Netsanet Online Samuel adem
Freedom and Justice for oppressed people.
Monday, 12 January 2015
"እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በማን እና እንዴት???"
የኢትዮጲያ የኑሮ ሁኔታዋ እና የህዝቧ መከራ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ለችግር እና ለመከራ የተጋለጠች የደም አኬልዳማ ምድር ከሆነች ሰነባብታለች ።ገሚሱ ለስደት የተሳካለት ብቻ የስደቱ መድረሻ ጋር ሲደርስ ግማሹ በየበርሃው የአሞራ ሲሳይ ይሆናል ።የተማረ የተናገረ መንግስት ለመናድ ህዝብ ለማሸበር እየተባለ ያለ ፍርድ በእስር እየተቀጡ መላ ቅጧ የህዝቧ ታሪኳ ትውፊቷ ሁሉ በወያኔ መንግስት ገደል ገብቷል ። ታሪክ አልባ ሀገር ከ2000 አመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ያለ ታሪክ በወያኔ መንግስት ድምጥማጧ ጠፍቷል ዛሬ ስንት የሀገራችን ክፍል የስራ እና የዕድገት በር የሚሆነውን የቀይ ባህር ወደብን አሳልፎ ሰጥቶ የባህር በር እያለን እንደሌለን ሆነናል ። በ 11/1/2015 ከጠዋቱ እንደ ኢትዮጲያ ሰሀት አቆጣጠር 3 ሰሀት ላይ በሀገራችን የመጀመሪያው ታሪካዊው እና የስልጣኔ ምንጭ የሆነውን በነሀሴ ወር በ1898 ስራ የጀመረው በንግስት እቴጌ ጣይቱ የተከፈተው ጣይቱን ሆቴል ወያኔ ለፓለቲካ ማራመጃ አድርጎ ታሪክን ከሀገር የማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል ።የአራዳው እሳት እና አደጋ ቢሮ እዛው ጉረቤት ሆነው እስኪወድም አላማው ታርጌት እስኪመታ በውስጡ የነበሩት ታሪካዊ ነገሮች በእሳት እስኪወድሙ እሳት አደጋ መኪና በአካባቢው አልደረሰም ።ታሪክን ማቃጠል ይቻል ይሆናል ታሪክን የሚመዘግብ የእፉኝት ልጆችን ግን ወያኔ በገዛ እጁ እየፈለፈለ ነወረ ።የሚበላውን ያጣ ህዝብ መሪውን ይበላል ። ታድያ እውን ለመጀመርያው ዘመናዊ ሆቴል ተጠያቂ ማነው ትላላቹ? "አውቆ የተኛ ሲቀሰቅሱት አይሰማም አይደል ተረቱስ" ወያኔ ታሪክ ይጠይቀሃል።
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment