛውም የሠላማዊ እንቅስቃሴዎች ከጐናቸዉ እንደምንቆም በዚህ እጋጣሚ ማሣወቅ እንወዳለን፡፡ አንድነት ፓርቲ በሚያደርጋቸው የትብብር ጥሪዎችና የአመራር ስልቶች በተናጠልም ወይም ከሌሎች አጋር ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርጋቸው ትግሎች ሙሉ በሙሉ የማቴሪያልና የሞራል ድጋፍ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብም የአገዛዙን ተንኮል በመረዳት ከአንድነትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጐን በመሰለፍ የነፃነት ትግሉን እንዲያፋጥን ጥሪ አናቀርባለን፡፡
-......... source,-http://satenaw.com/amharic/archives/3694
Friday, 16 January 2015
ኢ/ር ይልቃልና ሌሎች ሁለት የፓርቲ አመራሮች ምስክርነታቸውን ሰጡ
ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና ሌሎች ሁለት የፓርቲ አመራሮች ምስክርነታቸውን ሰጡ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ስለሺ ፈይሳ እና የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው የተከላካይ ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡
ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ በነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት ሲበትን ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሳይ ዘርፉ በፌደራል አቃቤ ህግ በቀረበበት ክስ ተከላካይ ምስክር ሆነው የቀረቡት የፓርቲ አመራሮቹ፣ አቶ ሲሳይ ባለፈው ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም የአቃቤ ህግ ሁለት ምስክሮች ቀርበው በተከሳሽ ላይ ምስክርነት በመስጠታቸውና በዕለቱ ዳኛው በበራሪ ወረቀቱ ላይ የተጠቀሰውን ‹‹የኢህአዴግ መንግስት ያፍናል፣ ያጭበረብራል፣ ይገድላል…›› የሚለውን በመጥቀስ ድርጊቱ ወንጀል ስለሆነ ተከሳሹ መከላከል አለበት ማለቱን ተከትሎ የመከላከያ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ተከሳሹ አቶ ሲሳይ ዘርፉ ‹‹…‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ› ለመላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ….ተብሎ የተጻፈበት በራሪ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ሲያከፋፍል እጅ ከፈንጅ በመያዙ በፈጸመው የሐሰት ወሬን በማውራት ህዝቡን ማነሳሳት ወንጀል…›› በሚል ነው ክስ የቀረበበት፡፡
በመሆኑም የተከሳሽ ተከላካይ ምስክሮቹ ተከሳሹ ሲያሰራጨው የነበረውን ወረቀት ያዘጋጁት የትብብሩ አባል ፓርቲዎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ተከሳሹ እንደማነኛውም አባል የፓርቲዎቹን መልዕክት ለህዝብ ከማድረስ ባለፈ በግሉ የራሱን መልዕክት አለማስተላለፉን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ በበራሪ ወረቀቱ ላይ የሰፈረውን መልዕክት በተመለከተም፣ ‹‹የኢህአዴግ መንግስት ያፍናል፣ ያጭበረብራል፣ ይገድላል…›› የሚለው አገላላጽ ትክክል መሆኑን የተለያዩ ሪፖርቶችን በማጣቀስ አስረድተዋል፡፡
ምስክሮቹ የኢህአዴግ መንግስት ‹‹ያፍናል፣ ያጭበረብራል፣ ይገድላል…›› የሚለው እውነት ስለመሆኑ በምርጫ 97 ወቅት 193 ዜጎች መገደላቸውን መንግስት ራሱ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሲዮን ማረጋገጡን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚያም በኋላ በቅርብ ጊዜ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ግድያ እንዲሁም በባህር ዳር ከተማ በተመሳሳይ ሰልፍ የወጡ ዜጎችን ግድያ አንስተው አስረድተዋል፡፡
‹‹ያጭበረብራል›› የሚለውን በተመለከተም በ97 ምርጫ ወቅት የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን ያወጣውን ሪፖርት በማስረጃነት አንስተዋል፡፡ ‹‹ያፍናል›› የሚለውን በተመለከተም መንግስት በተለያዩ ወቅቶች የመብት ጥያቄ ያነሱ የዴሞክራሲ ኃይሎች ላይ እየተወሰደ ያለውን እስር አውስተዋል፡፡ በተለይ ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ መሪዎችን፣ ጦማርያንን እንዲሁም በሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ምክንያት የታሰሩ አካላትን አጣቅሰው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአጠቃላይ በበራሪ ወረቀቱ ላይ የሰፈረው መልዕክት የሀሰት ወሬ እና ስም ማጥፋት ሳይሆን ተጨባጭ እውነታ መሆኑን በምስክርነታቸው ቃል አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ እስካሁን የነበረውን የአቃቤ ህግ እና የተከሳሽ ምስክሮችን ቃል አገናዝቦ ብይን ለመስጠት ለጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የተመስገን ደሳለኝ ወንድም በ8 ፖሊሶች ተደበደበ
የተመስገን ደሳለኝ ወንድም በ8 ፖሊሶች ተደበደበ * ጠ/ፍ/ቤት የተመስገንን ይግባኝ ውድቅ ኣድርጎ የ3 ዓመት ፍርዱን ኣጸና
...(ዘሐበሻ) ጋዜጠኛ ተመስገን ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ የ3 ዓመት እስሩ እንዲፀናበት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ከዚህ ፍርድ ቀደም ብሎ ወንድሞ ታሪኩ ደሳለኝ በ8 ፖሊሶች ክፉኛ ተደበደበ።
ታሪኩ ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ጉዳዩን እንዲህ ገልጾታል:-
ክልከላና ድብደባ በዝዋይ እሰር ቤት
ለስምንት አንድን ሰው በደም እስኪታጠብ ድረስ በርግጫ፣ በጥፊና በሰደፍ መደብደብ፣ በእጁ ላይ የሚገኝውን ብርና መፃሀፍ መንጠቅ፣ ስልኩን መስበር…. ይህ ድርጊት በሌሊት አንድ ሰው ላይ በሌቦች የተፈፀመ ሳይሆን ትላንት ከረፋዱ በ 5 ሰዓት ላይ በዝዋይ እስር ቤት ግቢ ውስጥ በኔ ላይ የተፈፀመ ነው፤
ነገሩ እነዲህ ነው የሆነው፣ እንደልማዴ ዝዋይ የደረስኩት በማለዳ ነው፡፡ የያዝኩትን ስንቅ አስፈትሼ እንደጨረስኩ የሬዲዬ መገናኛ የያዘ መቶ አለቃ እንደሆነ የሚገልፅ ማዕረግ ያለው ወታደር እየገላመጠኝ “ለምን መጣህ?” አለኝ፤ “እዚህ የታሰረ ወንድም አለኝ እሱን ለመጠየቅ ነው” ስል መለስኩ፡፡ ቀጥ ብለህ ወጣ ተከተለ “አንተ ወንድምህን መጠየቅ አትችለም” ሲለኝ “ምክኒያቱ ይነገረኝ” ብዬ ብናገር ከጉዳይም አልቆጠረኝም “እሺ እ…ኔ ባልገባ እንኳን ያመጣሁት ምግብን አድርሱልኝ” ብል ስሚ አጣሁ፡፡ አንገቴን ደፍቼ ልወጣ ስል መቶ አለቃው በሬዲዬ እያወራ አንድቆም በእጁ ምልክት ሲሰጠኝ ልገባ ነው ብዬ ደሰ አለኝ፡፡ መቶ አለቃው በፍጥነት ወደኔ በመምጣት ያዙት አለ፡፡ በዙሬያዬ ወደ ስምንት የሚጠጉ ወታደሮች ከበቡኝ፡፡ የመቶ አለቃው “የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ነህ?” አለኝ፡፡ የተመስገን ወንድም መሆኔን በአንገቴም በአፌም “አዎ ነኝ” ከማለቴ ጥፊ ጆሮዬ ላይ ጮኽ፡፡ ከዛም አንደኛው በከስክስ ጫማ ሌላኛው በሰደፍ ተቀባበሉኝ፡፡ ደምቼ መሬት እስክወድቅ ድረስ ደበደቡኝ….ደበደቡኝ፤ ወደኩኝ፡፡ ከነደሜ አነሱኝ የያዝኩትን ብርና መጽሐፍ ነጠቁኝ ያመጣሁትን ምግብ መሬት ላይ ደፉተው እየገፈታተሩ ከግቢው አስወጡኝ፡፡ እስር ቤቱ ፊት ለፊት አቧራው ላይ ተቀመጥኩኝ፡፡ ተሜን በዓይን ርቀት ያህል ብቀርበውም መጠየቅ ባለመቻሌ አለቀስኩኝ፤ ደሜን አፍስሼ ወንድሜን ሳላይ ተመልሻለሁ … ተሜ ለኔ አንተን አለማየት የማይቻል ሽክም ነው፡፡ ይሄንንስ እነዴት ልንገርህ?!
የታሪኩን ድብደባ ናፍቆት እንደሚከተለው ተርካዋለች:-
በሰላም እንዳሳደርከኝ በሰላም አውለኝ” ማለት ትልቅ ነገር ነው!
ታሪኩ ደስአለኝ የጋዜጠኛ ተመስገን ታናሽ ወንድም ነው። ተመስገን ከታሰረ በኅላ ታሪኩ ሥራ በዝቶበታል። ከዲስ አበባ ዝዋይ በሳምንት 4 ግዜ እየተመላለሰ ለወንድሙ ሥንቅ ማቀበል።
ሮብ ዕለት ለወንድሙ ሥንቅ ይዞ በጠዋት ዝዋይ የደረሰው ታሪኩ፣ የወንድሙን ደህነት አይቶ ለደካማ (በዕድሜ)እናቱ ለመግለፅ እንጂ፣ ሌላ ችግር ይፈጠራል ብሎ አላሰበም።
ነገሩ እንዲህ ነው፦ ታሪኩ ዝዋይ እሥር ቤት ወንድሙን ለማየት ይገባል። እዚያም፣ “ተመስገንን ጥሩልኝ ” ሲል ፖሊሶችን ይጠይቃል። በዚህ ግዜ የመቶ ዓለቃ ማዕረግ ያለው ወታደር (ፖሊስ) ተመስገንን መጠየቅ እንደማይችል ይነግረዋል።
ታሪኩም “ምን ተፈጠረ ወንድሜን እንዳልጠይቀው የተከለከልኩት ?” በማለት ለፖሊሱ ጥያቄ ያቀር…ባል።
ፖሊሱም በማመናጨቅ “ውጣ” ይለዋል። ነገሩ ያላማረው ታሪኩ ለወንድሙ ያመጣውን ስንቅ እንደያዘ ወደ በሩ ያመራል። ነገር ግን” ውጣ” ያለው ፖሊስ በድጋሚ ታሪኩን እንዲቆም ያዘዋል።
ታሪኩም ወንድሜን ሊያገናኘኝ ነው ብሎ በደስታ ይቆማል። ፖሊሱ በመገናኛ እያወራ ” የተመስገን ወንድም ነህ አይደል?.”ይለዋል።” አዎ’ ብሎ ሳይጨርስ 8ፖሊሶች ታሪኩን ይከቡታል። ለወንድሙ ያመጣውን ምግብ ከደፉ በኅላ የዱላ ውርጅብኝ ያዘንቡበታል። ለ8። ደም በደም እስኪሆን። በድብደባ ከጎዱት በኅላ ወደ አዲስ አበባ መመለሻ የያዘውን ገንዘብ ከኪሱ (700 ብር) ይቀሙትና የእጅ ሥልኩን በመስበር ከግቢ ያስወጡታል።
ታሪኩም በዱላ የተጎዳውን ሰውነቱንና የሚፈሰውን ደም እየጠራረገ መታወቂያውን እስይዞ ገንዘብ ለትራንፖርት ተበድሮ ወደ አዲሥ አበባ ይመለሳል።…ታሪኩ ደስአለኝ በትላንትናው ዕለት በተክለኅይማኖት ሆስፒታል ህክምና ያደረገ ሲሆን፣ ጀርባው ላይ በጠመንጃ ሰደፍ በመመታቱ የአጥንት ስፔሻሊስት እንዲያየው እንደታዘዘለት ለማወቅ ችያለሁ።
ታዲያ የአባት ዕዳ ለልጅ ይተርፋል ይህ አይደል?…
ፍትህ! ፍትህ !
source,- http://www.zehabesha.com/
Thursday, 15 January 2015
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ሂደት በማወሳሰብ
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጪው ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ተፅእኖ እያደረብን ነው አሉ፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ሂደት በማወሳሰብ መጪው ምርጫ ፍትሀዊና ሚዛናዊ እንዳይሆን ጥርጣሬ ውስጥ ይከታል ሲሉ ይገልፃሉ፡፡
በፓርላማ መቀመጫ ያገኘ ብቸኛ አባል ያለው አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ በተደጋጋሚ የመወዳደሪያ ምልክቱ ውድቅ እንደተደረገበት መግለፁ ይታወሳል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ተሳታፊ እንዳይሆኑ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ሀሳባ ሲሰጥ እንዳለው የመወዳደሪያ ምልክት ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ሂደት ህጎች አለማሟላት ነው፡፡ የፓርቲው ፕሬዝዳንት በጠቅላላ ጉባኤ መታጨት ወይም መመረጥ ያለበት ሲሆን ነገር ግን እነሱ በጥቂት ሰዎች ብቻ ነው ፕሬዝዳንት ያጩት ሲሉ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቶ ወንድሙ ጎላ መናገራቸውን ቪ ኦ ኤ አስነብቧል፡፡
በምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፈው ሰማያዊ ፓርቲም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከምርጫ ቦርዱ ጋር በጋራ ለመስራት ቢሞከርም አልተሳካም ማለቱን የዜና ምንጩ አስነብቧል፡፡
ዝርዝሩን ይመልከቱ…
ኢትዮጵያ ውስጥ በህግ ማዕቀፍ ራሱን ችሎ የሚሰራ ነጻ ተቋምን ለማግኘት በየትኛውም የመንግስት አስተዳደር አልታደልንም፡፡ ስርዓቶቹን የመሩና ሚመሩ ባለግዜዎች የፈጠሯቸውን ተቋማት በአንድ የስልክ ጥሪ ሲያሽከረክሩ ቆይተዋል፡፡ምርጫ ቦርድም በአዋጅ ቢቋቋምም የስርዓቱ ሎሌ ከመሆን አልዘለለም፡፡ይህ ተቋም እንደ አንድ ገለልተኛ አካል ‹‹ቦርድ ››እየተባለ እንዲጠራ ከመደረጉ ውጪ ለገዢው ቡድን ዘብ በመቆም ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር አድልዎ ሲፈጽምና ኮሮጆ ሲገለብጥ እዚህ ደርሷል፡፡ሁልግዜም የአቅም /የገንዘብና የማቴሪያል/ችግር እንጂ ሌላ ጉድለት ሲያልፍም እንደማይነካው የሚናገረው ምርጫ ‹ቦርድ› አሁን የስንግ ተይዟል፡፡
ምርጫ ‹‹ቦርድን››አጣብቂኝ ውስጥ የመሰገው አንድነት ፓርቲ ነው፡፡የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ጠቅላላ ጉባኤ የሚደረገው በብሄራዊ ምክር ቤቱ ጥሪ ሲደረግ አልያም የፓርቲው ኦዲትና ኢንስፔክሽን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ሲወስን መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ባሳለፍነው እሁድ የተወሰኑ ግለሰቦች ባገኙት የገንዘብ፣ የማቴሪያልና የምርጫ ‹ቦርድ›ድጋፍ ጠቅላላ ጉባኤ በአንድነት ስም በማድረግ በነጋው ይህንኑ ለምርጫ ‹ቦርድ›ማሳወቃቸውን የምርጫ ‹ቦርድ›ታዛቢም በስብሰባው መገኘቱን ሰምተናል፡፡
አንድነት በህገ ደንቡ ስለጠቅላላ ጉባኤ አጠራር በማስፈር ይህንኑ ለምርጫ ‹ቦርድ›አሳውቋል፡፡ምርጫ ‹ቦርድ›ም የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚመዝነው ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በመነሳት እንጂ በራሱ መንገድ አልያም በእነ በረከት ቀጭን የስልክ መልእክት መሰረት አይደለም፡፡በሆቴል ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ ትዕግስቱን መረጥን ካሉ ሰዎች መካከል ከሶስት የማይበልጡ ሰዎች የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እንደነበሩ ከለጠፉት ፎቶ ግራፍ በቅርበት የሚያውቃቸው ሰው ሊረዳ ይችላል፡፡ሌሎቹ ምንም ያህል ቁጥር ቢኖራቸው ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግና መሪ መምረጥ አይችሉም፡፡
በፓርቲ ስም ስብሰባ ለማድረግ የአዲስ አበባ መስተዳድር ከምርጫ ቦርድ የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ይጠይቃል፡፡ምርጫ ‹ቦርድ›ለእነዚህ ሰዎች በአንድነት ስም እንዲሰበሰቡ ፈቃድ የሰጣቸው ምን አግኝቶባቸው ይሆን ?
በፓርቲው ውስጥ መርህ ተጥሷል ፣በህገ ወጥ መንገድ ሰዎች ሀላፊነት ወስደዋል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ጉዳያቸውን ለኦዲትና ኢንስፔክሽን በማቅረብ ወይም ብሄራዊ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ፊርማ በማሰባሰብ ኮረም እንዲያስሞሉ ምርጫ ‹ቦርድ›መምከር ሲገባው በስብሰባው ወቅት ታዛቢ መላኩ አመራሮቹን በወንጀል ሊያስጠይቃቸው ይገባ ነበር፡፡
ምርጫ ‹ቦርድ›ባለመኖሩ ግን እነትዕግስቱ ከስብሰባው መልስ ኢቴቪ ላይ ቀርበው ዲስኩር እንዲያሰሙ ነገሮች ተመቻቹላቸው፡፡
Wednesday, 14 January 2015
በዞን 9 ጦማርያንና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበው ክስ በድጋሜ ‹‹ተሻሻለ››
.በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር.........................
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም ለ15ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተሰየመው ቀደም ብሎ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲሻሻል ባዘዘው መሰረት የፌደራል አቃቤ ህግ ክሱን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ያላሻሻላቸው ነጥቦች ስለነበሩ እነዚህኑ ነጥቦች በድጋሜ አሻሽሎ እንዲቀርብ ባዘዘው መሰረት የተሻሻለውን ክስ ለመስማት ነበር፡፡
በመሆኑም የፌደራል አቃቤ ህግ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ ይዞ ቀርቧል፡፡ ክሱ ‹‹ሌሎች ብዙ ‹ኬዞች› ስላሉ›› በሚል ምክንያት በችሎቱ ላይ በንባብ እንዲሰማ አልተደረገም፡፡ ተሻሻለ የተባለው ክስ ለተከሳሾችና ለጠበቆች እንዲደርስ የተደረገውም እዚያው ችሎት ውስጥ ነው፡፡
ክሱ በንባብ ባለመሰማቱና ጠበቆቹና ዳኞቹም ስላላነበቡት በሚል ተሻሻለ በተባለው ክስ ላይ ምንም አስተያየት አልቀረበም፡፡ በመሆኑም ክሱ መሻሻል አለመሻሻሉን ለመመርመርና ብይን ለመስጠት ለጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
የጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ጠበቃ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን እንዳሉት በቀጣዩ ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተሻሽሎ ካልሆነ ነጥቦቹን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደርጋል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በእኛ በኩል ከዚህ በኋላ የማሻሻያ ሀሳብ አቅርበን ጊዜ አንፈጅም፤ ከሚቀጥለው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ መደበኛ ክርክራችንን መቀጠል ነው የምንፈልገው›› ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በዛሬው የችሎት ውሎ ላይ በጣም ብዙ እስረኛ (ተከሳሽ) ችሎቱ ውስጥ በመገኘቱ ምክንያት ከፍተኛ የቦታ ጥበት ማጋጠሙ ተስተውሏል፡፡ በአጠቃላይ እስከ 70 የሚደርሱ እስረኞች በችሎቱ ተገኝተዋል፡፡ ስለሆነም ችሎቱን መታደም የቻሉት ጥቂት ጋዜጠኞችና ዲፕሎማቶች ብቻ ሆነዋል፡፡ የተከሳሽ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች ችሎቱን መታደም አልቻሉም፡፡
Tuesday, 13 January 2015
ነፍሰጡር መሆኗ እየታወቀ ደብዳቢዎቹ ሆዷን በመርገጥ ደብድብዋታል
የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት
ወይዘሪት ወይንሸት፣ ንፋስ ስልክ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች ከረፋዱ 5፡30 ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባት ለፍኖተ-ነፃነት የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወይዘሪት ወይንሸት፣ ነፍሰጡር መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን ደብዳቢዎቹም ሆዷን በመርገጥ ድብደባውን ሲፈፅሙባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደብዳቢዎቹ ድብደባውን ፈፅመው የተሰወሩ ሲሆን ወይዘሪት ወይንሸት፣ በአሁኑ ሰዓት ራሷን ስታ ሆስፒታል መግባቷን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወይንሸት፣ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ድምፅ የአስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆና በመመረጥ በምርጫው ላይ ጉልህ ሚና በመጫወት ድርሻዋን መወጣቷ ይታወሳል፡፡ በእለቱ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአንድነት ስም የሚነግዱትን ግለሰቦች በማውገዝ አስተያየቷን መሰንዘሯን ተከትሎ ድብደባው ሊፈፀምባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወይዘሪት ወይንሸት፣ በፓርቲው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያላት ወጣት ከመሆኗም በተጨማሪ የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ሀላፊ በመሆን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ በአንድነት አባላት ላይ ድብደባ ሲደርስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ባለፈው እሁድ በአቶ መሳይ ትኩ፣ ላይ ድብደባ መፈፀሙ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ ዜና አንድነት ፓርቲ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረው አቶ መሳይ ትኩ፣ ከጉባኤው ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ በሚያቀናበት ወቅት፤ ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ በሚገኝ የኮሚኒቲ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ገልጿል፡፡
አቶ መሳይ ትኩ፣ ባለፈው ሳምንት “አንድነትን” ከገዢው ፓርቲ ጋር በመመሳጠር ለማፍረስ ሲሰሩ የነበሩት ግለሰቦችን ሴራ በማጋለጡ የተነሳ፤ በእነዚሁ ግለሰቦች ጠቋሚነት እና ግብረ-አበርነት በዛሬው እለት በከባድ ሁኔታ እንዲደበደብ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከግብረ-አበሮቹ መሃል ዳንኤል ሙላት የተባለው (ቅድስተ ማርያም አካባቢ ነዋሪ የሆነው) ግለሰብ ክትትል ሲያደርግበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ (ምንጭ: ፍኖተ-ነፃነት ፌስቡክ ገጽ)
Monday, 12 January 2015
"እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በማን እና እንዴት???"
የኢትዮጲያ የኑሮ ሁኔታዋ እና የህዝቧ መከራ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ለችግር እና ለመከራ የተጋለጠች የደም አኬልዳማ ምድር ከሆነች ሰነባብታለች ።ገሚሱ ለስደት የተሳካለት ብቻ የስደቱ መድረሻ ጋር ሲደርስ ግማሹ በየበርሃው የአሞራ ሲሳይ ይሆናል ።የተማረ የተናገረ መንግስት ለመናድ ህዝብ ለማሸበር እየተባለ ያለ ፍርድ በእስር እየተቀጡ መላ ቅጧ የህዝቧ ታሪኳ ትውፊቷ ሁሉ በወያኔ መንግስት ገደል ገብቷል ።
ታሪክ አልባ ሀገር ከ2000 አመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ያለ ታሪክ በወያኔ መንግስት ድምጥማጧ ጠፍቷል ዛሬ ስንት የሀገራችን ክፍል የስራ እና የዕድገት በር የሚሆነውን የቀይ ባህር ወደብን አሳልፎ ሰጥቶ የባህር በር እያለን እንደሌለን ሆነናል ።
በ 11/1/2015 ከጠዋቱ እንደ ኢትዮጲያ ሰሀት አቆጣጠር 3 ሰሀት ላይ በሀገራችን የመጀመሪያው ታሪካዊው እና የስልጣኔ ምንጭ የሆነውን በነሀሴ ወር በ1898 ስራ የጀመረው በንግስት እቴጌ ጣይቱ የተከፈተው ጣይቱን ሆቴል ወያኔ ለፓለቲካ ማራመጃ አድርጎ ታሪክን ከሀገር የማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል ።የአራዳው እሳት እና አደጋ ቢሮ እዛው ጉረቤት ሆነው እስኪወድም አላማው ታርጌት እስኪመታ በውስጡ የነበሩት ታሪካዊ ነገሮች በእሳት እስኪወድሙ እሳት አደጋ መኪና በአካባቢው አልደረሰም ።ታሪክን ማቃጠል ይቻል ይሆናል ታሪክን የሚመዘግብ የእፉኝት ልጆችን ግን ወያኔ በገዛ እጁ እየፈለፈለ ነወረ ።የሚበላውን ያጣ ህዝብ መሪውን ይበላል ።
ታድያ እውን ለመጀመርያው ዘመናዊ ሆቴል ተጠያቂ ማነው ትላላቹ? "አውቆ የተኛ ሲቀሰቅሱት አይሰማም አይደል ተረቱስ" ወያኔ ታሪክ ይጠይቀሃል።











የአርቲስት አስቴር በዳኔና ሳሞራ ፍጥጫ በደደቢት በረሃ
…አርቲስት አስቴር በዳኔ ከተቀመጠችበት ወደፊት ወጥታ ማይኩን ስትጨብጥ ፍርኃት ቢጤ እንደወረራት ከመጀመሪያው ያስታውቃል፡፡ ‹‹በጣም ነው የሚያስፈራው፤›› በማለት የጀመረችውን አስተያየቷን የያዘችውን ማስታወሻ እያነበበች አስተያየት መስጠት ቀጠለች፡፡
Aster Bedae
አርቲስት አስቴር በዳኔ
‹‹ይህንን ዕድል ተመቻችቶልን በቴሌቪዥን ስናየው የኖርነው ታሪክ ለማየት ስለቻለን እጅግ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ በፊት የነበረኝ ያልተጨበጠ አመለካከት በመረጃ የተደገፈ ሆኗል፤›› በማለት ሐሳቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹እውነትን መናገር እወዳለሁ፡፡ የሐሳብ ነፃነትም አለ፡፡ በእርግጥ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፤›› በማለት ታዳሚዎችን ፈገግ ያሰኘች ሲሆን፣ በሒደትም የፍርኃቷ መጠን እየቀነስ የመጣ ይመስላል፡፡
‹‹ዛሬ ባልናገረው የሚቆጨኝ የተከፈለው መስዋዕትነት እጅግ በጣም ከባድ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በጆሮ ስሰማው ደርግ ተደምስሶ ታጋይ እንዲህ ሆኖ ሲባል ከሁለቱም ወገን የተሰዉት በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ የሞቱት፣ እግራቸው የተቆረጠ፣ ዓይናቸው የጠፋ ስላሉ ለሁለቱም ‹ጠላት› የሚለው ቃል ተገቢ አይመስለኝም፡፡ የወንድማማቾች ደም በመፍሰሱ ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሄደን ስናይ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የጦርነትና የትግል ታሪክ ዘመኑ የፈጠረው ነው፡፡ በወቅቱ መንግሥታዊ ለውጥ ለማምጣት የትጥቅ ትግሉ አማራጭ አልነበረውም፡፡ አሁንስ?›› አርቲስት አስቴር ትንፋሿን ዋጥ በማድረግ ቀጠለች፡፡
‹‹የትግሉ ዋና ሐሳብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በአገሪቱ ለማምጣት ነው፡፡ የመንግሥትም ሆነ የሥርዓት ለውጥ በጦርነት ሳይሆን በዲሞክራሲ እንዲሆን ነበር ያ ሁሉ ከባድ መስዋዕትነት የተከፈለው፡፡ አሁን ላይ ሲታሰብ የሚመጣው ግንቦት ላይ 24 ዓመት የሚሆነው ሥልጣን ላይ ያለው አንድ ፓርቲ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ላይ ልባችሁ ምን ይላል? ያኔ ለሥልጣን ሳይሆን ለሕዝብ ስትታገሉ በጦርነት ሳይሆን በዲሞክራሲ ለውጥ እንዲደረግ ነበር፡፡ አይለደም?›› በማለት ጠየቀች፡፡
‹‹በእርግጥ የድሮን አስተሳሰብ መናፈቅ አዲስ አስተሳሰብ ለመቀበል ይከብዳል፡፡ አሁን ዝም ብዬ ሳስበው ራሱ ተቃዋሚ የሚለው ቃል ራሱ ጥሩ አይደለም፡፡ ተፎካካሪ ቢባል፡፡ አዲስ አስተሳሰብና ፍልስፍና ያለው ተተኪ መሪ ሊፈጠር አይችልም የሚል አቋም ነው ያላችሁ?›› በማለት ሐሳቧን ያልቋጨችው አርቲስት አስቴር፣ ሐሳቧ በብዙዎች ተጠብቆ የነበረ አይመስልም፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ›› የሚለው የመጨረሻውን ቃል እስክትናገር ከአጠገቧ የተቀመጡ ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት አንጋፋ ታጋዮች ጥያቄው እስኪያልቅ የተጨነቁ ይመስላል፡፡ እርስ በርስ አየት ተደራርገው የተለዋወጡት ፈገግታ ጥያቄውን የጠበቁት እንዳልሆነ ያሳብቃል፡፡ በእርግጥም በምርጫ ዋዜማ ሆነው ለጥያቄው ምን ተብሎ ምላሽ እንደሚሰጥ ሳያስጨንቃቸው አልቀረም፡፡
‹‹እውነት መናገር እውዳለሁ›› በሚል የጀመረችው ፍርኃት እየፈጠረባትም ቢመስል የመጨረሻ ማጠናቀቂያ ሐሳቧ እንዲህ ነበር የሚለው፡፡ ‹‹ምክንያቱም እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፡፡ ‘So, next time’ ምን ያህል አዲስ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተለውጦ እናያለን?›› የሚለው ፈራ ተባ እያለች የጨረሰችውን ጥያቄ ‹‹ውርድ ከራሴ›› ይመስል ድምጿ እየተቆራረጠ ‹‹አመሰግናለሁ›› ብላ፣ ‹‹እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን?›› ብላ ነበር ጥያቄዋን የቋጨችው፡፡
አቶ በረከት ስምኦን ሁለት እጆቻቸውን ወደፊት ወስደው እንደማፍተልተል ሲያደርጉ፣ ሌሎች ብዙዎቹ አንጋፋ አመራሮች በግርምት ጉንጫቸውን ደገፍ አድርገው ይዘው ቀታይተዋል፡፡
ተዛማጅ ፅሁፎች
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3510#sthash.5Z1F7k4x.dpuf
Sunday, 11 January 2015
.የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የውህደት ስምምነት ተፈራረሙ
.የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ ደርሰናል” ብለዋል። ድርጅቶቹ አያይዘውም ”አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድ አስፈላጊው መስዋዕትነት በመክፈል የትግል እድሜ እናሳጥር በሚል ለውህደት የሚያደርሰንን ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።” ብለዋል።

ከዚህ በሁዋላ በሚኖረው የሽግግር ሂደት ወቅትም በሁሉም የትግል ዘርፍ በጋራ መሥራት መጀመራቸውን ድርጀቶቹ ገልጸዋል። የውህደቱን ስምምነት የሶስቱ ድርጀቶች ተወካዮች፣ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ዜና መሆኑን ተናግረዋል። የውህደት ስምምነቱ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚወክል ነው ያሉት የአርበኞች ግንባር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አርበኛ መንግስቱ ወ/ስላሴ ”ትግላችን መስዋትነትን በሚጠይቅ ትግል ላይ የተመሰረተ መሆኑ ውህደቱን ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል” ብለዋል። ሶስቱም ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉን እንዲደግፍ በተለይም የመከላከያ ሰራዊት አባላት አዲሱን ውህድ ሃይል ተቀላቅለው ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገውን ትግል እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በወያኔ ወታደሮች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል። ይህ የውህደት መስመር ስምምነትም ይህን የተጀመረውን መራራ ትግል ወደ አንድ በማምጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ስራ ለመስራት የሚያስችል ይሆናል።
source,-http://sebhatamare.wordpress.com
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ፤
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ፤ እንዲሁም በሰማያዊ ፓርቲ አባል አቃቤ ህግ ምስክር አሰማ
በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሶስት ዓመት እስር የተበየነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መውደቁን ቤተሰቦቹ ገለፁ፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት፤ ኮማንደር ቢኒያም ተብሎ በሚጠራው የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጠዋትና ማታ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ከመሆኑም በላይ በቀን ለአምስት ጊዜ ያህል ሌሊትን ጨምሮ በሰበብ አስባቡ ከክፍሉ እየተጠራ ይወሰዳል፡፡
ቤተሰቦቹ እንዳሉት፦ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በኮማንደር ቢኒያም እየተጠራ “እንገልሃለን፣ ከዚህ አንተ ሳይሆን ሬሳህ ነው የሚወጣው” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ ነው እየደረሰበት ያለው፡፡
በተመስገን ላይ በእስር ቤት ውስጥ ዛቻውና ማስፈራሪያው እየጠነከረ የመጣውም በቅርቡ ለንባብ ባበቃው “የኢትዮጵያ መንግስት ገመና” በሚለው መጣጥፉ ምክንያት እንደሆነ ቤተሰቦቹ መናገራቸውን የፍኖተ-ነጻነት ዘገባ ያመለክታል።
ተመስገን ከተያዘው ሳምንት ጀምሮም ምግብ እንዳይገባለት፣ በቤተሰብ፣ በወዳጅ -ዘመድ እና በስራ በባልደረቦቹ እንዳይጎበኝ ከመደረጉም በላይ ለህይወቱ አስጊ በሆነ ሁኔታ ቀዝቃዛ መሬት ላይ እንዲተኛ እየተደረገ ይገኛል።
ጋዜጠኛ ተመስገን፣ ፍትህ ጋዜጣ ላይ በፃፋቸው ፅሁፎች የተነሳ የሶስት ዓመት እስር ተበይኖበት ከወርሃ ጥቅምት ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በሌላ በኩል ‹‹መንግስትን የሚቃወም ወረቀት ሲበትን ይዘነዋል› የሚል ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ በሚገኙት በሰማያዊ ፓርቲ አባል ላይ አቃቤ ህግ ምስክር አሰምቷል። የአቃቤ ህግ ምስክር የተሰማባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ፤ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ ለነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት በመበተናቸው ለእስር የተዳረጉት አቶ ሲሳይ ዘርፉ ናቸው።
‹‹…‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ› ለመላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ….ተብሎ የተጻፈበት በራሪ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ሲያከፋፍል እጅ ከፈንጅ በመያዙ ፤ በፈጸመው የሐሰት ወሬን በማውራት ህዝቡን ማነሳሳት ወንጀል ተከሷል…›› የሚል ክስ፤ በፌዴራል አቃቤ ህግ በተመሰረተባቸው አቶ ሲሳይ ላይ ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት- ሁለት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ጉዳዩን ባስቻለው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት የአቃቤ ህግ የመጀመሪያ ምስክር ሆነው የቀረበው ኮንስታብል ያለው መንግስቴ፣ ‹‹ተከሳሹን ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ላይ መንግስትን የሚቃወም በራሪ ወረቀት ሲበትን አይተነዋል፤ በዚህም ወረቀት ሲበትን ያገኛችሁትን ሰው ያዙ ተብልን ስለነበር ተከሳሹን በቁጥጥር ስር አውለነዋል›› ብሏል፡፡
መስካሪው በወቅቱ ተከሳሹን ሲይዙት የፖሊስ ደንብ ልብስ እንዳልለበሱና በሲቪል እንደነበሩ ጠቅሶ፣ ‹‹የሚበተነው ወረቀት በዘጠኙ ፓርቲዎች መዘጋጀቱን እንጂ ይዘቱን አላስታውሰውም፤ የህግ አስከባሪ እንደመሆኔ ግን ተከሳሹን በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጌያለሁ›› ሲል መስክሯል።
ሁለተኛ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆኖ የቀረበው ኮንስታብል ማርክሽ ሹመሌ በበኩሉ፣ ‹‹ሲቪል ነበር የለበስኩት፤ ተከሳሹ ወረቀት ሰጠኝ፡፡ ሳየው መንግስትን የሚቃወም ወረቀት ነው፡፡ ወረቀቱን ለጓደኛዬ አሳየሁት፡፡ ከዚያም በቁጥጥር ስር አዋልነው› ሲል የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል።
አቃቤ ህግም ሁለቱ ምስክሮች የሰጡትን ምስክርነት ከተያዘው በራሪ ወረቀት ጋር አገናዝቦ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲሰጥለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ተከሳሽ አቶ ሲሳይ በበኩላቸው ‹‹መንግስትን መቃወም ህገ-መንግስታዊ መብቴ ነው፡፡ ስለሆነም ወንጀል አልሰራሁም›› ሲል ተከራክሯል፡፡
ይሁንና ዳኛው በበራሪ ወረቀቱ ላይ የተጠቀሰውን ‹‹የኢህአዴግ መንግስት ያፍናል፣ ያጭበረብራል፣ ይገድላል…›› የሚሉትን ሀረጎች በማውሳት ድርጊቱ ወንጀል ስለሆነ ተከሳሹ መከላከል አለበት ሲሉ ውሳኔ አስተላልፈዋል። በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲው አባል አቶ ሲሳይ ዘርፉ የሰነድ ማስረጃዎቻቸውን ጨምሮ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ለጥር 7/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡source,-http://dagmawitewodros.com/category/
Friday, 9 January 2015
ህዝብን ያነቃቃሉ የተባሉ ቲሸርት እንዳይለበስ ተከለከለ
ለጥምቀት ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለበስ ተከለከለ • ህዝብን ያነቃቃሉ የተባሉ መንፈሳዊ ጥቅሶች መጠቀም አይቻልም ተብሏል
የክርስትና እምነት ተከታይ ወጣቶች ጥምቀት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርቶችን እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ጀምሮ እስከ ጃንሜዳ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች በተለያዩ ማህበራት ስር ለጥምቀት በዓል ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮቹ ከዝግጅታቸው መካከል ቲሸርት አሳትሞ መልበስ አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ወጣቶቹ ለጥምቀት በዓል የተለያዩ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታተሙበት ሰማያዊ ቲሸርት ማሳተማቸውም ተከትሎም ደህንነትና ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች በየ ቤታቸው እየዞሩ ‹‹ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም፡፡›› እያሉ እያስጠነቀቁ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በነገው ዕለትም ካድሬዎች ከፈረንሳይ ለጋሲዮን እስከ ጃን ሜዳ አካባቢ የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ስብሰባ መጥራታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ህዝብን ያነቃቃሉ ከሚል ስጋት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በቲሸርት ላይም ሆነ ሌላ ለጥምቀት በዓል ላይ በማድመቂያነት በሚውል ነገር ላይ ማተም እንደማይቻል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ወጣቶቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለጥምቀት በዓል ማድመቂያነት እንዳይውሉ ከተከለከሉት ጥቅሶች መካከል ‹‹የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚያብሄር ትዘረጋለች፣ የአባቶቻችን ርስት አንሰጥም….›› የመሳሰሉት ይገኙበታል ተብሏል፡፡ እነዚህን መንፈሳዊ ጥቅሶች መጠቀም እንደሚያስቀጣም ደህንነትና ፖሊሶች የበዓሉ አዘጋጅ ወጣቶችን አስጠንቅቀዋል፡፡
ወጣቶቹ ሰማያዊ ቲሸርትም ሆነ የተከለከሉትን መንፈሳዊ ጥቅሶችን በሐይማኖታዊ ፋይዳቸው ምክንያት ባለፉት የጥምቀት በዓላት ላይ ሲጠቀሙባቸው እንደቆዩ፣ አሁን ደህንነቶች እነሱ ካላሰቡት ፖለቲካ ጋር ማገናኘታቸው እንዳሳዘናቸውና ከሐይማኖታዊ ፋይዳቸው ውጭ ምንም አይነት ትርጉም እንዲኖራቸው ታስበው የተሰሩ ባለመሆናቸው በበዓሉ ላይ እንደሚጠቀሙባቸው ገልጸዋል፡፡
..source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archive
Thursday, 8 January 2015
መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት
... ሁሉን ማድረግ አልችልም ሁሉን ማድረግ አለመቻሌ ግን የምችለዉን ከማድረግ ወደ ኋላ አያስቀረኝም”
..... በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
የኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ ምላሻቸዉን ለማዉጣት የእነሱ መደወልም ሆነ ትዕዛዝ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ የዝግጅት ክፍላችን አንድ ጽሑፍ የቀረበበት አካል ምላሹን በዚያዉ በተፃፈበት የህትመት ዉጤት ላይ ማስነበብ እንደሚችል በህግ የተደነገገ መሆኑን ከማወቁም በላይ የትኛዉንም አይነት ሀሳብ ለማስተናገድ ክፍት ነበርና ምላሻቸዉን በጋዜጣችን ላይ ታተመ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አልተገቱም፤ በወቅቱ የገዢዉ ፓርቲን ሀሳብ በማቀንቀን ይታወቁ የነበሩት እንደ ዳጉ ኢትዮጵያና ሰነድ ያሉ ጋዜጦች ሀሳቦቼን በሃሳብ መምታት ባለመቻላቸዉ ይሁን ባለመፈለጋቸዉ ተራ ዘለፋዎችን ያወርዱብኝ ጀመር፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የገዢዉ ፓርቲ ደህንነቶች ስልክ በመደወል፣ በዝግጅት ክፍላችን አድራሻ በስሜ ደብዳቤ በመላክና በአካልም በማግኘት ጭምር መንግስትን የሚተቹ ፅሑፎችን እንዳልፅፍ ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፡፡ “ማስፈራራት የሚቻለዉ የሚፈራ ሲኖር ነዉ” እንዲሉ ሙከራቸዉ ዋጋ አልነበረዉም፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያ ፅሑፌን ለህትመት ከማብቃቴ በፊት ልከፍለዉ ስለምችለዉ መስዋዕትነት በሚገባ አስቤበታለሁ፡፡ የሀገሬን ጉዳይ በንቃት የምከታተል ዜጋ እንደመሆኔም ከገዢዉ ፓርቲ የተለየ ሀሳብ ያቀነቀኑ ሰዎች የደረሰባቸዉን በሚገባ አዉቃለሁ፡፡ በመሆኑም ከሁለት መጥፎ ምርጫዎች አንዱን ማለትም እነሱ የደረሰባቸዉን ግፍ እንዳይደርስብኝ የሀገሬን ጉዳይ በተመለከተ ፍዝ ተመልካች መሆንን ወይም በሙያዬ የምችለዉን አስተዋፅኦ አበርክቼ የሚመጣዉን መቀበል መምረጥ ነበረብኝ፡፡ ሁለተኛዉን የተሻለ መጥፎ ምርጫ ከመረጥኩ የሰነበትኩ በመሆኑም እየበረከቱ የመጡትን ማስፈራሪያዎች ከቁብ ሳልቆጥር የጋዜጠኝነት ስራዬን መቀጠል ቻልኩ፡፡ በዚሁ መሰረት ስራ ለመያዝ፣ የደረጃ እድገት ለማግኘትም ሆነ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከደህንነት ስጋት የፀዳ ኑሮ ለመኖር የኢህአዴግ አባል ካልሆነም ደጋፊ መሆን ከጊዜ ጊዜ ግድ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳዩ፣ ገዢዉ ፓርቲ እንዳጎናፀፈን የሚገልፅልን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በተጨባጭ አለመኖሩን የሚሞግቱ፣ የኢህአዴግን እንደሀገር የማሰብ ችሎታ ወይም ፍቃደኝነት አናሳ መሆን የሚተቹና ሌሎችም መንግስት ቀናነት ቢኖረዉ ኖሮ ሊታረምበት የሚያስችሉትን በርካታ ፅሑፎች አቀረብኩ፡፡ አንድ ቀን ጧት ግን አምባገነኑ መንግስታችን ከጀመርኩት ጉዞ ገታኝ፡፡ ሰኔ10/2003 በወቅቱ እሰራባት በነበረችዉ ተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ ላይ የቀድሞዉን ጠቅላይ ሚኒስትር በተመለከተ ፅሑፍ ለህዝብ ማቅረቤን ተከትሎ ሰኔ14/2003 ዓ.ም ለእስር ተዳረግሁ፡፡
ማዕከላዊና ቃሊቲ ምንና ምን ናቸዉ?
ዉድ አንባብያን፤ ፊዘኛዉ መንግስታችን በሽብርተኝነት እንደሚጠረጥረኝ ገልፆ በእጆቼ ካቴና በማጥለቅ በቁጥጥር ስር አዋለኝ ካዋለኝ ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለቁጥር የሚያታክቱ የመብት ጥሰቶችን እየፈፀመብኝ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል እጅግ በጣም ጥቂቶቹን እነሆ!
ከህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነዉ የሚባልለት ህገመንግስት በጥበቃ ስር ያሉ ሰዎች በጠበቆቻቸዉ የመጎብኘት መብት እንዳላቸዉ ቢገልፅም እኔና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ግን ይሄ መብታችን በማዕከላዊ አለቆች ተጥሷል፡፡ ጠበቃዬን ለማግኘት የተፈቀደልኝ ምርመራዉ ከተጠናቀቀና ቃል ከሰጠሁ በኋላ ወደቃሊቲ ለመዉረድ የአስርቀናት ዕድሜ ያህል ሲቀረኝ ነበር፡፡ በቤተሰብና በጓደኞቼ ለመጎብኘት የተፈቀደልኝም ሁለት ወር ከ3 ሳምንታት ክልከላ በኋላ ነበር፡፡ ከጠበቃዬ ጋር እንዳልገናኝ ተደርጎ የሚካሄደዉ ምርመራ የፃፍኳቸዉን ፅሑፎች ለምን እንደፃፍኩ፣ ከበስተኋላዬ ሆኖ የሚገፋኝ አካል ስለመኖር አለመኖሩና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ ቢሆንም አልፎ አልፎ ደግሞ መልኩን ይቀይራል፡፡ አንዳንድ ቀን መርማሪዎቹ በማስተምርበት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄዱ ስብሰባዎች ላይ ያቀረብኳቸዉን ሀሳቦች እያነሱ ከመንግስት የደህንነት ሀይሎች የሚያመልጥ ምንም ነገር እንደሌለ በመግለፅ ቢጤ ያሰሙኝ እንደነበር ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፡፡፡ እንዲህ አይነቱ ንግግራቸዉ አሰልቺዉን ምርመራ ዘና እልበት ዘንድ የሚረዳኝ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶኛል፡፡ በአደባባይ ስብሰባዎች ላይ የተናገርኩትንና ደህንነት ሊሰልለዉ የማያስፈልገዉን ግልፅ ነገር እንደ ትልቅ የደህንነቶች የስራ ዉጤት ተደርጎ ሲገለፅ ከመስማት በላይ ምን የሚያዝናና ነገር ይገኛል? የት/ቤት ርዕሰ መምህራኖች በሙሉ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ የተደረገበት ምክንያት መንግስት እንደሚለዉ የትምህርት ፖሊሲዉን ለማስፈፀም ሳይሆን የመምህራንንና የተማሪዎችን የፖለቲካ አቋም ለማወቅና ይህንኑ ሪፖርት ለማድረግ መሆኑን የማይረዳ መምህር ይኖራል? ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ ርዕሰ መምህራኖች ሰበብ እየተፈለገላቸዉ ከቦታቸዉ እንዲነሱ ሲደረግስ ስንታዘብ አልኖርንም? “ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” አለ ያገሬ ሰዉ! ሆዴ ባዶ እንዳይቀር ሁሉን መተንፈሴን ትቼ የጀመርኩትን የማዕከላዊ ምርመራ ጉዳይ ልቀጥል፡፡
የምርመራዉ ይዘት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መልኩን እየቀየረ መጣ፡፡ በሪፖርተርነት እሰራበት የነበረዉ የኢትዮጵያ ሪቪዉ ድረገፅ አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ የሽብር ተልዕኮ እንደሰጠኝ በሀሰት እንድናገርና ተከሳሽነቴ ቀርቶ ምስክር ሆኜ እንድፈታ ለማድረግ የተለያዩ ጫናዎቸው ይደርሱብኝ ጀመር፡፡ ለአምስት ደቂቃ ያህል ጧትና ማታ ወደመፀዳጃ ቤት ለመሄድ ከሚከፍቱልኝ በስተቀር ለአስራሶስት ቀናት ያህል ብቻዬን አንድ መጥፎ ሽታ ያለዉ ክፍል ዉስጥ ተዘግቶብኝ ከረምኩ፡፡ በዚህ ወቅት ጉዳዬን የያዘዉ ዐቃቤህግ ማዕከላዊ በመምጣት እያስጠራኝ ሀሳቤን የማልለዉጥ ከሆነ እድሜ ልክ ወይም ሞት እንደሚያስፈርድብኝ ይዝትብኝ ነበር፡፡ ሀሰን ሽፋ በበኩሉ በሀሳባቸዉ የማልስማማ ከሆነ የያዘኝን የወጣት ጀብደኝነት ማስተንፈስ ለነሱ ከባድ ስራ አለመሆኑን ነግሮኛል፡፡ በኔ በኩል ደግሞ ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ንፁህ መሆኔ እንጂ ኤልያስ ላይ በሀሰት መመስከሬ ሊያስፈታኝ እንደማይገባ ስለማምን ይህንኑ በተደጋጋሚ አስታዉቄ ተከሳሽ መሆንን መረጥኩ፡፡ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ የተሻለዉን መጥፎ እየመረጡ መኖር ዕጣፋንታችን ከሆነ ቆየ አይደል?
ማዕከላዊ እያለሁ ከተፈፀሙብኝ የመብት ረገጣዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ በአንድ ፖሊስ የተሰጠኝ ጥፊና ከግድግዳ ጋር ማጋጨት በተለይ ወንድ የፖለቲካ እስረኞች ከሚፈፀምባቸዉ ለዘላቂ የአካል ጉዳት የሚዳርግ ከባድ ድብደባ አንፃር ሳስተያየዉ የማዕከላዊ መርማሪዎች እንደሚሉት “ቁንጥጫ” ተብሎ ከመግለፅ የሚያልፍ ባለመሆኑ ብዙ ልልበት አልፈልግም፡፡ በወቅቱ የነበርነዉ ሴት እስረኞች ላይ ያን ያህል የከፋ አካላዊ ድብደባ አልተፈፀመም ማለት ግን የማዕከላዊ መርማሪዎች ለሴቶች ይሳሳሉ ማለት አይደለም፡፡ ለማሳያነት እስካሁን ድረስ ማዕከላዊ በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ የተነሳ በህመም የምትሰቃየዋን የፖለቲካ እስረኛ እማዋይሽ አለሙን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አይ ማዕከላዊ! ማዕከላዊ ዘና ብለዉ የሚራመዱ ኩሩ የኢትዮጵያ ልጆች በገቡ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ በቃሬዛና በሰዎች ድጋፍ በሸክም ሲያሳልፉና የድረሱልኝ ዋይታ ሲያቀርቡ የሰማሁበት አሰቃቂ ቦታ ነዉ፡፡ ምስላቸዉ ከአይኔ ላይ፣ ጩኸታቸዉ ከጆሮዬ ተጣብቆ የሚኖረዉ እነዚህ ወገኖቼን እያሰብኩ መናደድ መቆጨት የዕለት ተዕለት የኑሮዬ አካል ሆኗል፡፡
የማዕከላዊዉን የመብት ረገጣ እዚህጋ ገታ ላድርገዉና በተለይ የፖለቲካ እስረኞችን ሰብአዊ መብት ከመጨፍለቅ አንፃር አምሳያዉ ወደ ሆነዉ የቃሊቲ እስር ቤት ልለፍ፡፡ ጳጉሜ3/2003 ዓ.ም ቃሊቲ እንደገባሁ በኋላ ላይ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ እንደሆነች በተገነዘብኩት ሀላፊ አማካኝነት ጋዜጠኝነቴ ከታሰርኩ በኋላ የቀረ በመሆኑ ግቢዉ ዉስጥ በሚኖረኝ ቆይታ አርፌ መቀመጥ እንደሚኖርብኝ ተነገረኝ፡፡ አልጋ እስከሚለቀቅ ተብሎም እኔና በአንድ መዝገብ የተከሰስነዉ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ምንም እንኳን ሁለታችንም የሳይነስ በሽታ ያለብን ቢሆንም ሽንት ቤት አጠገብ መሬት ላይ ፍራሽ አንጥፈን እንድንተኛ ተደረገ፡፡ ዉድ አንባቢያን ስለቃሊቲ ስታስቡ ወደ አዕምሮአችሁ የሚመጡት ያማሩ ግንብ ቤቶችና የተዋቡ አልጋዎች ከሆኑ ኢቲቪ እንደሸወዳችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ የፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ ፕሪዝን ፌሎሽፕ የተባለ ድርጅት እንዳሰራቸዉ የሚናገሩት እነዚህ ያማሩ ግንብ ቤቶች ሁለት ክፍሎችና መፀዳጃ ቤት ብቻ ያሏቸዉ ሲሆኑ የተቀሩት በሴቶች ዞን ዉስጥ ያሉ ክፍሎች ከሁለት ያረጁ ግንብ ቤቶች በስተቀር በቆርቆሮ የተሰሩና እስረኞች በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖሩባቸዉ ናቸዉ፡፡ የቃሊቲ ምቾት አልባነት የሚሰማዉ አካልን ብቻ አይደለም፡፡ ቃሊቲ ከአካል በከፋ ሁኔታ ለነፍስና ለመንፈስ ይጎረብጣል፡፡ እንዴት ቢሉ እንዲህ እልዎታለሁ፡፡ የቃሊቲ የሴቶች ዞን ቤተመፃሕፍት ከጥቂት ወራት ጀምሮ በመፅሐፍቱ አይነትም ሆነ ቁጥር መሻሻልን ቢያሳይም እኔ ቃሊቲ ከገባሁ ጀምሮ እስከቅርብ ጊዜያት ድረስ ግን ከመኖር በማይቆጠር ደረጃ የሚገኝ ነበር፡፡ ይህንን ክፍተት ቤተሰብና ጓደኞቼ በሚያስገቡልኝ መፀሐፍት ለመሙላት ባስብም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሚመጡልኝ መፅሐፍት የቃሊቲን ሳንሱር እንደወደቁ ተገልፆ እኔጋ ሳይደርሱ ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ መፅሐፍት ዉስጥ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የሚሳትማቸዉ የታሪክ መፅሐፍት ሳይቀር ይገኙበታል፡፡ ቃሊቲ ለመንፈስም አይመችም ያልኳችሁ በዚህ ብቻ አይደለም፡፡ በራሴ ወጪ ኢንድራ ጋኒዲ ናሽናል ኦፕን ዩኒቨርስቲ በርቀት ፖለቲካል ሳይንስ ለማጥናት ከብዙ ዉጣዉረድ በኋላ ተፈቅዶልኝ የተበዘገብኩ ቢሆንም የመማሪያ ሞጁሎቹን ለማስገባት ግን የቃሊቲ አለቆች ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ከብዙ ደጅጥናት በኋላ ሞጁሎቹ ሲገቡ ደግሞ በትምህርቱ ዙሪያ ላነባቸዉ የሚገቡኝ አጋዥ መፅሐፍት ስለፖለቲካ የሚያወሩ በመሆናቸዉ በፍጹም ሊገቡ እንደማይችሉ የመፅሐፍት ገምጋሚዎቹ አረዱኝ፡፡ ይባስ ብሎ በዚያን ወቅት ከሌላዉ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ምንም አይነት መፅሐፍት እንዳይገቡልኝ በመደረጉ ለጠቅላላ ዕዉቀት ያህል ሞጁሎቹን ማንበቤን ብቀጥልም ትምህርቱ ግን በዚህና በሌሎች ምክንያት ለማቋረጥ ተገደድኩ፡፡
በቃሊቲ የኔ ብቻ ሳይሆን ከእኔ ጋር የተቀራረቡ ወይም ደግሞ ሰላምታ ያቀረቡልኝ ሰዎች ሳይቀር መብታቸዉ ተጥሷል፡፡ ከሁለት አመታት በላይ የሚሆነዉን ጊዜ በርካታ እስረኞች በነበሩበት ክፍል ያሳለፍኩ ቢሆንም እኔን እንደሌላዉ እስረኛ ለመቅረብ የሞከሩ በሙሉ ስሜትን የሚጎዳ ወከባ፣ዘለፋና ለየት ያሉ ፍተሻዎችን አስተናግደዋል፡፡
በህክምና ጉዳይ የነበሩብኝን ችግሮች በተመለከተ ቤተሰቦቼ ደጋግመዉ የገለፁት መሠረታዊ ችግር በመሆኑ በዚህ ፅሑፍ ነካ አድርጌዉ ብቻ አልፋለሁ፡፡ ጡቴ ዉስጥ በበቀለዉ እጢ ምክንያት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል በማደርግበት ወቅት በቀጠሮዬ ቀን ወደ ሆስፒታሉ ከምወሰድባቸዉ ይልቅ የማልወሰድባቸዉ ጊዜያት ይበዙ ነበር፡፡ የግራ ጡቴ ቀዶጥገና ከተደረገለት በኋላ በወቅቱ ክትትል ታደርግልኝ የነበረችዉ ዶክተር በሶስተኛ ቀን የቁስሉ ፕላስትር መቀየር እንዳለበትና በሳምንቱ ደግሞ ክሩ መዉጣት እንዳለበት ገለፀችልኝ፡፡ አብረዉኝ የሚሄዱት አጃቢ ፖሊሶች ከዶክተሬም ጋር ስነጋገር እዛዉ ነዉና የሚቆሙት እንዲህ አይነቱን ነገር ለማድረግ የሚችል ጤናጣቢያ ማረሚያቤቱ እንዳለዉ ተናገሩ፡፡ እኔም ቀጠሮ ቢሰጠኝ እንኳ በዚህ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደሆስፒታሉ ተመልሼ መሄድ አዳጋች መሆኑን ስለማዉቅ የተባሉት ነገሮች ቃሊቲ መፈፀማቸዉን አልጠላሁትም፡፡ በመሆኑም ለህክምና ክትትል የሶስት ወራት ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ ክሩ መዉጣት ባለበት ቀን ስለጉዳዩ ለጥበቃ ክፍሉ አስታወቅኩ፡፡ እነሱም አሁን ደቡብ ሱዳን ከሚገኝዉ ጦር ጋር አብራ ከተጓዘች አንዲት የህወሐት ታጋይ የነበረች ነርስ ጋር አገናኙኝ፡፡ እሷም እዛዉ ጨርሼ መምጣት እንደነበረብኝና እዚህ ክሩን ማዉጣት እንደማይችሉ ነገረችኝ፡፡ የምታሳየኝ ጥላቻ በሷ እጅ የህክምና አገልግሎት ከማግኘት ቢቀር የሚሻል መሆኑን የሚጠቁም በመሆኑ ብዙም ልከራከራት አልፈለኩም፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ሌሎች ሀላፊዎች ወደጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲወስዱኝ ብጠይቅም “ቀጠሮ የለሽም” በሚል ሰበብ ሳይወስዱብኝ ቀሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የቀኝ ጡቴም ተመሳሳይ እጢ ያለበት በመሆኑ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ቀዶጥገና አደርግ ዘንድ የላከኝ ቢሆንም (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በእድሳት ላይ በመሆኑ)እጅግ የከፋ ህመም ካልታመምኩ በቀር ቃሊቲ ሆኜ ቀዶጥገና ማድረጉን አልፈለኩም፡፡ በመሆኑም አልፎ አልፎ የሚሰማኝን ህመም በህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች በማቃለል የቃሊቲን አስቀያሚ ቀኖች በመግፋት ላይ እገኛለሁ፡፡
ሌላዉ የቃሊቲ ቆይታዬን በተመለከተ ልጠቅሰዉ የምፈልገዉ ጉዳይ ከመንግስት አካላትና ከተለጣፊዎቻቸዉ ጋር ካለፍላጎቴ እንድንገናኝ እየተደረገ የሚፈፀምብኝ የሰብአዊ መብት ረገጣ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ያህልአንዱን ብቻ ልጥቀስ፡፡ አምና መጋቢት ወር ዉስጥ አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መምጣታቸዉን የገለፁ ሌሎች አስር ሰዎች ከአመት በፊት ወደገባሁበትና ከሌሎች ከአራት ሰዎች ጋር ብቻ ወደምኖርበት ክፍል መጡ፡፡ እኔም ኮሚሽኑ በተለይም ደግሞ አምባሳደሩ የሰብአዊ መብት አከባበርን አስመልክቶ የሚሰጧቸዉ ከእዉነት የራቁ መግለጫዎች የሚያሳዝኑኝ በመሆኑ ለመነጋገር ፍቃደኛ አለመሆኔን በማስታወቅ ከክፍሉ ወጥቼ በሩ ላይ ቆምኩ፡፡ ከሰዎች አንዱ የምኖርበትን ክፍልና አልጋዎቻችንን ፎቶ ሲያነሳ ተመለከትኩ፡፡ ገረመኝ፤ መሬት አንጥፌ ስተኛ፣በተደራራቢ አልጋ የላኛዉ ክፍል ላይ ከጡት ህመም ጋር እየታገልኩ ስተኛና በተፋፈገ ክፍል ዉስጥ ስኖር ለምን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፎቶ አላነሳም? ማረሚያ ቤቱ በጥሩ ሁኔታ እስረኞቹን የያዘ መሆኑን ማሳያ ለማድረግ እንደተፈለገ ገመትኩ፡፡ እዉነታዉ ግን ይቺ ያለሁባት በቆርቆሮ የተሰራች ክፍልና ጠባቧ ግቢ አምና መስከረም ላይ በጠያቂዎች የመጎብኘት መብቴ መጣሱን ተከትሎ በጥድፊያ የተዘጋጀች ማግለያ ቦታ መሆኗ ነዉ፡፡ ክፍሉን ብቻ ፎቶ አንስተዉ መሄዳቸዉ ያላረካቸዉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰዎች በማግስቱ አራት ሆነዉ መጡ፡፡ ሁለቱ ወደግቢዉ ዉስጥ ሲገቡ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ በሩጋ ቆሙ፡፡ ግቢዉ ዉስጥ ከገቡት አንዱ ትላንት ለምን ላናግራቸዉ እንዳልፈለኩ ጠይቆኝ በድጋሚ ከነሱ ጋር መነጋገር ያልፈለኩበትን ምክንያት እያስረዳኋቸዉ እያለ የግቢዉ በር ክፍት ስለነበር ግቢዉ በርጋ ከቆሙት አንዱ ፎቶ ሊያነሳኝ ሲሞክር ለመመልከት ቻልኩ፡፡ ምስሌን አንስቶ ቢሆንና ስለኔ አንዳች አይነት ዉሽት ሲናገሩ ብሰማ ጉዳዩን በዝምታ እነደማላልፈዉ ነገርኩትና ወደቤት ዉስጥ ገብቼ በሩን ዘጋሁት፡፡
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ከክፍሉ ወጥቼ ኢህአዴግ ማሰሩ ሳይበቃዉ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር እንዳቋቋማቸዉ በሚናገረዉ ተለጣፊ ድርጅቶቹ ሳይቀር ሰብአዊ መብቴን ለምን እንደሚጥስ ከሀላፊዎቹ አንዷን በማስጠራት ጥያቄ አቀረብኩላት እሷም ሰዎቹ ካሜራ መያዛቸዉን እንደማታዉቅ ነገረችኝ፡፡ በ2005ዓ.ም ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግኑኝነት ክፍል እኔን ለማናገር እንደመጣ የገለፀልኝ ሰዉ ኮቱ ዉስጥ ደብቆ በያዘዉ ሪከርደር ድምፄን ለመቅረፅ ሲሞክር ደርሼበት ይህንን ማድረግ የሚችለዉ የግል ፕሬስም ተገኝቶ ንግግራችንን የሚቀርፅ ከሆነ ብቻ መሆኑን ነግሬዉ ነበር፡፡ ይሄንን ያልኩበት ምክንያት የግል ፕሬሱ ባልተገኘበት ለመንግስት ሚዲያዎች ብቻ አስተያየታቸዉን የሰጡ ግለሰቦች ሀሳባቸዉ ተቆርጦና ተቀጥሎ ለማለት ያልፈለጉት ይዘት ይዞ እንደሚቀርብ አዉቅ ስለነበር ነዉ፡፡ የተናገርኩትን ሙሉዉን ነገር ቀርፀዉ ሊያወጡልኝ የሚችሉ አካላት በሌሉበት ለሰዉዬዉ አስተያየቴን መስጠት ያለፈለኩትም ይኸዉ እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር፡፡ አስገራሚዉ ነገር ይቺ የኮሚሽኑ ሰዎች ካሜራ መያዛቸዉን እንደማይታወቅ የገለፀችልኝ ሀላፊ ያኔም የሰዉየዉን የድምፅ ሪከርደር መያዝ በተመለከተ ላቀረብኩላት ጥያቄ የሰጠችኝ ተመሳሳይ መልስ ነበር፡፡
የቃሊቲ ጉድ ማብቂያ ስለሌለዉ አንድ የመጨረሻ ጉዳይ ላንሳና የፅሁፌ መነሻ ወደሆነዉ የአመክሮ ጉዳይ አልፋለሁ፡፡ ዉድ አንባቢያን በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የትኞቹንም እስረኞች አያያዝ የተመለከቱ ህጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንም ሆኑ መመሪያዎችን በጣሰ ሁኔታ ከወላጆቼ በቀር ጠበቃን ጨምሮ በሌላ በማንም ሰዉ የመጎብኘት መብቴን ከተነጠቅኩ አመት ከኣራት ወራት አልፎኛል፡፡ አዛዉንት እናትና አባቴም ከእርጅና፣ ህመምና ድካም ጋር እየታገሉ የቃሊቲን ፈታኝ መንገድ መዉጣትና መዉረዳቸዉን ቀጥለዋል፡፡
ነገረ አመክሮ
ያለፈዉ አመት ነሐሴ ስምንት ቀን ከሰአት በኋላ ወደ ጠበቃ ክፍል ሃላፊዋ ቢሮ በአንዲት ፖሊስ ተጠርቼ ተወሰድኩ፡፡ እዚያም ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋናዉ መስሪያ ቤት የይቅርታና የአመክሮ ጉዳይ ክፍል እንደመጣና ኮማንደር አስቻላዉ እንደሚባል ከነገረኝ ሰዉ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ኮማንደሩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ያቀረበልኝ የመጀመሪያዉ ጥቃቄ “ይቅርታ ለምን አልጠየቅሽም? ይቅርታ በመጠየቅ ላይ ያለሽ ሀሳብስ አልተቀየረም ወይ?” የሚል ነበር፡፡ ይቅርታ ያልጠየኩት ስላላጠፋሁና የተፀፀትኩበት ጉዳይ ስለሌለ በመሆኑና አሁንም ምንም የተቀየረ አቋም እንደሌለኝ አስረዳሁተ፡፡ “ይሄ የፍርድቤት ጉዳይ ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ እስካለሽ ድረስ ወደዚያ መመለስ አይኖርብንም” አለኝ፡፡ እኔም አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት እንዳሻዉ የሚያሽከረክረዉ ፍርድቤት በንፁሃን ላይ የጥፋተኝነት ዉሳኔና ፍርድ ማስተላለፉን አሜን ብዬ ይቅርታ የምጠይቅበት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ ገለፅኩለት፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ያህል ስለጤንነቴና በጊቢዉ ዉስጥ ስለሚያጋጥሙኝ ችግሮች በተመለከተ ጥያዎችን ስያቀርብልኝ ቆየና ወደ መጣበት ሌላዉ ዋና ጉዳይ ተመለሰ፡፡
“ቅድም ይቅርታ የማልጠይቀዉ ስላልተፀፀትኩ ነዉ ብለሻል፡፡ አመክሮ እኮ የሚሰጠዉ ለተፀፀተ ሰዉ ነዉና እንዴት ልታደርጊ ነዉ?” በማለት ስለ በአመክሮ የመፈታት አካሄድ አንዳንድ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንቦችን ጭምር በመጥቀስ ሊያብራራልኝ ሞከረ፡፡ “ታዲያ እንዲህ ከሆነ በይቅርታና በአመክሮ መሀል ምንም አይነት መሰረታዊ ልዩነት የለም ማለት ነዋ?” ለሚለዉ ጥያቄ ቀጥታ መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም ይልቁኑ ሁሉም ታራሚ 2/3ኛዉን የእስር ቅጣቱን ለመፈፀም ሁለት ወራት ገደማ ሲቀሩት እንደታረመና እንደተፀፀተ የሚገልፅ ፎርም መሙላት ስለሚኖርበት እኔም ለመፈታት ከፈለኩ ይህንኑ ማድረግ እንደሚጠበቅብኝ አስረግጦ ነገረኝ፡፡ የፃፍኩት የማምንበትንና መቼም ልቆምለት የምችለዉ እዉነት መሆኑን፣ በዚህ የተነሳ አሸባሪ መባሌ ደግሞ የበለጠ ኢህአዴግን እንድታገለዉ የሚየደርገኝ እንጂ የሚያፀፅተኝ ባለመሆኑ እንዲህ አይነቱን ከማንነቴ ጋር የሚቃረን ፎርም እንደማልሞላ አስረግጬ ነገርኩት፡፡ ኮማንደሩም ላልታረመና ለልተፀፀተ ሰዉ አመክሮ መስጠት ለእነሱም እንደሚከብዳቸዉ ከገለጸልኝ በኋላ “እኛ ፎርሙን ብንሞላልሽስ?” የሚል አስገራሚ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔ “ታርሜያለሁ” እንዳልኩ ተደርጎ ምንም አይነት ነገር ቢደረግ ሀሰት መሆኑን ከማጋለጥ ወደኋላ እንደማልል አስታወቅኩት፡፡ በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሀሳቦች ላይ እየተሸከረከርን ጥቂት ጊዜ ከፈጀን በኋላ እንዳሰብበት አሳስቦኝ ተለያየን፡፡
ይህ ከሆነ ሀሁለት ወራት በኋላ የመፈቻዬ ቀን የነበረዉ ጥቅምት 14/2007 ማለፊን ተከትሎ “የአመክሮ ፎርሙን ለምን አትሞይም?” የሚል ጥያቄ ከተለያዩ ሀላፊዎች ይቀርብልኝ ጀመረ፡፡ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ ጥያቄዉ እየጨመረ መጣ፡፡ በተለይ በመጨረሻዎቹ የህዳር ወር ቀናት በአንዱ አራት ሆነዉ ክፍሌ ድረስ በመምጣት አነጋገሩኝ፡፡ ለኮማንደሩ የሰጠሁትን ምላሽ ሰጠኋቸዉ፡፡ የሃለፊዎቹ ሁኔታ ከሁለት አመት በፊት የሆነዉን አስታወሰኝ፡፡ ያኔም የይቅርታ ፎርም ለመሙላት ፍቃደኛ ሳልሆን በመቅረቴ እንዳሁኑ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ፎርሙን እሞላ ዘንድ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ በእንቢታዬ ስፀና ግን የተለያዩና አብዛኛዎቹም እስከዛሬ የዘለቁ የመብት ጥሰቶችን ይፈፅመብኝ ጀመር፡፡ ያሁኑስ እምቢታዬ ምን ያስከትል ይሆን? አላዉቅም፡፡ አንድ ነገር ግን አዉቃለሁ፡፡ መታረምና መፀፀት ያለብን ኢህአዴግ በሀገር ላይ የሚያደርሰዉን ጥፋት በመቃወማችን ምክንያት የታሰርን እኛ ሳንሆን አምባገነኑ መንግስት መሆኑን!
ዉድ አንባቢያን በመጨረሻ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት ኢትዮጰያን ለማየት እንዲያበቃን እየተመኘሁ፣ ለተግባራዊነቱም የምችለዉን ሁሉ እንደማደርግና እንደምከፍል ቃል እየገባሁ እሰናበታችኋለሁ፡፡ “ምን ልታደርጊ ትችያለሽ?” የምትሉኝ ካላችሁ መልሴ የሚሆነዉ ማን እንደተናገረዉ ባላስታዉስም “የፍቅር አብዮት” የተሰኘ መጸሀፍ ሳነብ ያገኘሁት አንድ አባባል ነዉ ፡፡
” ሁሉን ማድረግ አልችልም ሁሉን ማድረግ አለመቻሌ ግን የምችለዉን ከማድረግ ወደ ኋላ አያስቀረኝም”
...............ርዕዮት አለሙ
...............ከቃሊቲ እስር ቤት
................source.-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37857
Subscribe to:
Posts (Atom)