Wednesday, 31 December 2014
የ30 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ በደቡብ አፍሪካ በጎርፍ ተወስዶ ሕይወቱ አለፈ…
A 30-year-old Ethiopian man drowned in Rustenberg, South Africa ... Read More at...http://goo.gl/iJe1Sy |
የ30 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ በደቡብ አፍሪካ በጎርፍ ተወስዶ ሕይወቱ አለፈ…
ኢትዮጵያዊው በጎርፍ የተወሰደው በደቡብ አፍሪካዋ የሩስተንበርግ ከተማ ሲሆን አደጋው በደረሰበት ወቅት መኪናውን እያሽከረከረ በድልድይ ላይ ያልፍ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
መኪናዋ የምታልፍበት ድልድይ ዝቅ ያለ በመሆኑ በድልድዩ ስር የሚያልፈው ጎርፍ መኪናዋን እንደወሰዳትና በዚህም የኢትዮጵያዊው ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል፡፡
ዝርዝሩን ይመልከቱ…
source.-http://www.diretube.com/article_read.php?
እንግሊዛዊው በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኘው በሽብርተኝነት ተጠርጥሮ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተሰማ፡፡
በሽብርተኝነት ተጠርጥሮ በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኘው እንግሊዛዊው አሊ ኦዶረስ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተሰማ፡፡
ኢንዲፔንደንት የተሰኘው የዜና ምንጭ እንዳስነበበው እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው ይህ ግለሰብ በለንደን የደህንነት ባለሙያ ሲሆን በኢትዮጵያ ከተያዘ አንድ አመት ከስድስት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የሽብርተኝነት ውንጀላው የፈጠራ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀይ ኮሚሽን ገለፃ ተጠርጣሪው በእስር ቤት ቆይታው ከፍተኛ እንግልትና በደል እየደረሰበት ነው፡፡ በኤሌክትሪክ ማስያዝ እንዲሁም ድብደባ ደርሶበታል የሚል ቅሬታ ቀርቧል፡፡
ተጠርጣሪው በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ገና ልጅ እያለ ነበር ወደ እንግሊዝ የሄደው፡፡ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የሆነው አሊ MI5 ተብሎ በሚታወቀው በእንግሊዙ የደህንነት አገልግሎት እና ሜትሮፖሊታን ፖሊስ አገልግሎት ከአክራሪ ቡድን ጋር ግንኙነት አለው በሚል መወንጀሉን አይቀበለውም፡፡
ባለቤቱ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ ሚዛናዊ አይደለም ስትል ቅሬታዋን ታሰማለች፡፡ ፍርድ ቤቱ ህግን ያልተከተለ ውሳኔ ነው ያስተላለፈው ስትል መናገሯን ኢንዲፔንደንት አስነብቧል፡፡
‹‹ምናልባትም የቃቤ ህግ ምስክሮች በግዴታ ወይም በመታለል በባለቤቴ ላይ የተሳሳተ ምስክርነት ሳይሰጡ አይቀሩም›› ስትል ትናገራለች፡፡
የዜና ምንጩ እንደገለጸው ከእንግሊዝ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ መንገስት የደረሰው ደብዳቤ በግለሰቡ ላይ እየደረሰ ያለው ነገር ከአለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ህግ ውጪ ነው ይላል፡፡
የአሊ አዶረስ የህግ ባለሙያ እንደሚለው በ 2013 በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መረጃ እንዲያወጣ ድብደባ እና ኤሌክትሪክ ንዝረት ደርሶበታል፡፡
ተጨማሪ ዝርዝሩን ያገኛሉ…...source,-http://www.diretube.com/
Tuesday, 30 December 2014
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኢትዮጵያ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻ አገር ሆናለች ሲል አስታወቀ
ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል። አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣
ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ ቤቶች በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተዋል ይላል። ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ከኢትዮጵያ ውጪም በተለይ በጂቡቲ፣ደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ በቤት ሠራተኝነት እና በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰሩ እንደሚገደዱ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶች ደግሞ ጂቡቲ ውስጥ በሱቅ ሰራተኝነት፣ በተላላኪነት፣ በቤት ሰራተኝነት፣ በስርቆት እና በጎዳና ላይ ልመና ለግዳጅ ሥራ ተዳርገዋል ብሎአል። በርካታ ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሲሰደዱ ጂቡቲ፣ ግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን ወይም የመንን እንደመሸጋገሪያ ይጠቀማሉ የሚለው ሪፖርቱ፣አንዳንዶቹ ሊሄዱ ካሰቡበት አገር ሳይደርሱ እንደመሸጋገሪያነት ባረፉበት አገር ተይዘው ለብዝበዛ፣ለእስራት፣ለግዳጅ ስራ እና ለመታገት ይዳረጋሉ ብሎአል። በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በቤት ሰራተኝነት የተሰማሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አካላዊ እና ወሲባዊ ጥቃት፣ ደሞዝ ክልከላ፣ እንቅልፍ መነፈግ፣ የፓስፖርት መያዝ፣ በቤት ውስጥ መታገት እና ግድያን ጨምሮ አስከፊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው፣ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያውያን ሴቶች ስራ ፍለጋ ከአገር ከወጡ በኋላ፣ በወሲብ ንግድ ቤቶች፣ በማዕድን ማውጫ ቦታዎች፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ ነዳጅ ዘይት ማውጫ አካባቢዎች ለወሲብ ንግድ ብዝበዛ ይዳረጋሉ ብሎአል። የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀን እስከ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውን በሕጋዊ መንገድ ከአገር እንደሚወጡ ቢገልጽም፣ ይህ ቁጥር ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ30 እስከ 40 በመቶ ብቻ የሚወክል ብሎአል። ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች በሕገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይንም ስደት እንደሚዳረጉ ጠቅሷል። መንግስት በአስቀጣሪ ኤጀንሲዎች ላይ ክልከላ ቢጥልም ክልከላውን ተከትሎ በሱዳን በኩል የሚደረግ ሕገወጥ የሰራተኞች ፍልሰት መጨመሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ጠቁሟል። እ.ኤ.አ. ከሕዳር 2013 ጀምሮ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከ163 ሺ 000 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከአገሩ ያስወጣ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከ94 ሺ 000 የሚበልጡት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ ወንዶች፤ ከ8 ሺ 000 የሚልቁት ደግሞ በእረኝነት እና በቤት ሰራተኝነት የተቀጠሩ ሕጻናት ናቸው ብሎአል። መንግሥት ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድ የተቀመጡትን ዝቅተኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባያሟላም፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል የሚለው ሪፖርቱ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 106 ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የፈጸሙ ወንጀለኞች ሕግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ያደረገ ሲሆን፤ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበርም ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች መጠለያ እና የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አድርጓል ሲል አትቷል። መንግስት የሕገወጥ ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ጨምሮ ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከሌሎችም አገራት የተባረሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የማመቻቸት ስራ ቢሰራም፣ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ሳያደርግ የውጭ አገር ድርጅቶች ይወጡት በማለት ሃላፊነቱን ለእነሱ መተውን ገልጿል። መንግስት ውጭ አገር በሚገኙ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች የሰራተኛ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አታሼዎችን አለመመደቡ፤በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሚሰጡ የዜጎች ደህንነት አገልግሎቶች ላይም ማሻሻያ አለማድረጉም ተጠቅሷል፡፡ መንግስት የሕጻናት የወሲብ ንግድን እና ሌሎች በአገር ውስጥ የሚፈጸሙ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎችን በሕግ ማስከበር፣ ከለላበመስጠት እና በመከላከል በኩል በቂ ሥራ አልተሰራም በሚል ስቴት ዲፓርመንት ትችት አቅርቧል። - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3202#sthash.uvRmXEQ5.dpuf
Monday, 29 December 2014
ዶ/ር መረራ ጉዲና አዲስ ቃለምልልስ
“አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫው ቅርጫ የሚሆን አይመስልም” – ዶ/ር መረራ ጉዲና አዲስ ቃለምልልስ
(ዘ-ሐበሻ) ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ ማምሻውን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከላስቬጋስ ኔቫዳ ለሚሰራጨው ሕብር ራድዮ በሰጡት ቃለምልልስ የዘንድሮው ምርጫ አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ሳይሆን ቅርጫም የሚሆን አይመስልም አሉ:: ዶ/ሩ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተማር ሥራቸው ተባረዋል ስለተባለው ዜናም በቃለምልልሱ ላይ አንስተዋል::ሙሉ ቃለምልልሱን ቀጥሎ ካለው ቭዲዮ ይመልከቱ::
Sunday, 28 December 2014
ለጠ/ሚ/ሩ ጥሪ – የኦባንግ ጥሪ
በባህር ዳር ቁጣ እንዳይገነፍል ፍርሃት አለ
“ዕርቅ ብቸኛ አማራጭ ነው” በሚል እምነታቸው ሁሉንም ወገኖች ነጻ ለሚያወጣ ትግል ራሳቸውን የሰጡት ኦባንግ ሜቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ የመልስ ጥሪ አሰሙ፡፡ ከአቶ ሃይለማርያም የሰሙትን የእንነጋገር ጥሪ በአዎንታዊነቱ ተመልክተውታል፡፡
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ይህንን የተናገሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ያቀረቡትን “ለጋራ አገራችን በጋራ እንወያይ የሚል ጥሪ ማቅረብ ግን እፈልጋለሁ” ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ከሁሉም ፓርቲዎች ጋር በተናጠል መወያየት አንደማይቻል የገለጹት ሃይለማርያም፤ በሦስት ደረጃዎች የመደቧቸውን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ባወገዙበት መግለጫቸው ማገባደጃ ላይ የእንነጋገር ጥሪ አሰምተዋል፡፡ በግልጽ ተለይቶ ያልቀረበው የእንነጋገር ጥሪ ለአኢጋን መሪ ምላሽ መነሻ ሆኗል፡፡
“ምንም ይሁን ምን ከኢህአዴግ መሪ በጋራ የአገራችን ጉዳይ በጋራ እንወያይ የሚል ጥሪ መሰማቱ አኢጋን የጀመረው የረጅም ጉዞ ውጤት ስለመሆኑ ጥሩ ምልከታ ያሳየ ነው” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡
“አኢጋን ለጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ሌላ የመልስ ጥሪ አለው” ያሉት “ጥቁሩ ሰው”፣ ኢህአዴግ እኛ እንደጀመርነው ከራሱ ጋር ተነጋግሮ በጋራ አገራችን ጉዳይ ለመወያየትና ለመምከር ከወሰነ በቀጣዩ ዓመት (2015) በኦስሎ በሚካሄደው የዕርቅ ማመቻቻ ጉባዔ እንዲገኝ መጋበዙን ከወዲሁ ማብሰር እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ኢህአዴግ ወደ ዕርቅ ጎዳና መምጣት እንደሚያዋጣው ከማንም በላይ ጠንቅቆ እንደሚረዳ የገለጹት አቶ ኦባንግ “የጋራ ንቅናቄው ለሁሉም ቦታ ስላለው ከኢህአዴግ የሚጠበቀው በሃሳቡ መጽናትና ለጽናቱ ተግባራዊነት የቀረበለትን ግብዣ መቀበል ብቻ ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡ “ቃል እምነት ነው” ያሉት ኦባንግ ከዚህ ካነሰ እና በተግባር የማይገለጽ የጥሪ ቃል ከሆነ እንደተለመደው ተራ የሚዲያ ፍጆታ ከመሆን አያልፍም ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ለቃላቸው እንዲታመኑ አሳስበዋል፡፡
በአውሮጳውያን አዲስ ዓመት የዕርቅ ቦርድ (ኮሚሽን) ለማቋቋም በኦስሎ የሚደረገውን ጉባዔ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ዝርዝር መግለጫ ለጊዜው አልሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ የዕርቅን ሥራ ለመሥራት የተጀመረው እንቅስቃሴ አሜሪካንን ጨምሮ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ አገራት ድጋፍ እንዳለው አልሸሸጉም፡፡ “ለአገራችሁ የሚያስፈልጋት ትክክለኛ መፍትሔ ይህ ነው” በማለት ከላይ የተጠቀሱት አካላት “ከዲሲው የአኢጋን ጉባዔ በኋላ አጋርነታቸውን በግልጽ አረጋግጠውልኛል፡፡ ለጊዜው ከዚህ በላይ አስተያየት የለኝም” የሚል ሃሳብ የሰነዘሩት አቶ ኦባንግ “በእርግጠኝነት ጉዞውን ስንጀምር መድረስ የምንፈልግበት ግብ ላይ እንደምንደርስ አውቀን ነው፤ ጉዞው ተጀምሮ እዚህ ደርሰናል ቀጣዩ ጉዞ ይቀጥላል፤ የኦስሎ ጉባዔ አስቀድሞ የተቀመጠ የጉዞው አንድ ፌርማታ ነው” ሲሉ አክለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም አቶ ስብሃት ነጋ በተመሳሳይ የዕርቅን አስፈላጊነት መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ የህወሃት የቅርብ ሰዎች ህወሃት ወደ ዕርቅ እንዲመጣ የማሳመን ሥራ መጀመራቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን አቶ ሃይለማርያም ያቀረቡት የእንነጋገር ጥሪ ድንገት አፈትልኮ የወጣ ሃሳብ እንዳልሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡ ጎልጉል ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት፣ በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ ከተለያዩ የማጎሪያ ቦታዎች የሚሰሙት ድምጾች፣ ዓለምአቀፍ ሪፖርቶች፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና፣ ጥላቻ፣ ወገናዊነት፣ በእምነት ደጆች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ ያለ አንዳች ርህራሄ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች፣ ተፈናቃዮች፣ ባይተዋሮች፣ የበይ ተመልካቾች፣ ወዘተ የእነዚህ ሁሉ ድምር በአንድነት የሚያስከትለው መዘዝ ሊጸዳ የሚችለው በይቅርታ ብቻ እንደሆነ ኢህአዴግ በአግባቡ ስለሚረዳ ጥሪውን አናንቆ ማየት አግባብ አይደለም፡፡ የኢህአዴግ በጀት ደጓሚ ምዕራባውያንም ህወሃት/ኢህአዴግን ያነገሡ እንደመሆናቸው እጅ መጠምዘዙንም በውል ያውቁበታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ዘለቀ የከፋቸው ሲበዙ ዓመጽ መነሳቱና አብዮት መቀጣጠሉ እንደማይቀር የተለያዩ አምባገነኖችን መጨረሻ ዋቢ በማድረግ ተናገሩ፡፡ ሐሙስ ዕለት ቪኦኤ ባቀረበው ዘገባ የተደመጡት ይልቃል “ያለአንዳች ፍርሃት እናገራለሁ” በማለት እንደገለጹት ኢህአዴግ በማስፈራራትና በማሰር የሕዝብን ቁጣና ምሬት የማስቆም አቅም ሊኖረው እንደማይችል ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ሥርዓቱ ከአንገት እስከ እግሩ በሙስና መነከሩን አመልክተዋል፡፡ በእስር ቤት ያሉት ጓዶቻቸው እስር ቤት ካልገቡት ጓዶቻቸው የተለየ የፈጸሙት ተግባር እንደሌለም መስክረዋል፡፡
የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው ኢህአዴግን የማስገደድና የማስጨነቅ ሥራ ተጠናቅሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቻ ግመል ሰርቆ የሚለውን ተረት በመተረት የኢህአዴግን ታላቁ የንግድ ኢምፓየር የዝርፊያ ማዕከል መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የአገሪቱን ሃብት ኢህአዴግ ለግል የፖለቲካ ሥራ እንደሚጠቀምበትም አረጋግጠዋል፡፡ በቪኦኤ የቀረቡት ሦስቱም የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች ይህንን ምላሽ የሰጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ ላቀረቡት ውንጀላ ምላሽ ለሰጡት መግለጫ ነው፡፡
ዜና ባለፈው ሳምንት በባህር ዳር ከተማ የተፈጸመውን ግድያና ድብደባ ተከትሎ የቁጭት አመጽ እንዳይነሳ ሥጋት መኖሩ ተጠቆመ፡፡ ከአካባቢው የሚሰሙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢህአዴግ ለፈጸመው ግድያና ድብደባ የነዋሪዎች ቁጣና የበቀል ስሜት ሊሸሸግ የሚችል አይደለም፡፡ ለዚህ ይመስላል ቪኦኤ ያናገራቸው ሰው ጥበቃው በከፍተኛ ደረጃ መጠናከሩን ያረጋገጡት፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት እዚሁ ባህርዳር እንግሊዛዊው በነፍጥ አንጋቢ መገደሉ የውጥረቱ መጠን የት እንደደረሰ እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡ ከጸጥታው ጋር በተያያዘ የበቀል ዓመጹ ወደ ወረዳና ቀበሌ አድባራት ብሎም ወደ ሌሎች ዞኖች እንዳይዛመት የኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሌት ተቀን የመረጃ ልውውጥ እንደሚያካሂድ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ ወደ ከተማዋ ከተላኩት ነፍጥ አንጋቾች በተጨማሪ ሲቪል የለበሱ ሰላዮች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ ከአካባቢው የሚገኙ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ት/ቤቶችና በአጠቃላይ የትምህርት ማዕከላት የክትትሉ ቁልፍ ቦታዎች ናቸው፡፡
የባህር ዳር ሟቾች ቁጥር ስድስት መድረሱን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የሆስፒታል ምንጮቻቸውን ጠቅሰው አመልክተዋል፡፡ በወቅቱ ምንጮቼ ሰው እንደሞተ ማረጋገጥ አልቻሉም በማለት የዘገበው ሪፖርተር በረቡዕ ዕትሙ ፖሊስን ጠቅሶ አንድ ሰው ሞተ፤ ምንጮቹን ጠቅሶ ሦስት ሰው ሞተ፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ደግሞ ጠቅሶ አምስት ሰው ሞተ ሲል ወጥነት የሌለው ዜና ማቅረቡ ለዜናው የሰጠውን ደንታቢስነት የሚያሳይ እንደሆነ ቅሬታ የተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ አስቀድሞም ቢሆን የሟቾቹ ቁጥር በትክክል አይገለጽ እንጂ ሪፖርተር ከስፍራው በቂ መረጃ ደርሶት እንደነበር የሚያውቁ ትዝብታቸውን “ጊዜ ይፍረድ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ጉዳት ደረሰባቸው የተባሉትን አስመልክቶ ማኅበራዊ ገጾች በፎቶ አስደግፈው ካቀረቡት መረጃ በስተቀር ቁጥራቸው፣ የጉዳታቸው መጠን፣ ግለ መረጃዎች፣ ወዘተ ዘርዝሮ ያቀረበ አካል የለም፡፡ በክርስትና ሃይማኖት ተቋምነት የሚታወቁ ማኅበራት፣ አድባራት፣ ሰባካ ጉባዔዎች፣ የፓትርያርኩ ጽ/ቤት፣ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች ያቀረቡት ውግዘትም ሆነ አንዳች ነገር እስካሁን አልተሰማም፡፡
source,-(http://www.goolgule.com/)
Friday, 26 December 2014
የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት የተቀነባበረ ግድያ
የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት የተቀነባበረ ግድያ ድንጋጤ ፈጥሯል::
Dec 26th, 2014 ·
የባህር ዳሩ ገዳይ ካለምንም ጥያቄ በቀጥታ ለፖሊስ እጁን ሰቷል::
ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ካሳንቺስ ከቀድሞ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ከሚገኘው ድብቅ የደህንነት እስር ቤት ውስጥ በመገኘት በከፍተኛ የሴኩሪቲ ጥበቃ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር Greg Dorey እንዳነጋገሩ ሲታወቅ ከአንዳርጋቸው ጋር ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ባይገኝም በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲገልጹ የኤምባሲው ምንጮች እንዳሉት ስለ አንዳርጋቸው መረጃ ያላቸው ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ክፍተኛ የደህንነት አባላት እና የአንድ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል::እንዲሁም አመነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳርጋቸውን በተመለከተ ከታፍነ 6 ወር መሆኑን ገልጾ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ሲል ለእንግሊዝ መንግስት አቤት ያለበተን መግለጫ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ አውጥቶ ነበር::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ አንድ አርሶ አድር ታጣቂ ሚሊሻ በሚመስል ጸጉረ ልውጥ ሰው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ቱሪስት መገደሉ ታውቋል::የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት መገደል ድንጋጤ ፈጥሯል::ገዳዩ ለግድያው እንደተዘጋጀበት በሚያስታውቅ መልኩ በአከባቢው አድብቶ ሲጠባበቅ የነበረ እና ወዲያው እንግሊዛዊውን እንደገደለው ለፖሊስ ያለምንም ጥያቄ እጁን ሰቷል::በአከባቢዉም የታተቁ ፖሊሶች የነበሩ ሲሆን ግድያው ሲፈጸም ምንም ያደረጉት መከላከል አልነበረም::ግድያው የተቀነባበረ ነው ሲል የባህር ዳር ህዝብ እየተናገረ ነው::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
-source:- http://satenaw.com/amharic/archives/3175#sthash.DV7Q1RLI.dpuf
በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፎች ይደረጋሉ
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ይፋ አደረገ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ትብብሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብሩን በህዳር ወር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩ ደግሞ ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን ተገልጹዋል፡፡
የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ፤ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳርና በአዳማ ደግሞ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) በመግለጫው ወቅት ተናግረዋል፡፡
‹‹የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር ነው›› ያለው መግለጫው፣ በትብብሩ በኩል በአመራር ከፊት ቆመው ትግሉን ለመምራት ዝግጁነትና ቁርጠኝነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡
‹‹የያዝነው የትግል መንገድ ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣ መጓጓዣችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን›› ብሏል ትብብሩ በመግለጫው፡፡
እቅዱ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ መሆኑን ያተተው የትብብሩ መግለጫ፣ ‹‹ዓላማችን የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ ሚናችንም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው›› ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡ ነጻነት በሌለበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው ሲልም አክሏል መግለጫው፡፡
ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት ማካተቱም ተመልክቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት፤ በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡
የትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ተግባራቱን በጊዜ ሠሌዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት ማጽደቁንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ትብብሩ ለያዘው ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ሌሎች ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
......... source,-https://www.facebook.com/negere.ethiopia
Thursday, 25 December 2014
ሰብአዊነት ያስቀደመ ኢትዮጵያዊ
አብርሃ ደስታ - ሰብአዊነት ያስቀደመ ኢትዮጵያዊ
(ከፍኖተ ነፃነት)
ትግራይ ክልል ላይ የሚፈፀሙትን ጭቆናዎች ሳይታክት አጋልጧል። ዘረኝነትን ፣ አምባገነንነትን ፣
ሙሰኝነትን ፣ ኢ-ፍትሐዊነትን አውግዟል። ሰብአዊነትን በማስቀደም ሰውን በሰውነቱ የሚለካ ምርጥ
ኢትዮጵያዊ ነው-አብርሃ ደስታ፡፡ አብርሃ ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሰዎችን ቀልብ ለመሳብ
ከመቻሉም በላይ ፤ “ፌስቡክን” ከፌዝ-ቡክነት በመታደግ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን ሲያቀብለን
ነበር፡፡
በመግቢያችን ላይ በአጭሩ እንደተገለጸው ይህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ፣ የአሁኑ የፖለቲካ እስረኛ አብርሃ
ደስታ በአንድ ወቅት ከፍኖተ-ነፃነት ባልደረባ ጋር ያደረገው ወግ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
በቀዳሚነት የቀረበለት ጥያቄ “በመጪው ምርጫ ተቃዋሚዎች የሚያሸንፉ ይመስልሀል? የሚል ነበር፡፡
የሠጠው ምላሽ “በተቃውሞ ጎራ ውስጥ ያሉ ሀቀኛ ተቃዋሚዎች ምርጫን እንደ ግብ ማየት
የለባቸውም፡፡ በምርጫ መሳተፍን እንደ መንገድ (means) እንጂ እንደ ውጤት (end) ሊወስዱት አይገባም፡፡ በምርጫ መሳተፍን
የሚቀበሉ የምርጫ ፓርቲዎች የተናጠል ጉዞ የትም እንደማያደርስ ተገንዝበው አንድ ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የተናጠል ትግል
ተጠቃሚ የሚያደርገው ገዢውን ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ ምርጫ 1992ትን ብንመለከት በዚህ ምርጫ ላይ ገዢው ፓርቲ በአንድ ምርጫ
ጣቢያ ላይ በርካታ እጩዎች እንዲመዘገቡ በማድረግ ድምፅ እንዲከፋፈል ተግቶ ሰርቷል፡፡ በአንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ ከ20 በመቶ
በሚያንስ ድምፅ ብቻ ገዢው ፓርቲ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ይህ ለምን ሊሆን ቻለ? የሚለውን ብንመለከት በአንድ የምርጫ ክልል ላይ
በርካታ እጩዎችን አስርጎ በማስገባት የተቃዋሚዎች ድምፅ እንዲከፋፈል ስለተደረገ ነው፡፡ በወቅቱ ተቃዋሚዎችም በህብረት ከመታገል
ይልቅ በተናጠል መታገልን መርጠው እንደነበር የሚዘነጋ አልነበረም፡፡ ከዚህ በመነሳት ነው የተናጠል ትግል አያዋጣም የትም አያደርስም
የምልህ፡፡ ስለሆነም በመጪው ምርጫ ጠንካራ የሚባሉት ፓርቲዎች ቢቻል ውህደት ካልሆነም ግንባር ፈጥረው ከታገሉና ህዝቡ ጋር
በደንብ ከተገናኙ ገዢውን ቡድን በምርጫ የማያሸንፉበት ሁኔታ አይታየኝም፡፡
ትልቁና አሳሳቢው ጉዳይ ገዢው ቡድን በምርጫው ሲሸነፍ ወይም እንደሚሸነፍ ሲያውቅ የሚወስደው እርምጃ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ላይ
ኮሮጆን ከመገልበጥ አንስቶ እስከመግደል የሚዘልቅ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡ ስርዓቱ ጡንቻውን ማሳየት የጀመረ ጊዜ ህዝቡ
እምቢተኝነቱን በተግባር ሊያሳይ ይገባል፡፡ ድምፁ ሲሰረቅ በዝምታ መመልከት አይኖርበትም፡፡ ለድምፁ መከበር ራሱ ዘብ ሆኖ መቆም
ይኖርበታል፡፡ ህዝቡ ከራሱ ውጪ ለራሱ ድምፅ የሚቆምለት አንድም አካል እንደሌለ ተረድቶ ድምፁን ማስከበር ይጠበቅበታል፡፡ ህዝቡ
ግዴታውን በዚህ መልክ ከተወጣና ሀቀኛ ተቃዋሚዎችም የተናጠል ትግሉን ትተው በህብረት ከታገሉ ይህን ስርዓት በምርጫ
የማያስወግዱበት አንዳች ምክንያት የለም፡፡” የሚል ነበር፡፡
አብርሃ ፣ በምሳሌነት ያነሳውን የምርጫ 92ቱን ሁነት የቀድሞው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ ለገሠ ፣
“የመለስ ትሩፋቶች ባለቤት አልባ ከተማ” በሚለው መፅሀፉ ላይ አንድን ወረዳ በምሳሌነት በማንሳት በወቅቱ ስለነበረው ሁነት እንዲህ
ይተርክልናል፡፡
“በወረዳ 24 ለፓርላማ የቀረቡት የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ከአራት በላይ መሆናቸው እና የራሳቸው ደጋፊ ያላቸው መሆኑ
በተጨማሪነት ጠቀመን፡፡ ኢዴፓን ወክሎ የቀረበው ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) በወጣቶች ፣ ክፍሌ ጥግነህ (የቅንጅት አመራር
የነበረ) በምሁራንና ነጋዴው ማህበረሰብ ፣ የትግረ ወርጂው ሀጂ መሃመድ በሙስሊም ዘንድ ተቀባይነት ነበራቸው፡፡
የሰርቶ አደር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረው ታዲዮስ ታንቱ በቀድሞ ስርዓት ደጋፊዎችና ወታደሮች ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ሌሎቹ የግል ተወዳዳሪ
እጩዎች በእኛ የቀረቡ ሲሆን ኢህአዴግን መምረጥ በማይፈልገው አካባቢ ድምፅ እንዲሻሙ የተዘጋጁ ናቸው። በመሆኑም በአብላጫ
ወንበር አሰራር መሰረት ከ84% በላይ ህዝብ ያልመረጠው የኢህአዴግ እጩ ወደ ፓርላማ ገባ፡፡ ከውጤቱ ማየት እንደሚቻለው
አግባብተን ካስገባናቸው የግል እጩዎች አንዱ ራሱን ቢያገል ውጤቱ ግልብጥብጡ ይወጣ ነበር ፣ ኢህአዴግን የወከለው ሰው ፓርላማ
አይገባም ነበር፡፡” (ገፅ 60-61)
ለአብርሃ ደስታ የቀረበለት ሁለተኛ ጥያቄ “ሀቀኛ የምትላቸው ተቃዋሚዎች ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ሀቀኛ የምትላቸው
ተቃዋሚዎችስ እነማን ናቸው?
አብርሃ ፣ ምላሹን እንደሚከተለው አስከተለ፡፡ “ሀቀኛ ስል እውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ ምርጫ ሲደርስ ብቻ
ከመሸጉበት ወጥተው አለን የማይሉና ተለጣፊ ያልሆኑ ፓርቲዎች ልልህ ፈልጌ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ሀቀኛ ስል የምመድባቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አረና ፣ ኦፌኮ ሰማያዊ ፣ አንድነትና መድረክን ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በተናጠል ሳይሆን በጋራ ሆነው ሀገር የማስተዳደር ብቃት
አላቸው ብዬ እገምታለሁ፡፡ የራሳቸው ደንብና ፕሮግራም ያላቸውና አንድ ሰው እንዳሻው የማያሽከረክራቸው ፓርቲዎች ናቸው፡፡ በራሴ
መመዘኛ እነዚህን ፓርቲዎች ሀቀኛ በማለት እመድባቸዋለሁ፡፡ በአንፃራዊነት ከሌሎች ፓርቲዎችም የሚሻሉና ጠንካራ ብዬ የምመድባቸው
እነዚህ ከላይ በስም ያነሳሁልህን ፓርቲዎች ነው፡፡”
አሁን ባለው የፖለቲካ ምህዳር ምርጫ መሳተፍ አያዋጣም የሚሉ ወገኖች በስፋት አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች
ምርጫውን አለመሳተፍ (boycott) እንደ መፍትሔ ያስቀምጣሉ፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚያቀርቡት ነፃና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ
ቦርድ በሌለበት ፣ ስርዓቱ የፖሊስ ፣ መከላከያና ደህንነቱን በቁጥጥሩ ስር ባደረገበት ሁኔታ ምርጫ መሳተፍ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለዚህም
ምርጫውን አለመሳተፍና ገዢው ቡድን ብቻውን እንዲወዳደር ማድረግ የተሻለ ነው ይላሉ። “ምርጫን አለመሳተፍ (boycott) ማድረግ
መፍትሔ አይሆንም” ይለናል፡፡
ወጣቱ የፖለቲካ እስረኛ አብርሃ ደስታ ግን “በሰላማዊ መንገድ የምታገል ፓርቲ ነኝ እስካልክ ድረስ በምርጫ የመሳተፍ ግዴታ ውስጥ
ትወድቃለህ፡፡ በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፓርቲ ስልጣን የሚይዘው በምርጫ ነው። ስለሆነም በምርጫ መሳተፉ የሚጠበቅ ነው፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩ በጣም የጠበበ መሆኑ አያጠያይቅም። “የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል” ብሎ ግን ምርጫን አለመሳተፍ ግብ ሊሆን
አይገባም። ቅድም ስንነጋገር ሀቀኛ ብዬ ያነሳውልህ ፓርቲዎች ተባብረው እንኳ ምርጫውን ላለመሳተፍ ቢወስኑ ኢህአዴግ ግድ
አይሰጠውም። ራሱ የፈለፈላቸውን ፓርቲዎች ወደ ምርጫ እንዲገቡ አድርጎ ማሸነፉን ማወጁ አይቀርም፡፡ ምርጫውን ቦይኮት ለማድረግ
ቢታሰብ እንኳ ወቅቱን ማገናዘብ ያስፈልጋል፡፡ ለምርጫው የተወሰነ ጊዜ ሲቀረው ነባራዊ ሁኔታዎችን አገናዝቦ ራስን ከምርጫው ማግለል
ይቻላል። ምርጫ ህዝቡ ጋር የምትደርስበት አንድ መንገድ እንደመሆኑ መጠን ህዝቡን ከቀሰቀስክ በኋላ ከምርጫው ራስን ማግለል
ይቻላል፡፡ በግሌ ምርጫን ቦይኮት ማድረግን ግን አልደግፍም፡፡”
አንድ የሚከነክነኝ አከራካሪ ሀሳብ አለ፡፡ ይህ አከራካሪ ሀሳብ ጥቂት በማይባሉ ሰዎች ይነሳል፡፡ የትግራይ ህዝብ በስርዓቱ እንደተጠቀመ
አድርጎ የማቅረብ ነገር በስፋት ይታያል፡፡ የትግራይ ህዝብንና ሕወሓትን አንድ አድርጎ የመመልከት ነገርም አለ። አብርሃ ፣ የትግራይ
ህዝብና ሕወሓትን ለያይተን መመልከት እንዳለብን በተደጋጋሚ ገልጿል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ባነሳሁለት ጊዜ ተከታዩን ምላሹን ሰቶኛል፡፡
“የትግራይ ህዝብና ሕወሓት ሌላ ቢሆኑም የትግራይ ህዝብና ሕወሓትን የመቀላቀል ነገር በስፋት ይታያል። በትግራይ ምድር ስላለው
ጭቆና በስፋት ፅፌያለሁ። የትግራይ ህዝብ በስርዓቱ እንዳልተጠቀማ ለማየት የአዲስ አበባ ጎዳናዎችን ብቻ መመልከት በቂ ይመስለኛል፡፡
አብዛኛው ለማኝ ከትግራይ ክልል እየፈለሰ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣው በትግራይ ምድር መኖር አመቺ ስላልሆነለት እንጂ ልመናን መርጦ
አይደለም፡፡ ሕወሓት ሁልጊዜም የትግራይ ህዝብን የሚያስፈራራበት አንዳች ካርድ አለችው፡፡ ይህቺ ካርድም እኔ ከሌለሁ ደርግ ተመልሶ
ይመጣባችኋል የምትለው ናት፡፡ ተቃዋሚዎችን በጠቅላላ ፀረ-ትግራይ አድርጎ ይስልና ፕሮፖጋንዳውን ይረጫል፡፡ የትግራይ ህዝብ እንደ
ሌላው ህዝብ ሁላ ሕወሓትን ይፀየፋል። ሕወሓት ምንም ያመጣለት ነገር እንደሌለ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በስሙ እንደሚነገድበትም በሚገባ
ተረድቷል፡፡
ስለሆነም ሕወሓትን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ላይ የበኩሉን ሚና መጫወት ይፈልጋል፡፡ በዚህ ትግል ላይ እንዲሳተፍ የሚያደርገው
በሀገራችን የተንሰራፋው ጭቆና ነው፡፡ የትግራይ ህዝብን ጭቆና መቀበልና እውቅና በመስጠት ለችግሩ መፍትሔ ማበጀት ይቻላል ባይ
ነኝ። ሌላው እዚህ ላይ ላነሳው የምፈልገው ጉዳይ የተቃዋሚ አመራሮች ስለትግራይ ህዝብ ሲያነሱ ወያኔ ባይሉ ይመረጣል ባይ ነኝ፡፡ ወያኔ
ማለት እምቢ-ባይ ወይም አብዮተኛ ማለት ነው፡፡ የዛሬው ገዢዎቻችን ወያኔዎች አይደሉም፡፡ የትግራይ ህዝብ ግን ወያኔ ነው፡፡ የተቃውሞ
ጎራ አመራሮች ወያኔ በማለት ቃሉን ሲጠቀሙ የትግራይ ህዝብን እያስከፉ እንዳሉ ሊገነዘቡ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ዛሬም ድረስ የትግራይ ህዝብ
ወያኔ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ ወያኔ የሚለው ቃል ሕወሓትን ለመግለፅ መዋል የለበትም። ይህን ማድረግ ከተቻለ ለችግሮቹ በቀላሉ መፍትሔ
ማበጀት ይቻላል ባይ ነኝ እላለሁ፡፡”
አብርሃ ፣ ሕወሓት በትግራይ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍና በደል ማጋለጡ ፣ ገዢዎቻችንን እንቅልፍ አሳጥቶ ስላሸበራቸው
አስረውታል፡፡ የዛሬው ፅሁፍ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በአንድ ወቅት ስለ አብርሃ ፣ ከጻፉት በመቆንጠር ቆይታችንን እንቋጫለን፡፡
“በእኔ ግምት ባለፉት ሀያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ትግራይ እንደ አብርሃ ያለ ድንበር-ዘለል ፣ ጠልቆና አርቆ የሚያስብ ወጣት አፍርቶ
አላየሁም ፤ ከትግራይነት አልፎ ፣ ከኢትዮጲያዊነት አልፎ በሰውነት ደረጃ ላይ የሚከበርና የሚያስከብር ወጣት ነው ፤ ስለዚህም በአብርሃ
መጨቆንና መታፈን ትግራይ ብቻ ሳትሆን ኢትዮጵያም ትጎዳለች ፤ ይቺ ሀገር ሰው እንዳይበቅልባት የተደረገው እንዲህ በአምባገነኖች
ጭካኔና በሕዝብ አስረካቢነት ነው። እግዚአብሔር አብርሃን ይጠብቀው! እኛንም ከለላ ለመሆን መንፈሳዊ ወኔውን ይስጠን፡፡”
source,-ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
December 23, 2014
እየተደረገ ያለዉን በዘርኝነት ማክሸፍ የእያንዳንዱ እትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ ግዴታ ነው ፤
እየተደረገ ያለዉን በዘርኝነት ላይ የተመሠረተ የጥፋት ቃለ መሃላ ማክሸፍ የእያንዳንዱ እትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ ግዴታ ነው ፤
ከአየነው ብርሃኑ
ኢትዮጵያዉያን የዉጭ ጠላት ሲነሳባቸዉ የዉስጥ ልዩነታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ ጠላትን ድባቅ የመምታት አቅሙ እንዳላቸዉ የሩቅም ሆነ የቅርብ ታሪካችን ነዉ።
ከቅርቡ እንኳን ብንነሳ በሻቢያና ወያኔ የጥቅም ግጭት ምክንያት በተነሳ ጦርነት ሮጠዉ ያልጠገቡ ወጣቶች የፈንጅ ማምከኛ እየሆኑ ዉድ ህይወታቸዉን አሳልፈዋል።
ወያኔ ለራሱ ህልዉና ማጠናከሪያ ቢጠቀምበትም የጦርነቱ የመጨረሻ ዉጤት ለኢትዮጵያ ያደላዉ ከኢትዮያዊነት ስሜት በመነጨ ወኔ መሆኑ አይዘነጋም።
አዎ ወያኔ እና ጀሌዎቹ ከኋላ ፤ በሺህዎች የተቆጠሩ ወጣቶች ግን በግንባር ቅደምትነት ተሰልፈዉ የቦንብ ማምከኛ በመሆናቸዉ የጦርነቱ አቅጣጫ ተቀየረ። በዚህ እልቂት ኢትዮጵያዉያን እናቶች የሃዘን ማቅ ለበሱ። ወያኔም በሥልጣን መንበሩ ላይ መቆየቱን አረጋገጠ።
ጭር ሲል አልወድም የሚለዉ ወያኔ ዛሬም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው። የማይደፈር ሃይል መሆኑን ለማሳየትም በርጥባን ከጌቶቹ ያገኘዉን የጦር መሳሪያ ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ህዝብን በማሸበር ላይ ነዉ።
በጦር ሃይሉ ዉስጥ ያሉ የሌላ ብሄር የጦር መሪዎችን በማባረር በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግድያ እና የጥፋት ሃይሉን በማዘጋጀት ላይ ዪገኛል።
ለዚህ ተግባር የሚዉል አዲስ ወታደራዊ ቅጥር ጥሪ እያደረገ መሆኑ ዪታወቃል።
የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት ከሆነችዉ ሱዳን ጋር ወታደርዊ ስምምነት አደረኩ የጋራ ጦርም መሠረትኩ በሚል ለጥቂት ቀናት አደነቆረን።
ተጠቅሞ የጣላቸዉን የቀድሞ ሰራዊት አባላት ተመልሰዉ እንዲቀላቀሉት በተለያየ መንገድ ጥሪ እያደረገ ነው። ሁሌ እኔ ብቻ ላሞኛችሁ የሚል የደንቆሮዎች ዘይቤ። መልሱ ግን ሞኚህን ፈልግ ሆነ !!
ለመሆኑ ይኸ ሁሉ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ከምን መጣ ? ይህ የድረሱልኝ ጥሪ መነሻዉ ምንድን ነዉ፡የዉጭ ጠላት አልወረረን!!!!!
የወንድ ልጅ ሞቱ የሚጀምረዉ ያደረገዉን የረሳ ጊዜ ነው ይላሉ አበዉ ሲተርቱ።
ሃብት አደንቁሮአቸዋልና !! ወያኔን ለማጥፋት አዲስ አበባም ጫካ መሆኑን ለመገንዘብ የዕዉቀት አድማሳቸዉ አልፈቀደላቸዉም ።
ያም ሆነ ይህ ግን ምኞታቸዉ የተሳካ ጥያቂያቸዉም በአግባቡ እየተመለሰላቸዉ ባለበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል። የስብሃት ነጋ የዘር ጥላቻ፡ የአባይ ጸሃየ የዕምነት ተቋማትን የማፈራርረስ ሴራ፤የአዲሱ ለገሰ ከጡረታ መመለስ ከውዲያ ወዲህ መፈራገጥ፤ የበረከት በስብሰባ ላይ ራሱን ጥሎ ከመዉድቅ ዉጭ ፋይዳ ያለዉ ሥራ ለመከወን ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረስ ወይም ደግሞ ብአዴን በግንቦት ሰባት ኦህዴድንም በኦነግነት መፈረጅ ከዉድቀት አያድናቸዉም ።
የእነ ደብረጽዮን እና ጌታቸዉ አሰፋ ድንበር ዘለል የዉንብድና ተግባር አልፈየደም ። የህዝብ ወገኖችን እያደኑ መያዝ፡ በአለም ላይ አለ የተባለ የማሰቃያ መንገድ ሁሉ በታጋዮች ላይ እንዲፈጸም ማድረግ በተጠናወታቸዉ የዘር ጥላቻ እየተወጠሩ ለመኖር እና ያለ አግባብ በተካበተ የሀገር ሃብት እየተንደላቀቁ ለመኖር መፍትሄ አልሆነም።
በሌላ መልኩ የመሃል አገር ህዝብ የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ በመበጣጣስ አንድነቱን አጠናክሮ ወያኔን ጥግ ማስያዝ ከጀመረ ሰነባበተ ። የህዝብ ጉልበትም መጎልበትና መፈርጠም ጀምሮአል ።
ሰላሙና ተቻችሎ መኖሩ ይበጃል በሚል እንጂ ለሌላዉማ ከእናንተ በተሻለ እኛም እናዉቅበታለን የሚሉ አንበሶች ብቅ ብቅ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አንድነታቸዉንም አጠናክርው ለመጨረሻዉ ፍልሚያ በትጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ ።
ለዚህም የትግራይ ረመጦች በአንድ በኩል የግንቦት 7 ፤ የአርበኖች ግንባርና ሌሎችም አንበሶች በሌላ በኩል ለዎያኔ እኩይ ተግባር ምላሽ ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል በሚል የድል ችቦ እየለኮሱ ያሉት ህያዉ ምስክር ነው።
ወያኔ አንድ አርጋቸዉንና ሌሎችንም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ያዘ፤ አሰቃየ ፤ የአካልም የመንፈስም ጉዳት አደረሰ ይህን ሲያደርግ ግን ያለኪሳራ አይደለም። መቃብሩን እየቆፈረ መሆኑን ራሱ ወያኔም ያዉቀዋል ።
ለትግራይ ረመጦችና ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መጠናከር መሠረት የሆነዉን አንዳርጋቸዉ ነዉና ። አንዳርጋቸዉን መያዝና ማሰቃየት ዉድቀቱን እያፋጠነለት መሆኑን ወያኔ ራሱ ከተረዳዉ ቆይቶአል።
በሌላ በኩል እስኪ የዘርኝነት መሃንዲሶቹን አንድ አንድ ጥያቄዎች እንጠይቅ፡
ይኸ የህዝብ ትግል የጦርነት ነጋሪት በመጎሰምና የድረሱልኝ ለቅሶ በማላዘን ወደ ኋላ ይቀለበስ ይሆን እንዴ አቶ ስብሃት?
የስንት ቀን ፋታ የምታገኙ ይመስልሃል አቶ አባይ?
በርግጥ የአንተና የስዩም መስፍን ማገገም፡ ወደ ሥራ መመለስና መንፈራገጥ መፍትሄ ይሆን እንዴ አቶ አዲሱ ለገሠ?
ሃዉልትህ ምትሃታዊ ሃይል ኖሮት የልቀቁኝ በቃኝ ጥያቄህን ወደ ኋላ እንድትል ይረዳህ ይሆን ጀኔራል ሳሞራ?
በአፈናና በስቃይ ተግባራችሁ ግለሰቦችን ከማሰቃየት በዘለለ የህዝብን ትግል አፍናችሁ ከዛሬ ነገ ምን ይከሰት ይሆን ከሚለዉ የፍርሃት ቆፈናችሁ የምትላቀቁ ይመስላችኋል እነ ደብረ ጽዮን ፤ ጌታቸዉ በላይ እና የአፈና ቡድናችሁ?
በጭራሺ ከንቱ ድካም። ከንቱ ልፋት። የኢትዮጵያ ህዳሴ መቃረቡን የህዝብ የነጻነት ጮራ እየፈነጠቀ መሆኑን ምነዉ ያኔ የሱዳኑ አባታችሁና የአምልኮት ጣኦታችሁ ሲሞት በቀብር የተገኙት እነስዩም መስፍን አልነገሯችሁም ነበር እንዴ?
ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርስ ለማገዳደል እያሰባችሁ ያላችሁት የጥፋት ድግስ የማይሳካ ጊዜዉ ያለፈበት ዘዴ ነው። የተበላ እቁብ !!!
በሀገራዊ ስሜትም ሆነ በግል የኢኮኖሚ ችግርህ አሁን ያለዉን የመከላከያ ሠራዊት የተቀላቀልክ ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ቆም ብለህ አስብ። እነዚህ የቀን ጅቦች ለጥፋት እያዘጋጁህ መሆኑን ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን መዘንጋት የለብህም።
የባህር በር እጠብቃለሁ እንዳትል ወያኔ አገርህን የባህር በር አልባ አድርጎልሃል። ድንበር አስከብራለሁ እንዳትል ወያኔ የአገርህን ድንበር እየቆራረጠ ለአገራችን ጠላቶች ለገጸ በረከትነት እያቀረበልህ ነው።
ወያኔ ወኔህን ሰልቦ ብሄራዊ ወኔህን ገፎታል። እንድ ለአምስት እንድትደራጅ ፡መሪህ ከወርቁ ዘር የወጣዉ ብቻ እንዲሆንና አንተ አንድ ካርታ ጥይት ብቻ እንዲኖርህ መሪህ ግን እስካፍንጫዉ እንዲታጠቅ እየተደረገ ያለዉ ለምን ይመስልሃል። በዚህ አይነት ጥርነፋ ከወገኖችህ ጋር እንድትዋጋ ከኋላ ሆነው ሊነዱህ እንደሆነ ግን ተገንዝበኸዋል?
ይኸን ከንቱ የወያኔ ምኞት ለማክሸፍ ከነጻነት ታጋዮች ወገኖችህ ጋር ጊዜ ሳትሰጥ ተቀላቀል።
ይህን በማድረግህ አገርህን ከነዚህ የባንዳ ዉላጆች ነጻ ታወጣለህ ። በስቃይ ላይ የለዉን ወገንህን እንባ ትጠርጋለህ።
በዘር ማንነት ፖለቲካ ተሰብካችሁ ከሌላዉ በበለጠ ጀግንነት የእናንተ ብቻ እንደሆነ እየተሰበካችሁ ያደጋችሁ የመሪነት ቦታዉን የያዛችሁና እኛ ከኋላ ሆነን ሌላዉን ኢትዮጵያዊ ከፊት በማሰለፍ የጌቶቻችንን የስልጣን ዕድሜ እናራዝማለን ብላችሁ በዘር ላይ የተመሠረተ ቃለ መሃላ የፈጸማችሁ ። ይህ መሃላ ግን መፈራረሱን ወደ ህዝብና ወደ ህሊናቸዉ ተመልሰዉ ወደ ዕዉነታዉ ዓለም በተቀላቀሉት ሻምበል ግደይ ሳሙእል እና ቴክኒሺያን ፀጋብርሃን ግደይ ላይ ያዎረዳችሁት የከሃዲነት ዉንጀላ አብይ ምስክር ነው።
በከንቱ ዉዳሴ ተወጥራችሁ ህዝብን አሸንፈን በሥልጣናችን እንቀጥላለን ብላችሁ የምታስቡ የጦር መሪ ነን ባዮች ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ምንም ችግር የለበትም። ታሪኩ፡ ባህሉ ወጉና ልምዱ በአብሮ መኖር በኩል ችግር እንደሌለበት ምስክሮች ናቸዉና!!!
በሌላ በኩል ግን የትግራይ ረመጦችም ሆኑ የግንቦት ሰባት አንበሶች ለአንድ አላማ ለኢትዮጵያዊነት እና በሰላም ተቻችሎ ለመኖር ነዉ እየዘመሩ ያሉት።
ይህ ሲባል ግን ስብሃት ነጋ ከዘር ጥላቻዉ እንዲላቀቅ ሱባኤ እንዲገባ አይደረግም ማለት አይደለም።
አባይ ጽሃይም ላለበት ሃይማኖትን የማፍረስ አባዜ በአርባ ቀን ጥምቀት ለመንጻት ቄስ አያጠምቀም ወይም ሼህ እይጎበኘዉም ማለት አይደለም። የትኛዉ እንደሚፈዉሰዉ ምርጫዉ የራሱ ነው።
የነ ደብረጽዮን ፤ ጌታቸዉ አሰፋና አምስቱ የአፈና ቡድናችዉ የመሰረቷቸዉን ድብቅ ያማሰቃያ ቦታዎች ይፋ እንዲያደርጉ ፤ ያጠፏችዉን ኢትዮጵያዉያን ዝርዝር እንዲያቀርቡ ህዝብ አይጠይቃቸዉም ማለትም አይደለም።
ሳሞራ የኑስ ምን ኣልባት ለዚያ ከደረሰ የጀኔራልነት ሃዉልቱን ተሸክሞ በአደባባይ በመዞር ለዚህ ያበቃዉን ገድል እንዲተርክለት ህዝብ ይጠቅ ይሆናል ።
የብአዴን፤ ኦህዴድና ኦህዴድ ፈረሶችም ቢሆኑ በሀገር ላይ ክህደት ከፈጸመዉ ደመቀ መኮነንና በንጹሃን ደም እጁ ከተጨማለቀዉ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ከመሳሰሉት በስተቀር ሌሎቹ የማስመሰያ የዘር ጭምብላቸዉን አዉልቀዉ ለአጠፉትም ጥፋት ይቅርታ ጠይቀዉ ወደ እዉነተኛ ማንነታቸዉ እንዲመለሱና የ 24 ዓመት ድራማዉን እንዲተርኩለት የኢትዮጵያ ህዝብ መጠየቁ የሚቀር አይመስለኝም።
የትናት ሺፍቶች የዛሬ ሚሊዮነር ጀኔራሎች የሃብት ምንጫቸዉን እንዲነግሩን መጠየቅ የኢትዮጵያዊነት መብታችን መሆኑም መዘንጋት ያለበት አይመስለኝም።
ዕዉነት ዕዉነት እላችኋለሁ ። ዛሬ ወገኖቻችን እየታደኑ በተገኙበት እርምጃ የሚወሰድባቸዉ ፤ ወደ ወህኒ የሚወረወሩት እና ሁሉም ስቃይ በህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ወያኔ በጣዕር ላይ በመሆኑ እርምጃዎቹ ሁሉ የደመነፍስ በመሆናቸዉና በዚያዉ ከዘር ጥላቻ በመነጨዉ ጥላቻዉ ነው።
እናም እላችኋለሁ ግንቦት ወር የወያኔ የምርጫ ድራማ የምናደምቅበት አይሆንም። በሌላ በኩል ግን ወያኔን አሽቀንጥረን ጥለን ለመቻቻል አብሮ ለመኖርና ያገራችንን የወደፊት አካሄድ የምወስንባት ወር ነው መሆን ያለባት ግንቦት ወር።
ይህን ዕዉን ለማድረግ በጥቅማ ጥቅም ተገዝተህ ለዘረኛዉ ቡድን ሰግደህ ያደርክ ሁሉ ወደ ህሊናህ ተመልሰህ ከህዝብ ተቀላቀል።
ለግል ጥቅምህ ተገዥ በመሆን ከዚህም ከዚያም አይደለሁም እያልክ ሌላዉ ሳይሆን ራስህን እያታለልክ የምትኖር የወገንህን ብሶት አስብ ከጎኑም ለመሰለፍ ጊዜ አትዉሰድ።
ባጋጠማችሁ መልካም አጋጣሚ ሥልጣን ላይ ተኮፍሳችሁ ያካበታችሁት ያገር ሃብት የማሰብ ህሊናችሁን ለሸፈነው ዘረኞች የእስካሁኑ ይበቅል ። የያዛችሁትን ለመብላት ከበቃችሁ ከበቂም በላይ ሁሉንም አድርጋችኋል። ይህ ግን እንዳይቀጥል ህዝብ በቃ ብሎአል እና ለሁሉም አይንት ጥፋት ብላችሁ ከምርጥ ዘራችሁ ዉስጥ ያዘጋጃችሁት የጥፋይ ሃይል አያድናችሁምና ለንስኃ ሞት የምትበቁበትን መንገድ ፈልጉ የምነት ድሃዎች ። ህዝብ በቃ ብሎአልና!!!
የጥፋቱን መጠን መቀነስ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለሚል የሆነ ሁሉ ሃላፊነት ነዉ።
ከዚህ በተረፈ ግን ሁሉንም ሥራዉ ያዉጣዉ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37496
Wednesday, 24 December 2014
አስገራሚ ውሎ በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳ
በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ –በላይ ማናዬ
.∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል
.∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያ
ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡
ችሎቱ የተሰየመው ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ወቅት ተከሳሾች በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ የሰጡትን መልስ በተመለከተ 7ኛ ተከሳሽ መልስ በዕለቱ ባለማቅረባቸው አሟልተው እንዲቀርቡ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ስለነበር ይህን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ማብራሪያውን ለመስማት ነበር፡፡
_nየተከሳሾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በጥየቃ ወቅት በተለየ መዝገብ ይመዘገባሉ የተባለውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደብዳቤ መልስ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ‹‹ማረሚያ ቤቱ በሰጠው መልስ እስረኞች ከሌሎች በተለየ የደረሰባቸው ችግር የለም›› ማለቱን ገልጾ ይህንኑ መልስ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉን አስታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በዛሬው የችሎቱ ውሎ ላይ ተከሳሾች ለየት ያለ አቤቱታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል፡፡ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለችሎቱ እንዳስረዱት ደንበኞቻቸው ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ አቶ ተማም አባቡልጉ በታህሳስ 12 ለ13 ቀን 2007 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት ስምንት ሰዓት ጀምሮ ደንበኞቻቸው ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የግል ማስታወሻዎቻቸው፣ ገንዘብ እና በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ እያዘጋጁት የነበረው መቃወሚያና መከራከሪያ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡
‹‹ደንበኞቼ ላይ እየተደረገ ያለው ጉዳይ ለህይወታቸውም የሚያሰጋቸው ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ በሌሊት ፍተሻ ያደረጉባቸው ሰዎች ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት ‹ህገ-ወጥ› ተግባራት ሲፈጽሙባቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስና የደህንነት አባላት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ደንበኞቼ ያውቋቸዋል፡፡ ስለሆነም ፍተሻው የተከናወነው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አልነበረም ማለት ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው የተለየ የስም ዝርዝር ተይዞ ከሌሎች በተለየ መልኩ ነው፡፡ ለአብነት ደንበኞቼ አቶ አብርሃ ደስታና በሌላ የክስ መዝገብ የተከሰሰው አብዱራዛቅ አክመድ ላይ የሆነው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ነው፡፡ ፍተሻው ስለት ነገር አልያም ሌላ ህገ-ወጥ ቁሳቁስ ለመያዝ የተደረገ አለመሆኑን ከተወሰዱት ንብረቶች ማየት ይቻላል›› ሲሉ አቶ ተማም ለፍርድ ቤቱ በደንበኞቻቸው ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አስረድተዋል፡፡
ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ‹‹ማረሚያ ቤቱ መንግስት ዜጎች ታንጸው እንዲወጡ ያሰራው ነው፡፡ ይህን አሰራር ለመጠበቅም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የተለያዩ ስራዎችን ሊሰራ ይችላል፡፡ እየቀረበ ያለው አቤቱታም ከዚህ አኳያ መታየት ያለበት ነው›› ብለዋል፡፡
ጠበቃ ተማም የደንበኞቻቸውን አቤቱታ ከህግ አንጻር ያስረዱ ሲሆን፣ ‹‹በመሰረቱ ፍተሻ ሊካሄድ መቻሉ ላይ አይደለም አቤቱታው፡፡ የተካሄደው ፍተሻ ግን ህገ-ወጥ ነው፤ ምክንያቱም ፍተሻው የተከናወነበት ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ሳይሆን ሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ህገ-ወጥ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ፍተሻው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አይደለም የተከናወነው፡፡ በደህንነቶችና የፌደራል ፖሊሶች ነው ፍተሻው የተደረገው፡፡ ይህም ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎቱም ሆነ ብቃቱ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ይህን መሰል ድርጊት የፈጸሙት አካላትና በማን ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡
ጠበቃ ተማም በተጨማሪ ከደንበኞቻቸው ላይ በፍተሻው ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶችና ማስታወሻዎች እንዲመለሱላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ‹‹የተለየ ከፍተኛ በደል ደርሶብኛል›› በሚል ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበሩት 3ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የጠየቁት የመናገር እድል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል፡፡
በጠበቆቹ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ችሎቱ አስተያየት የሰጠ ሲሆን በተለይ ጠበቃ ተማም አቤቱታውን ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎትም ብቃትም የለውም›› ያሉት አገላለጽ ተገቢ ስላልሆነ እንዲታረሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በቃል የገለጹት የመሐል ዳኛው፣ ‹‹እንዲህ አይነት አገላለጽ ማረሚያ ቤቱ የበቀል እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፋ እንዳይሆን…›› በማለት ሌላ አስገራሚ መነጋገሪያ ከፍተዋል፡፡
ይህን የዳኛውን ንግግር ተከትሎ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የመናገር እድል ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ ለአጭር ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ እናም፣ ‹‹እርስዎ እያሉት ያለው ነገር ተገቢ አይደለም፡፡ በህይወቴ ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ይህንን ስጋቴን ለችሎት እያስረዳሁ ነው፡፡ ግን እርስዎ ‹የበቀል እርምጃ› እንዲወሰድብን ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ በእርግጥ አሁንም የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድብን ማረጋገጫ የለንም፡፡ እሺ ለማን አቤት ይባላል? የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት ከማስረዳት ውጭ ለማን አቤት እንላለን….አሁን እኮ ፍርድ ቤቱ ከማረሚያ ቤቱ ጋር መወገኑን ነው እያየን ያለነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የእኛን አቤቱታ እየሰማ አይደለም፡፡ ከፍርድ ቤት ውጭ ለማን አቤት እንበል?›› ሲል አቤቱታውን በስሜት ውስጥ ሆኖ አስረድቷል፡፡
የሀብታሙን ንግግር አዳምጠው አንደኛ ዳኛ ‹‹እኛ ሳንሆን ህጉ ነው ይህን እንድንል የሚያደርገን›› በማለት አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ መልኩ ቀጥሎ የዋለው ችሎት በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ፍርድ ቤቱ ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት፣ እና መደበኛ ክሱን ለማየት ለታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተጥቷል፡፡
. ...... source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37482
Tuesday, 23 December 2014
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ
ለሰላማዊ ዜጎች ጥያቄ ጥይት መፍትሄ አይሆንም! (ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ)
በባህርዳር ከተማ ለዘመናት የእምነት ቦታ ሆኖ ለአምልኮ አገልግሎት ሲውል የነበረ የህዝብ ይዞታ በማያውቁትና ባልመከሩበት ሁኔታ ባለሀብት እንዲያለማው በከተማው መስተዳድር ተሰጥቷል መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል፡፡ ይህ የኃይል እርምጃ በምንም መለኪያና ሁኔታ፣ ባለሥልጣናት ጥያቄው ያስከትላል ብለው የቱንም ታሳቢ ቢያደርጉ የህግም ሆነ የሞራል መከራከሪያ ሊቀርብለት የማይችል ህገወጥና ኃላፊነት የጎደለው ‹‹መንግሥት ነኝ›› ከሚል አካል የማይጠበቅ ዘግናኝ የአረመኔ ተግባር ነው፡፡
በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ በወያኔ ታጣቂዎች በጥይት የተመቱ መነኩሴ
ከዚህ ባለፈም የከተማ ልማትም ሆነ የመሰረተ ልማት መስፋፋት ህዝብን በማሳመን በህዝብ ተቀባይነት ካላገኘና ለህዝብ ጥቅም ካልሆነ ለማን እንደሚሆን ያልገባቸው እብሪተኛ ባለሥልጣናት ፍርኃትና ሥጋት ወለድ አምባገነናዊ እርምጃ ነው፡፡ በመሆኑም የኃይል እርምጃው እስከዛሬ ‹‹ይህ መንግሥት የማን ነው፣ የቆመውስ ለማን ነው?›› ለሚለው ተደጋጋሚ ጥያቄ ‹‹የሥልጣኑና ለሥልጣኑ ብ ›› መሆኑን በግልጽ ያሳየበትና በህገ አራዊት ስለመመራቱ የማያሻማ ምላሽ የሰጠበት በመሆኑ ትብብራችን እርምጃውን አበክሮ ያወግዛል፡፡ የተወሰደው እርምጃ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በሰጡ ባለሥልጣናትና እርምጃ በወሰዱት ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣ ለተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ካሳ እንዲከፈል ይጠይቃል፣ ለተፈጻሚነቱም ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ጎን በመቆም ይታገላል፡፡
ይህ አምባገነናዊና የጭካኔ እርምጃ በቅርቡ ህዳር 27/07 ዓ.ም በህጋዊና ሠላማዊ መንገድ ለሠላማዊ ሠልፍ የወጡ የትብብራችን አባላትና ደጋፊዎች ላይ የተወሰደውን ዘግናኝ የኃይል እርምጃ፣ በየጊዜውና በተለያዩ ቦታዎች በተናጠል ለተደረጉ ሠላማዊ የህዝብ ተቃውሞዎችና ጥያቄዎች (የሙስሊሙ ማኅበረሰብ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች፣…) ላይ ገዢው ፓርቲ/መንግሥት የተጠቀመውን ተመሳሳይ የኃይል እርምጃ፣ በፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ በነጻው ፕሬስ አባላት፣… በሽብር ሥም በፈጠራ ወንጀል የፈጸመውን፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ በሚገኙ ዜጎች ላይ ‹‹በከፋፍለህ ግዛ›› ስልት እያሳደረ ያለውን የማስፈራሪያ ተግባራት ያስታውሰናል፡፡
በዚህ መሠረት የዚህ እርምጃ ግልጽ መልዕክት ኢትዮጵያዊያን እኔ ፖለቲከኛ ወይም የዚህ ወይም የዚያ ፓርቲ አባል አይደለሁም፣ እኔ ሙስሊም ወይም ክርስቲያን አይደለሁም፣ እኔ አማራ ወይም ኦሮሞ፣ የዚህ ወይም የዚያ ብሄረሰብ አባል አይደለሁም፣ እኔ ተማሪ፣ መምህር፣ የመንግስት ሠራተኛ ወይም ነጋዴ፣ … ከዚህ ከዚያ ማኅበረሰብ ክፍል አይደለሁም፣… አይደለሁምና ጥያቄውና ትግሉ አይመለከተኝም በሚል የወር ተራችንን ከመጠበቅ እንድንላቀቅና ይህን አምገነናዊ ሥርዓት ለማስወገድ በአንድነት ቆመን በጽናት ለመታገል እንድንነሳ ወቅቱ መሆኑን፤ በተናጠል በየተራ በህገ ወጥ እርምጃ የሚደርስብንን በአንድነት ቆመን እስካልመከትን በየተራ የያንዳንዳችንን በር ማንኳኳቱ የማይቀር መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ ዓይነቱ የኃይል እርምጃ እየከፋና እየተስፋፋ፣ ጭቆናው እየከፋና የህዝብ ብሶት እየጨመረ ሲሄድና ከማናችንም ቁጥጥር ውጪ ሲሆን በአገራችን የሚያስከትለውን ፖለቲካዊ ቀውስ፣ ኢኮኖሚያዊ ውድመትና ማኅበራዊ ትርምስ ቀድሞ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ስለሆነም፡-
1ኛ/ ገዢው ፓርቲ የተያያዘው የአፈና መንገድ ለጥያቄዎች መልስ ሊሆን ወይም ትግሉን ሊያቆም እንደማይችል በቅርቡ ከታየው ያለፈው ጁምኣ የቤኒ መስጂድ የሙስሊሞች ተቃውሞ ስልትና አተገባበር ተረድቶ ቆም ብሎ እንዲያስብና ለህዝብ ጥያቄዎች ጆሮውን፣ ለህዝብ ብሶት ልቡን ፣ለመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ለህግ የበላይነት በሩን እንዲከፍት፤
2ኛ/ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የእያንዳንዱ በር እስኪንኳኳ ሳንጠብቅ ይህን ዓይነቱን ኢ-ህገመንግሥታዊና አረመኔያዊ እርምጃ በአንድነት ቆመን እንድናወግዘውና እንድንታገለው፤
3ኛ/ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲ ጥቅምና ፍላጎት የአገርና ህዝብ ጉዳይ የበላይና ቀዳሚ ስለሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከትብብራችን ጋር በጋራ ለመስራት ትብብሩን እንድትቀላቀሉ፤ ጥሪያችንን እያቀረብን፤
በእኛ በኩል ትግሉ የሚጠይቀው ዋጋ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም ከዓላማችን ሳናፈገፍግ ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት በመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስ የተያያዝነውን የጋራ ትግል አጠናክረን ለመቀጠል የገባነውን ቃል እንጠብቃለን!
በዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው ህገወጥ አረመኔያዊ እርምጃ እስከሚያበቃ የጋራ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
source,-http://ecadforum.com/Amharic/archives/13977/
ሕወሓት የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ
የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ
(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::
አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::
በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል::
source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37465
Monday, 22 December 2014
ፌደራል ፖሊሶች ለሚፈጽሟቸው ተጠያቂው ማን ነው?
የቃሊቲ እስረኞች እቃ በፖሊስ ተበረበረ
• የእስክንድር ነጋና የአንዱዓለም አራጌ ማስታወሻዎች ተወስደዋል
Eskinder-Nega-and-Andualem-Aragie1
ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ‹‹ከፌደራል ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ የፌደራል ፖሊሶች እቃቸው በድንገት እንደተበረበረና እንደተወሰደ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 12/2007 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ቃሊቲ እስር ቤትና አካባቢው በበርካታ የፌደራል ፖሊሶች ተከቦ እንደነበር የገለጹት ምንጮቹ ባልታወቀ ምክንያት የሁሉም እስረኞች እቃ በድንገት የተበረበረ ሲሆን በተለይም ፖለቲካ ነክ ጽሁፎች የሰፈሩባቸው ማስታወሻዎችና ሰነዶች መወሰዳቸውን ከእስረኞቹን ጠይቀው እንደተረዱ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ብርበራም የታዋቂው ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከ30 በላይ ገጽ የፖለቲካ ትንታኔ ጽሁፎች፣ እንዲሁም የአንዱ ዓለም አራጌ ማስታወሻዎች መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፖሊስ ማስታወሻዎችንና ሌሎቹንም የእስረኞቹን ንብረቶች እያስፈረመ የወሰደ ሲሆን እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ እስር ቤቱ አካባቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደነበሩ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡
- .source:-//satenaw.com/amharic/archives/
በባህርዳር የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተደረገውን የጅምላ ግድያና ድብደባ እናወግዛለን
አገር በቀል የሆነው፤ የቅኝ አገዛዝና ዘረኛው የወያኔ ሰርአት በባህር ዳር የሚኖሩ ወገኖቻችንን ላይ በትናንትናው እለት ያደረገውን የጅምላ ግድያና ድብደባ አሁንም በታላቅ ቁጭትና ሀዘን ለማየት ተገደናል። በተለይ አካለ ስንኩላንና በእድሜ የገፉ አዛውንት በድብደባ ቆስለው ማየት ምን ያህል ልብ የሚያደማና የስርአቱን ኢሰብአዊነትና ጨካኝነት አሁንም ደግሞ ደጋግሞ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ይህንን ዘግናኝ ወንጀል የፈጸሙት የስርአቱ አራማጆች አንድ ቀን ለፍርድ በሚቀርቡበት አደባባይ በመረጃነት የሚያዝ ይሆናል። ምንም እንኳን የመሳሪያና የዱላ እሩምታውን ቢያወርድበት፤ ቆራጡ የባህር ዳር ህዝብ ይህንን ተቋቁሞ ምሬቱን መግለጽ ብቻ ሳይሆን ከትግል አጋሩ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር፤ ይህንን የበሰበሰ ስርአት ከተከሻው አሽቀንጥሮ የሚጥልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የወያኔ ሰርአት ላለፉት 23 አመታት በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይና ከዚህም የከፉ የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ድርጊቶች በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጽም ቆይቷል። የአንዱ ኢትዮጵያዊ ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥቃት መሆኑን አምነን በአንድነት በመቆም ስርአቱን ለማስወገድ ካልታገልን፤ ወያኔ ስልጣኑን ለማራዘም ወደፊት ከዚህ የከፉ ድርጊቶች እንደሚፈጽም ያሳለፍነው የ23 አመት የመከራ ታሪክ ማሳያ ሊሆነን ይገባል።
ይህን አገር በቀል የቅኝ አገዛዝ፤ ዘረኛና ጨካኝ ሰርአት ለማስወገድ የኢትዮጵያን ሕዝብ መሰረት ያደረገ ሁሉንም አካላት የሚወክልና ትግሉን በአንድ ማእከል የሚመራ ጠንካራ የአንድነት ሃይል መክሮና ተስማምቶ ማቋቋም አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ድርጅታችን በጽኑ ያምናል። በዚህም መሰረት የሽግግር ምክር ቤቱ ይህንን የትግል አስተባባሪና መሪ አካል በጋራ ለማቋቋም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ ሀገር ወዳድና ነጻነት ናፋቂ ወገን ሁሉ ተመሳሳይ ጥረትና ግፊት እንዲያደርግ ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት
. soruce,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37377
Sunday, 21 December 2014
ጋዜጠኞችን በማሠር ኢትዮጵያ አሁንም ከአፍሪካ 2ኛ ሆናለች
መራው አበበ
አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ 2014 አመት በመላው ዓለም 220 ጋዜጠኞች መታሠራቸውንና ቻይና በቀዳሚነት የጋዜጠኞች ሲኦል መሆኗን ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሠር በአለም 4ኛ፣ በአፍሪካ ኤርትራን አስቀድማ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
በኢትዮጵያ በ2014 እ.ኤ.አ የታሣሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ከአምናው ከሰባት እጥፍ በላይ ጨምሮ ወደ 17 ከፍ ማለቱን የድርጅቱ ሪፖርት ይጠቁማል፡፡ በኢትዮጵያ ጦማሪያን ጭምር መታሰራቸውንና ከወትሮው በተለየ በርካታ ጋዜጠኞች መሠደዳቸውንም አመልክቷል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ ጋዜጠኞችን በማሰር ተወዳዳሪ ያልተገኘላት ቻይና፤ 44 ጋዜጠኞችን ዘብጥያ እንዳወረደች በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ አምና በሀገሪቱ ታስረው ከነበሩት 32 ጋዜጠኞች ሌላ ዘንድሮ 12 ተጨማሪ ጋዜጠኞች መታሠራቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ቻይና ለጋዜጠኞች ሲኦል መሆኗን አጠናክራ ቀጥላለች ብሏል፡፡ ሁሉም ጋዜጠኞች የመንግስትን ፖሊሲና አሰራር በመንቀፋቸውና አበክረው በመተቸታቸው ለእስር እንደተዳረጉም ተጠቁሟል፡፡ ኢራን ደግሞ ከቻይና ለጥቃ በሁለተኛነት ተቀምጣለች፡፡
የታሣሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ከዓምናው በአምስት ያህል ቢቀንስም አሁንም ከዓለም ለጋዜጠኞች የማትመች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች ብሏል – ሪፖርቱ፡፡ አምና በኢራን 35 ጋዜጠኞች ታስረው የነበረ ሲሆን ዘንድሮ አምስቱ ተለቀው 30ዎቹ በእስር ላይ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች የታሰሩበት ምክንያት እንደማይታወቅ ተገልጿል፡፡
በአለም ላይ ጋዜጠኞችን በማሠር የሚስተካከላቸው አልተገኘም ተብለው ከተለዩት 10 ሀገራት መካከል ኤርትራና ኢትዮጵያ በ3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን እነሱን በመከተል ቬትናም፣ ሶሪያ፣ ግብፅ፣ በርማ፣ አዘርባጃንና ቱርክ ተጠቅሰዋል፡፡ በኤርትራ ስለታሰሩት 23 ጋዜጠኞች ጥናት ለማድረግ መሞከሩን የጠቆመው ሲፒጄ፤ ለበርካታ አመታት የታሠሩ ጥቂት ጋዜጠኞች በህይወት መኖራቸውን ከማረጋገጡ ውጪ በምን ምክንያት እስከዛሬ እንደታሠሩ ለማወቅ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ ከቀደመው አመት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ጋዜጠኞችን እንዳሰሩ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ግብፅ የአልጀዚራ ጋዜጠኞችን ጨምሮ 12 ጋዜጠኞች ማሠሯን ጠቅሶ የታሠሩበት ምክንያት ግን አልታወቀም ብሏል፡፡ ጋዜጠኞችን በማሰር በ8ኛ ደረጃ የተቀመጠችው በርማ፤ “መንግስትን ተቃውማችኋል” በሚል 10 ጋዜጠኞችን ያሰረች ሲሆን፤ አብዛኞቹም የ10 አመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡
በአዘርባጃን 9 ጋዜጠኞች ወህኒ ቤት የሚገኙ ሲሆን ዘንድሮ ብቻ አራት የማህበራዊ ሚዲያ “የመብት ተሟጋቾች” በሀገሪቱ ያለውን ሙስናና የሠብአዊ መብት ጥሰት በመተቸታቸው ከያሉበት ተለቃቅመው ለእስር መዳረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ከሁለት አመት በፊት ጋዜጠኞችን በማሠር በ1ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ቱርክ፤ ዘንድሮ በርካታ ጋዜጠኞችን ከእስር በመልቀቅ ደረጃዋን አሻሽላ፣ 10ኛ ሆናለች፡፡ በአሁን ሰአት በቱርክ 7 ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙም ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በአህጉር ደረጃ ለጋዜጠኞች ተስማሚ ሆናለች ተብላ የተጠቀሰችው አሜሪካ ነች፡፡ የኩባና የሜክሲኮ መንግስታት እያንዳንዳቸው አንድ ጋዜጠኛ ከማሠራቸው ውጪ አህጉሪቱ ሠላማዊ ነች ብሏል – ሪፖርቱ፡፡
የCPJ ሪፖርት እንደሚጠቁመው፤ ከ2012 ወዲህ በመላው ዓለም 220 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን፤ 132ቱ መንግስትን ተቃውማችኋል ወይም ሽብርተኛ ናችሁ በሚል ለእስር ሲዳረጉ፣ 45ቱ የታሠሩበት ምክንያት አይታወቅም ተብሏል፡፡ ከታሣሪዎቹ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚሠሩ ጋዜጠኞች እንደሆኑ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ቁጥራቸው 83 እንደሚደርስም ጠቅሷል፡፡ የተቀሩት ተቀጣሪ ያልሆኑ እንዲሁም የሬዲዮ፣ ዌብሣይት፣ ቴሌቪዥንና ማህበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች እንደሆኑ ገልጿል፡፡
የታሳሪ ጋዜጠኞችን ቁጥር በየዓመቱ እያበራከቱ ነው ተብለው ከተጠቀሱት ሃገራት መካከል ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ቻይና፣ ባንግላዲሽ፣ ታይላንድ፣ አዘርባጃን፣ ባህሬን፣ ግብፅ፣ እስራኤልና ሳውዲ አረቢያ እንደየቅደም ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን ዘንድሮ አንድም ተጨማሪ ጋዜጠኛ ባለማሰራቸው ከተጠቀሱት መካከል ካሜሩን፣ ስዊዘርላንድ፣ ሜክሲኮ፣ ኩባ፣ በርማና ቤላሩስ ይገኙበታል፡ ፡ ሲፒጄ እ.ኤ.አ ከ2009 እስከ 2014 “በአለማቀፍ ደረጃ የጋዜጠኞች ሁኔታ ምን ይመስላል?” በሚል ባካሄደው ጥናት፤ 404 ጋዜጠኞች በደረሰባቸው ጫና የትውልድ ሃገራቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደተገደዱ አረጋግጧል፡ ፡ በእነዚህ ዓመታት ጋዜጠኞች በብዛት ከተሰደዱባቸው ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ4ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፣ 41 ጋዜጠኞች ሃገር ለቀው ወጥተዋል ተብሏል፡፡ 76 ጋዜጠኞችን ለስደት በመዳረግ ፊትአውራሪ የሆነችው ደግሞ ኢራን ናት፡፡ ሶርያ 44፣ ሶማሊያ 42 ጋዜጠኞች እንዲሰደዱ በማድረግ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኤርትራ 29፣ ኩባ 18፣ ፓኪስታን 15፣ ሲሪላንካ 14፣ ሩዋንዳ 11፣ ጋምቢያ 10 ጋዜጠኞች ከሃገር እንዲሰደዱ በማድረግ ከ5-10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘውታል፡፡ ስደተኛ ጋዜጠኞች የተቀበሉ ሃገራት ተብለው ከተለዩ 10 ሃገራት መካከልም ኢትዮጵያ የምትገኝ ሲሆን ዘጠኝ ስደተኞች በመቀበል ከዓለም በ9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ አሜሪካ፣ ኬንያ፣ ቱርክ፣ ፈረንሳይ፣ ኡጋንዳ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ሱዳን፣ እንግሊዝ ከ1-8ኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ሊባኖስ 10ኛ ሆናለች፡፡ አፍሪካ ብዙ ጋዜጠኞች ከተሰደዱባቸው አህጉራት ቀዳሚዋ ስትሆን 165 ጋዜጠኞች በተጠቀሱት አመታት አገራቸ ውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ መካከለኛው ምስራቅና የእስያ አገራት ይከተላሉ ተብሏል፡፡ በጥናቱ እንደተጠቆመው፤ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ጋዜጠኞች እስራትና ክስ ሽሽት ከሃገራቸው የወጡ ሲሆን የስደት አገር ከገቡ በኋላ 21 በመቶ ያህሉ ብቻ በሚወዱት የጋዜጠኝነት ስራ የመቀጠል እድል አጋጥሟቸዋል፡፡
ከተሰደዱት ጋዜጠኞች ውስጥ ወደ ትውልድ ሃገራቸው መመለስ የሚፈልጉት 5 በመቶ ብቻ እንደሆኑም ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያን ያላካተተው “ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን” ሪፖርት በአለማቀፍ ደረጃ ጋዜጠኞች በሙያቸው የሚጋፈጧቸውን ጫናና ተግዳሮቶች እየመዘገበ በየዓመቱ ሪፖርት የሚያቀርበው “ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን” (Reporters without Borders) ዘንድሮ (በ2014) በአለም ዙሪያ 66 ጋዜጠኞች መገደላቸውንና 119 ታፍነው መወሰዳቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ መቀመጫውን በፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው ቡድኑ፤ ሶርያን “የጋዜጠኞችን ህይወት የበላች ሃገር” በማለት በቀዳሚነት አውግዟታል፡ ፡ በጦርነትና በእርስ በርስ ግጭት በምትታመሰው ሶርያ ዘንድሮ ብቻ 15 ጋዜጠኞች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
soyrce,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37421
Saturday, 20 December 2014
**የአንዱ ለቅሶ ለሌላው ደስታ እየሆነ ነው።**
ኢህአዴግ የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ ይበረግጋል። የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። ሲቃወሙት የበረሃ ወባው ይነሳበታል። ከድንጋጤው የተነሳ ይበረግጋል። ይደነብራል። ለምን? ቢባል በደም የተለወሰ ፓርቲ ስለሆነ ነው። ኢህአዴግ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ነፍስ ያላጠፋበት ስፍራ የለም። በመሀል አገር ክቡር የሰው ልጆችን ገሏል። የሚደመደም ነገር ባይኖርም በበላዮቹ ትዕዛዝ ኢህአዴግ ባፈሰሰው ደም መጠን ጠላት አፍርቷል። ወዳጁና አጋሩ ጠብመንጃና በደም የለወሳቸው አባላቱ ብቻ ናቸው። ሌላ ወዳጁ እንዳሻው የሚዘራው የአገሪቱ ሃብት ነው። የህዝብ ሃብት ህዝብን ለማፈን ማዋል!! ሌላው ስጋቱን ለመጥቀስ እንጂ ከዝርፊያ ጋር የተቆራኘውን ታሪኩን ለመዘርዘር አይደለም። ስለዚህ ህዝብ ሲቃወም ያጥወለውለዋል። ይጓጉጠዋል። አውሬ ይሆናል። ህግና ስርዓት አፍርሶ የጫካ ደንብ ይተገብራል። ባጭሩ ይገላል!!
ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ገዢ ነኝ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብን ያስቀየሙ፣ ያሳዘኑና፣ ያሳፈሩና ቂም ያስቋጠሩ ተግባራትን በግልጽና “በድብቅ ግን የሚታወቅ” አከናውኗል። በተለያዩ ጊዜያት በተግባሩ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን ሃይል ተጠቅሟል። አልሞ ተኳሾችን አሰማርቶ ዜጎችን ልባቸውና ግባራቸው አየተመታ እንዲገደሉ አድርጓል። የሚችለውን ያህል አስሯል። ገርፏል። ራሱ ክስ መስርቶ ራሱ እየፈረደ ወህኒ ወርውሯል። ነጻ ፕሬስን ሰቅሎታል። ሃሳብን በነጻ ማራመድን በህግና ህግ በማይጠቀስበት አግባብ አግቷል።
አሁን ጎንደር ላይ የተነሳውን የተቃውሞ አመጽ ተከትሎ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በጥበብ ከማስተናገድ ይልቅ ብረት አንስቶ መግደልን መርጧል። ኢህአዴግ በገደለ ቁጥር አገሪቱ ስጋቷ እየጨመረ፣ የህዝብ ስሜት እየተበላሸ ነው። ይህ እንደኢትዮጵያዊ ያስጨንቀናል። ኢህአዴግ የዘራው የቂም ዘር በየአቅጣጫው ፍሬው እየጎመራ መሄዱ ያሳዝነናል። ከሁሉም አቅጣጫ መፍትሔ የሚፈልግና ችግር የሚያረግብ አይታይም። አገሪቱ አስተዋይ በማጣቷ በስጋት ደመና እየነፈረች ነው። የአንዱ ለቅሶ ለሌላው ደስታ እየሆነ ነው። ከዚህ በላይ የሚያስጨንቅ ምን አለ? ኦሮሞው፣ አማራው፣ ደቡብ ክልል ያሉ ዜጎች፣ ኦጋዴን፣ ሶማሌ፣ ሁሉም ጋር ብሶት አለ። የኑሮ ችግር የጠበሳቸው የበይ ተመልካቾች መሯቸዋል። ያልመረራቸው ቢኖሩ ከቁጥር የማይገቡ ባለጊዜዎች ብቻ ናቸው። ይህም ታላቅ ስጋት ነው!!
ከሰብኣዊ
ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ!
በባህርዳር ዋይታ ሆነ!
በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡
አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡
“ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ ቀበሌ፣ ወሰንና የምክርቤት ስም ጠቅሶ የተፈጠረውን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡
“የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡ ህዝቡም “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል” በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡”
ግድያውንና ድብደባውን በተመለከተ “የክልሉ መስተዳድር ድርጊቱን እንደፈጸመ አድርገው የሚወጡት ዘገባዎች ትክክል አይደሉም፤ መስመርም ያስታሉ፤ ዋንኞቹን ወንጀለኞች ከደሙ የነጹ ያደርጋቸዋል” በማለት ቅሬታቸውን ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሰጡ ወገኖች “በየትኛውም የአገሪቱ ክልሎችም ሆነ ከተሞች ለሚፈሰው ደምና ለሚጠፋው ሕይወት ግምባር ቀደም ተጠያቂው ህወሃት/ኢህአዴግ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል” ሲሉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ “በቁጥጥር ሥር ውሏል” የተባለው የሙስሊሙ ተቃውሞ በድንገት መካሄዱ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ የተካሄደውን ተቃውሞ አስመልክቶ የተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች በተለይም የሙስሊሙን ጉዳይ በመከታተል ይፋ የሚያደርጉ መገናኛዎች እንዳስታወቁት ተቃውሞው የተካሄደው ኢህአዴግ ከሚጠብቀውና ከሚገምተው ውጪ ነበር፡፡ እንደወትሮውም የጥሪ ማስታወቂያና ቅስቀሳ አስቀድሞ አልተካሄደም በማለት ዘግበዋል፡፡ ተቃውሞው ውጤታማ፣ ግቡን የመታና የተጠናከረ ቅንብር እንደነበረው የታዘቡ ይናገራሉ፡፡
ኢህአዴግ በእሁድ የፖሊስ ፕሮግራሙ የሚሰጠው “ልማት ተኮር” የፖሊስ ማስተባበያ “ምርመራ ውጤት በተስፋ” ይጠበቃል፡፡ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ያገኘናችው ምስሎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል:: .
. source,-http://www.goolgule.com/eprdf-killed-ethiopians-in-bahirdar/
Friday, 19 December 2014
በባህርዳር አምስት ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት ሞተዋል
አምስት ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት ሞተዋል፣ የባህርዳር ህዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ጥረት እያደረ ቢሆንም ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች አምስት ያህል ወጣቶች እንደቆሰሉ ተገልጾአል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ባህርዳር ከተማ ውስጥ 04 ቀበሌ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የጥምቀት ታቦት ማደሪያ ለባለሀብት ይሰጣል መባሉን ተከትሎ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጸዋል፡፡Protest
ምንጮቹ እንደገለጹት እጅግ በርካታ ህዝብ አደባባይ የወጣ ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ በእምነታቸው እየተደረገባቸው የሚገኙትን ጣልቃ ገብነቶችና ሌሎቹንም ስርዓቱ እየፈጠራቸው የሚገኙትን ችግሮች የሚቃወሙ መፈክሮች እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡
ህዝቡም ‹‹በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል›› በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
(Click here to watch video) የባህርዳር ህዝብ ተቃውሞውን እየተቀላቀለ ነው
በእውቀት ላይ የተመሰረተ አሸናፊው ህዝብ ነው
በሰላማዊ ሰልፈኛ ላይ ዱላ መሰንዘር ሽንፈት ነው›› እስክንድር ነጋ
ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡
አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ ባለመሳሪያው ዱላውን ከሰነዘረብህ አሸናፊው አንተ ሰላማዊው ታጋይ ነህ፡፡ በትብብሩ ሰልፍ ላይ የሆነው ይኸው ነው፡፡ አሁን ሰላማዊ ትግሉ ፍጹም ሰላማዊነቱን እንደጠበቀ መጠናከር ነው ያለበት፡…፡ ሰላማዊ ትግል ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ፤ እሱም ሰላማዊ ሆኖ መዝለቅ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
Eskinder_Nega_
ሰላማዊ ታጋይ ይሰደባል፣ ይደበደባል፣ ይሞታልም፡፡ ግን ደግሞ ሰላማዊ ታጋይ አይሳደብም፣ አይደባደብም፣ አይገድልም፡፡ ይህ ከሆነ ሰላማዊ ትግል ያሸንፋል፡፡ አምባገነኖች ሰላማዊ ታጋዮችን በተለያየ መንገድ ከሰላማዊነታቸው እንዲወጡ ሊገፋፏቸው ይሞክራሉ፤ ስሜት ውስጥ በመክተትም የኃይል በትራቸውን ለማሳረፍ ይቋምጣሉ፡፡ ይህ ሴራ ሰላማዊ ታጋዮችን ሊያዘናጋቸው አይገባም፡፡
በቀደም በተደረገው ሰልፍ ላይ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ መፈጸሙ ለተደብዳቢዎቹ ሳይሆን ሽንፈቱ ለደብዳቢዎቹ ነው፡፡ በደረሰው ድብደባ ባፍርም፣ ባዝንም በውጤቱ ግን ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ሰላማዊ ሰልፈኞች ሰላማዊነታቸውን አሳይተዋልና! በሰልፉ ወቅት ድብዳባ እና እስር የደረሰባቸውን የመብት ጠያቂዎች ሁሉ በርቱ ልላቸው እፈልጋለሁ፡፡ ባደረጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጣም ኮርቻለሁ፡፡ሰላማዊና ህጋዊ ትግላችሁን ቀጥሉ ማለትም እፈልጋለሁ!
‹‹አሸናፊው ህዝብ ነው›› አንዱዓለም አራጌ
ግለሰቦች የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዚያው ልክ የሚሳሳቱትም ግለሰቦች ናቸው፡፡ የግለሰቦች አስተሳሰብ ህዝባዊ ከሆነ ግን በአሸናፊው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ ምክንያቱም አሸናፊው ህዝብ ነው፤ አሸናፊው ሀገር ነው፡፡ የሁላችንም አሸናፊነት የሚገለጸው ሀገር ከፍ ከፍ ስትል ነው፡፡ ስለዚህ ስራችን ሁሉ ሀገርን ከፍ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡
በትብብሩ ፓርቲዎች በተጠራው ሰልፍ ላይ የሆነውን ሰምቻለሁ፡፡ በሆነው ነገር አዝኛለሁም፤ ኮርቻለሁም፡፡ ያዘንኩት በደረሰው ድብደባ እና እስር ነው፡፡ የኮራሁት ደግሞ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊጠይቁ በድፍረት አደባባይ በወጡት ታጋዮች ነው፡፡ በእነዚህ ታጋዮች የእውነት ኮርቻለሁ፡፡
በቀጣይ ፓርቲዎች በአጋርነት መስራት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ፓርቲዎች ከእጩ አቀራረብ ጀምሮ ተቀራርበው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ተቀራርበው ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡ በተረፈ ግን በትብብሩ ሰልፍ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ጥንካሬን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ፡፡ ትግላቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ እላለሁ፡፡
‹‹ቃላችሁን ጠብቃችኋልና ክብር ይገባችኋል፣ ኮርቸባችኋለሁም!›› የሺዋስ አሰፋ
ሰማያዊ ፓርቲ መርህ አለው፡፡ ያመነበትን ነገር ህጋዊና ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንደሚፈጽም አውቃለሁ፡፡ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ላይም የሰማያዊ ወጣቶችና ሌሎችም ቃላቸውን ጠብቀው ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ በእውነት በጣም ኮርቸባቸዋለሁ፡፡ እንደሁሌውም ቃላቸውን ጠብቀው ለህዝቡ መብት መቆማቸውን አይቼ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔ በእስር ላይ ብሆንም ሌሎች የትግል ጓዶቼ ባደረጉት ነገር በጣም ነው ደስ የተሰኘሁት፡፡
ድብደባውና እስሩ የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ኢህአዴግ በህዝብ ፊት ኪሳራን ነው ያተረፈው፡፡ ሰላምን እና ህግን ማስጠበቅ የሚቻለው በልምምጥ ሳይሆን ትክክለኛ መስመርን በመከተል ነው፡፡ በዚህ መሰረት የትግል ጓዶቼ ትክክለኛ መስመር ላይ እንደሆኑ ይገባኛል፡፡ በርቱልኝ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ መሰል ሰላማዊነት ነው አምባገነኖችን ማሸነፍ የሚቻለው፡፡
. source,-ethioforum.org/amharic/በሰላማዊ-ሰልፈኛ-ላይ-ዱላ-መሰንዘር-ሽንፈ/
Thursday, 18 December 2014
ንግድ ባንክ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርን ከስራ አገደ
የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዳር ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ በደረሰበት እስር ምክንያት ከስራው ታገደ፡፡ እያስፔድ ተስፋዬ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ታስረው ከነበሩት አመራሮች መካከል አንዱ ሲሆን ከእስር ከተፈታ በኋላ ታስሮ ስለመቆየቱ ማስረጃ ቢወስድም ለ15 ቀን ከስራ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
‹‹ታስሬ መቆየቴን የሚያሳይ ማስረጃ ወደምሰራበት ቅርንጫፍ ስወስድ ከእኛ አቅም በላይ ስለሆነ ወደ ዲስትሪክት ውሰድ ተባልኩ፡፡ ዲስትሪክት ስወስድ የንግድ ባንክ ዳይሬክተር የሰው ኃይል አስተዳደር ማመልከቻና ታስረህ የቆየህበትን ማስረጃ አስገባና እነሱ ወደ ስራ ገበታህ ተመለስ ካሉህ ነው የምትመለሰው፤ እነሱ ተመለስ እስኪሉህ ድረስ ግን ወደ ስራ ገበታ መመለስ አትችልም አሉኝ፡፡ ባሉኝ መሰረትም ለሰው ኃይል አስተዳደር ደብዳቤና ከፖሊስ ጣቢያ የተሰጠኝን ማስረጃ ወሰድኩ፡፡ ዳይሬክተሩ እስኪያየው ድረስ ተብሎ አንድ ቀን ቀጠሮ ተሰጠኝ›› የሚለው እያስፔድ በቀጠሮው መሰረት ሲሄድ ጉዳዩ ለቅሬታ ሰሚ ኮሜቴ እንደተላከ፣ ነገር ግን የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባሎች ስልጠና ላይ በመሆናቸው ለ15 ቀን ስራ መግባት እንደማይችልና ለታገደበት ቀናትም ደመወዝም እንደማይከፈለው እንደተገለጸለት ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድቷል፡፡
ቀደም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ አቶ ወሮታው ዋሴ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባረሩ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
.source,-http://ecadforum.com/Amharic/archives/13941/
Wednesday, 17 December 2014
የዞን 9 ጦማርያን ፍርድ ቤት
የዞን 9 ጠበቃን ደብዳቤ ይዘናል
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከኦነግ እና ግንቦት 7 ጋር አብረው ሰርተዋል:: የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ወጣት ጦማርያን ፍርድ ቤት በድጋሚ ቀርበው ነበር:: የቀረቡበት ምክንያት… የተጠቀሰው የወንጀል ዝርዝር እና አንቀጹ ተዛማጅ ባለመሆናቸው የጦማርያኑ ጠበቃ በክሱ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር:: ጠበቃው ለፍርድ ቤት ካቀረቡት ደብዳቤ ውስጥ ገጽ 2 እና 3ትን ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል::
በፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ በሕቡዕ በመደራጀት፣ የወንጀል አድማ ስምምነት በማድረግ፣ በውጪ ኃይሎች በመደገፍና በማህበራዊ ድረ-ገፆች በመጠቀም እንዲሁም መንግሥት
አሸባሪ ብሎ ከሚጠራው ግንቦት 7 እና ኦነግ ጋር በመተባበር ሁከትና ብጥብጥን ሊያስነሱ ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የሽብር ወንጀል ክስ በመሠረተባቸው በእነሶሊያን ሽመልስ የክስ መዝገብ ላይ አሁንም በድጋሚ መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ በሚል; ከላይ በተገለጸው አይነት የተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታቸው በፅሁፍ አቅርበዋል።
source,-http://ethioforum.org/amharic/
Tuesday, 16 December 2014
∙የስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ
በላይ ማናዬ
ካዛንቺስ በተለምዶ እንደራሴ በተባለው ቦታ ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ረፋድ ላይ የሆነው እንዲህ ነው….
በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ እና በሌሎች 8 ፓርቲዎች ስምምነት የተመሰረተው የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የትግል መርሃ-ግብር ማሳረጊያ ሊደረግ በነበረው የ24 ሰዓት የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ ያሉ ሁኔታዎችን ለመዘገብ የሰልፉ መነሻ በሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሰልፉ ይጀምርበታል ከተባለው ጊዜ መዘግየቱን አስመልክቶ ከቢሮ ወጣ ብዬ ሁኔታውን ለመቃኘት እየሞከርኩ ነበር፡፡ ድባቡ ፍጹም ዝብርቅርቁ የወጣ ነበር፡፡ ሰልፍ ለመውጣት የወሰኑት ሰዎች በቢሮው ውስጥ መሰናዷቸውን እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ከቢሮ ውጭ ያሉ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ኃይሎች ደግሞ ቁጥራቸው በየደቂቃው እየጨመረ አካባቢውን መክበብ ተያይዘውት ነበር፡፡
ሁኔታውን በአንክሮ ለተመለከተው በደቂቃዎች ውስጥ ‹ፍጥጫ› ሊጀመር እንደሚችል አመላካች ነበር፡፡ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የእውቅና ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብቻለሁ፣ ስለሆነም ሰልፉን ለማድረግ ወስኛለሁ ሲል መንግስት በበኩሉ ሰልፉን ‹ፈቃድ አልሰጠሁትም› ሲል አስታውቆ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ትብብሩ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ‹ማሳወቅ› እንጂ ‹ማስፈቀድ› አይጠበቅብኝም ሲል አዋጅ ጠቅሶ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡
በዚህ አለመግባባት ውስጥ ተሁኖ ነበር የአዳር ሰልፉ ሊካሄድ ሽርጉድ ይባል የነበረው፡፡ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ሰልፉ ከሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ውስጥ ተጀመረ፡፡ የሰልፉ አጀማመር በራሱ የሚገርሙ ነገሮች ነበሩት፡፡ ባላሰብኩት ፍጥነት ቢሮ ውስጥ የነበሩት ሰዎች በአንዴ ሰብሰብ ብለው ቀጥታ ከበር እንደወጡ መፈክሮችን እያሰሙ በፈጣን እርምጃ ወደፊት ተስፈነጠሩ፡፡ እርምጃየን በእነሱው ፍጥነት ልክ አስተካክየ መቅረጸ-ድምጼን አበራኋት፡፡ ‹‹ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት!….›› እያሉ መፈክሩን አስተጋቡት፡፡
ፖሊሶች በሰልፈኞች ፍጥነት ግር የተሰኙ መሰሉ፡፡ ሰልፈኞቹ በጣም ብዙ ፖሊሶች በተሰደሩበት መንገድ ፊት ለፊት ቀጥታ ገሰገሱ፡፡ ይህኔ ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ተቁነጠነጡ፡፡ ሰልፈኞች መፈክራቸውን ለወጡ፤ ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው! ፖሊስ የህዝብ ነው! ፖሊስ የህዝብ ነው!›› እያሉ ለፖሊሶች መልዕክት ለማስተላለፍ ሞከሩ፡፡ ይህኔ ሁኔታዎች ከመቅጽበት ተለዋወጡ፡፡ እዛ የነበረው የ‹ፀጥታ ሰራተኛ› በሙሉ እንደንብ ሰልፈኞች ላይ ሰፈረ፡፡ እንደደነበረ ፈረስ ያገኙትን መርገጥ ጀመሩ፡፡ በሰልፈኞች ላይ የሆነው ሁሉ በእኔም ላይ ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ዱላ ካረፈብኝ በኋላ ያለውን የዱላ ብዛት አሁን አላስታውስም፡፡ ብቻ ዘግናኝ ነበር!
በእርግጠኝነት በሂደቱ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ቀድሜ ብገምትም፣ የሆነው ግን ከግምቴም በላይ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነበር፡፡ ሴቶች እና እድሜያቸው ከ70 በላይ የሆኑ አዛውንቶች ርህራሄ አልተደረገላቸውም፡፡ እንዲያውም በእነሱ ላይ ሳይበረታ አልቀረም፡፡ ያ ሁሉ ፖሊስና ‹ሌሎች የፀጥታ ሰራተኞች› እንደአሸን የፈሉ ነበሩ፡፡ አንድም ዱላ ሳይሰነዝሩ ሰልፉን ማገት በተቻላቸውም ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ትዕዛዝ ይመስላል፤ ዜጎችን ደብድብ የሚል ትዕዛዝ! ያሳፍራል፣ ያሸማቅቃል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አቧራ ላይ ተጥለው ተደበደቡ፡፡ ሴቶች ሆዳቸውን ተረገጡ፡፡ አዛውንቶች ዘለፋ ከተሞላበት ኃይለ-ቃል ጋር ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ ጋዜጠኛ ሰልፍ ላይ ተገኝተህ መዘገብ አትችልም ተብሎ ተቀጠቀጠ፡፡ አቶ ኤርጫፎ ኤርደሎ እና አቶ ቀኖ አባጆቭር (አባዬ) ተይዘው ከእኛው ጋር ሲንገላቱ ሳይ በእኔ ላይ የደረሰውን ሁሉ ረሳሁት፡፡ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሚሆኑ ‹የጸጥታ ሰራተኞች› የአሳፋሪው እርምጃ ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በእርግጥ እነ አባዬ ስለእኛ እንጂ ስለራሳቸው አልተሰማቸውም፡፡ እኛ ደግሞ በእነሱ ላይ ስለሆነም የበለጠ እናዝን ነበር፡፡
ይህ ሁሉ ድርጊት በካዛንቺስ እንደራሴ አካባቢ ከመሆኑ ከደቂቃዎች በፊት ብዙ ዜጎች በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ስፍራዎች እየተያዙ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ መንግስት የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ዜጎችን ለማፈን ቆርጦ እንደተነሳ ተገነዘብኩ፡፡ በዕለቱ የሆነው ተራ እስር አልነበረም፤ አፈሳ ነበር የተደረገው፡፡ ጅምላ እስር ነበር የተፈጸመው፡፡ ካዛንቺስ እንደራሴ አካባቢ የሆነው ግን በኃይልና በድብደባ የታጀበ ነበር፡፡ በድብደባ እራሱን ስቶ የቆየው ወጣት አቤል ኤፍሬምን ጨምሮ ብዙዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን በመኪና እንደእቃ እንድንጫን ተደርገን ካዛንቺስ አካበቢ ወደሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተጋዝን፡፡ ጣቢያ እንደደረስን በአንድ ቦታ እንድንሰበሰብ ተደርገን በፎቶ እና ቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ ተደረገብን፡፡ የሚገርመው ራሱን ስቶ ወድቆ የነበረው አቤል ሳይቀር በዚያ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ህክምና ሳያገኝ ቀረጻው ይደረግበት ነበር፡፡ ግራ ቀኜን ዞር ዞር ብዬ የተያዙ ሰዎችን አስተዋልኩ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ የተለያዩ የፓርቲ አመራሮች ተይዘዋል፡፡ አንዳንድ በዚያ ሲያልፉ የተገኙ፣ ስለጉዳዩ ምንም የማያውቁ ሰዎችም አብረው ተጀምለው ተይዘዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል በሁኔታው ተደናግጠው የሚያለቅሱ ሰዎች ይገኙበት ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሰልፍ ይሁን ሌላ የሚያውቁት ጉዳይ አልነበረም፡፡ እንዲሁ በቦታው ስለተገኙ ብቻ የተያዙ ነበሩ፡፡
ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እያለን ከመስቀል አደባባይ የተያዙ ሰዎችም በጣቢያው እንደሚገኙ ተገነዘብኩ፡፡ በጣም ብዙ ፖሊሶች ግቢውን ሞልተውታል፡፡ ብዙዎች ሰልፈኞችን ይሳደባሉ፤ አንዳንዶች አሁንም ለመደባደብ ሲቋምጡ አስተዋልኩ፡፡ ገረመኝ! ከመደብደብ የሚገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ቀደም ብሎ በተያዝንበት ቦታ ላይ ብዙ ከተደበደብን በኋላም ቢሆን ድብደባው እንዲቆም ትዕዛዝ የሰጡት የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዘውዴን በዓይኔ ፈለኳቸው፡፡ ግን ላገኛቸው አልቻልኩም፤ የእውነት ከድብደባው የሚገኘውን ትርፍ ማወቅ እፈልግ ነበር፡፡ ፍርሃቴ ልበለው አልያ ድንጋጤዬ ብን ብሎ ጠፍቶ ስለነበር ማናቸውንም አይነት ጥያቄ ልጠይቃቸው እፈልግ ነበር፡፡ የእውነት በወገኖቼ መካከል መገኘቴን እንኳ እጠራጠር ነበር፡፡ እንዴት ሰው አንዲት ጠጠር እንኳ በእጁ ሳይዝ፣ በሰላም ድምጹን ስላሰማ ብቻ ይህን ያህል ድብደባ በራሱ ወገኖች፣ በመንግስት ኃይሎች ይደርስበታል?
ስድስተኛ ብዙም አልቆየንም፤ የቪዲዮ እና የፎቶ ቀረጻው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ወደሌላ ፖሊስ ጣቢያ እንድንዛወር ተደረግን፡፡ የደረስንበት ፖሊስ ጣቢያ ፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ ነበር፡፡ በዚህ ፖሊስ ጣቢያ ደርሰን ትንሽ ጊዜ እንደቆየን ቃላችንን እንድንሰጥ ተደረግን፤ ድጋሜ ፎቶ እንድንነሳ ሆነ፣ አሻራም ተነሳን፡፡ ይህን አድርገው ወደተለያዩ ክፍሎች ካጨቁን በኋላ ምሽት ላይ እንድንወጣ ታዘዝን፡፡ በዚህ ጊዜ በታሳሪዎች መካከል የተለያዩ አስተያየቶች ይሰጡ ጀመር፡፡ አንዳንዱ ልንፈታ ነው ሲል ሌላው ደግሞ ወደ ካምፕ ሊወስዱን ነው ይል ነበር፡፡ ቀሪዎች ደግሞ ወደሦስተኛ ፖሊስ ልንወሰድ እንደሆነ ግምታቸውን ሰነዘሩ፡፡ እነዚህኛዎቹ ልክ ነበሩ፡፡ ጉዙው ወደ ሦስተኛ ነበር፡፡ በፖለስ መኪና እና ሞተር ሳይክል ታጅበን፣ የሳይረን ድምጽ በሚያሰማ ሞተረኛ መሪነት ሦስተኛ ፖሊስ (የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት) ተወሰድን፡፡
ወደሦስተኛ ፖሊስ እንድንዛወር የተደረግነው ታሳሪዎች ከመስቀል አደባባይ የተያዙትን አይጨምርም፤ ቁጥራችንም 44 ነበርን፡፡ ሌሎቹ እስከተፈቱበት ዕለት ድረስ እዚያው ፖፖላሬ ጣቢያ ቆይተዋል፡፡ ሦስተኛ ፖሊስ እንደደረስን በሁለት እንድንከፈል ግድ ሆነ፡፡ በአመራር ደረጃ ላይ ያሉት ወደቀዝቃዛ ክፍል (በረዶ ቤት) እንዲገቡ ሲደረጉ፣ ሌሎቹ ደግሞ በተለያዩ ክፍሎች (ጨለማ ክፍልን ጨምሮ) እንድንገባ ተደረግን፡፡ በዚያው በህዳር 27/2007 ዓ.ም ዕለት የሦስተኛ ፖሊስ ቆይታችን አሃዱ ተባለ፡፡ (በነገራችን ላይ አብዛኞቻችን ታሳሪዎች ለ24 ሰዓታት ያህል ምግብና ውሃ በአፋችን አልዞረም ነበር፡፡)
የስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ
ሦስተኛ ፖሊስ አሁን ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት ስፍራ ነው፡፡ ቦታው ድሮ በሚታወቅበት ገጽታው ሳይሆን በቅርቡ በተገነባው ዘመናዊ ህንጻው ተጀቡኖ በግርማ ሞገስ የሚታይ ነው፡፡ ይህ ቦታ በፌደራል ፖሊስ የማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያን ተጎራብቶ የሚገኝ ነው፤ (አንዳንዶች ከማዕከላዊ ጋር በምድር ዋሻ ይገናኛል ይላሉ፤ ይህን በተመለከተ እንደ ቀልድ ከእስር በወጣንበት ቀጣይ ቀን ሞባይል ስልኬን ልወስድ ወደጣቢያው ባመራሁበት ወቅት ለመርማሪዬ ፖሊስ በቀልድ መልኩ ጥያቄ አንስቼለት ነበር፡፡ መርማሪው ‹‹ማዕከላዊ እና እኛ አንገናኝም!›› ነበር ያለኝ በጥያቄየ ግር በመሰኘት አተያይ እያየኝ)፡፡ ሦስተኛ ፖሊስ በህንጻው ዘመናዊ ይሁን እንጂ በአሰራር ግን ብዙ ገራሚና አሰቃቂ ድርጊቶችን የሚያስተናግድ ቦታ መሆኑን በቆይታየ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡
ወደ ጉዳዬ ስመለስ፣ ሦስተኛ የገባን ዕለት (ህዳር 27) በሌሊት ምርመራ ሲደረግብን ነበር ያደርነው፡፡ በፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ የሰጠነውን ቃል በመድገም ሙሉ ማንነታችን ከመዘገቡ በኋላ ሌሎች ምርመራዎችም ተደረጉምብን፡፡ በምርመራው ወቅት ከሞላ ጎደል ድብደባ አልደረሰብንም፡፡ ምናልባትም በተያዙበት ወቅት የተደበደቡት ይበቃቸዋል ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጣዩ ቀን ሁላችንም ፍርድ ቤት እንድንቀርብ የተደረግን ሲሆን ፖሊስ ፍርድ ቤቱን 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠየቀ፤ የትብብሩ አመራሮች በበኩላቸው በሰልፈኞቹ በኩል የተፈጸመ አንዳችም ህገ-ወጥ ተግባር አለመኖሩን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ በነጻ እንዲያሰናብተን ጠየቁ፡፡ በተለይ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ኢህአዴግ በዘንድሮው ምርጫ ሙሉ ለሙሉ እንደምናሸንፈው ስላወቀ ነው ያሰረን፤ ይህም ህገ-መንግስቱን የጣሰ ነው›› ሲሉ አስረድተው ነበር፡፡
በዚሁ ፍርድ ቤት በቀረብን ጊዜ ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ታዝቤያለሁ፡፡ በተለይ በታሳሪዎች በኩል የደረሰባቸውን ድብደባ ተከትሎ ህክምና አለማግኘታቸውን፣ እንዲሁም አመራሮቹ በበረዶ ቤት ስለሚገኙ ለጤናቸው አስጊ ስለሆነ የተሻለ አያያዝና ህክምና እንዲደረግላቸው ለፍርድ ቤቱ ባስረዱ ጊዜ የዕለቷ ዳኛ ያሉትን አልረሳም፤ ወደ ፖሊሶች ዞር ብላ ‹‹የጠየቁትን ህክምና እንዲያገኙ አድርጉ፣ ለእናንተም ለመቅጣት እንድትችሉ በህይወት ይቆዩላችሁ›› ነበር ያለችው፡፡ ጆሮዎቼን ማመን ነበር ያቃተኝ! ሁኔታው ሰው ቅጣት እንዲቀበል ብቻ ነው በህይወት መቆየት ያለበት ማለት ነው ብዬ ራሴን እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡
ፍርድ ቤት የነበረን ቆይታ አብቅቶ ወደ ሦስተኛ ተመለስን፡፡ ምርመራውም ቀጠለ፡፡ በምርመራ ወቅት ተመሳሳይና አሰልቺ ጥያቄዎች ነበር በተደጋጋሚ የሚቀርቡልን፡፡ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ መርማሪዎቹ የኢሜልና ፌስ ቡክ አካውንት እስከ ይለፍ ቃል (password) ድረስ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ነበር፡፡
ኢሜልና ፌስቡክ ይኖረኝ እንደሆን ጠየቀኝ፡፡ እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ አስከትሎ አካውንቱንና ፓስወርዱን እንድነግረው ጠየቀኝ፡፡ ‹እንዴት ይሆናል፣ ይሄኮ የግል ጉዳይ ነው፤ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት ስጠኝ ትላለህ?› ስል መልሼ ጠየቅኩት፡፡ ፈቃደኛ ባለመሆኔ አንዴ በንዴት ሌላ ጊዜ በማባበል አይነት የጠየቀውን እንድነግረው ሞከረ፡፡ በአቋሜ መጽናቴን ሲያይ፣ ‹‹ይሄኮ የመንግስት አሰራር ስለሆነ ነው፤ ባትናገርም እኮ መንግስት ያውቀዋል›› አለኝ፡፡ አልመለስኩለትም፡፡ እሱም ‹‹ኢሜልና ፌስቡክ አካውንት አለው፣ ግን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም›› ብሎ የምርመራ መዝገቡ ላይ ሲያሰፍር አነበብኩ፡፡
ከምርመራ ክፍል ወጥቼ ሌሎች ታሳሪዎች ጋር ስንገናኝ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳስተናገዱ ነገሩኝ፡፡ ለመሆኑ ይሄ ምን አይነት የመንግስት አሰራር ይሆን?
የሦስተኛ የስድስት ቀናት ቆይታዬ ለእኔ ብዙ ነገሮችን እንድቃኝ ያስቻለኝ ስለነበር መታሰሬን በግድም ቢሆን ሳልወደው አልቀረሁም፡፡ ምናልባት ባልታሰር ኖሮ እኒያን ሁሉ ባለብዙ ታሪክ እስረኞች አላውቃቸውም ይሆናል፡፡ በታዳጊ ሃና ላላንጎ አስገድዶ መደፈር ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት አምስት ተጠርጣሪዎች እስከ በነፍስ ግድያና ሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው እስከገቡት ወንድሞች ጋር ብዙ ታሪኮችን አደመጥኩ፡፡ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን እና እየደረሰባቸው ያለውን ሰቆቃም ለመገንዘብ ቻልኩ፡፡
ሦስተኛ ፖሊስ በዘመናዊ ህንጻ ውስጥ ኋላቀር የምርመራ ዘዴ የሚተገበርበት ስፍራ መሆኑንም ከብዙ ሰዎች ላይ በደረሰው በደል አየሁ፡፡ በምርመራ ወቅት በተፈጸመባቸው ድብደባና ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎች ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እዛ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በረዶ ቤት (የትብብሩ አመራሮች ታስረውበት የነበረው ቤት) አንዱ የምርመራ ወቅት ማቆያ አሰቃቂ ስፍራ ነው፡፡ ሌላው ‹ቆመህ እደር› የሚባል ሲሆን ተጠርጣሪዎች ለቀናት በዚህ ስፍራ ቆመው ውለው ቆመው እንዲያድሩ የሚደረግበት እንደሆነ በዚህ ሁኔታ ላይ ያለፉ ታሳሪዎች አጫውተውኛል፡፡ ብዙዎች በ‹ቆመህ እደር› ያለፉ ሰዎች የተለያዩ የአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ሰለባ ይሆናሉ፡፡
እውነትም በሦስተኛ ፖሊስ ያለው የምርመራ ስልት እጅግ ኋላቀር ብቻ ሳይሆን ኢ-ህገ-መንግስታዊም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ተጠርጣሪዎች ሰውነታቸው በስፒል ይጠቀጠቃል፣ ትልቅ ሃይላንድ ውሃ ተሞልቶ ብልታቸው ላይ ይንጠለጠላል፣ እግራቸውን ከፍተው ቆመው እንዲያድሩ ይደረጋል፣ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸማል፣ ከብዙዎቹ እስረኞች አፍ እንደሰማሁትና በአካላቸው ላይ የደረሰውን ጉዳት በዓይኔ እንዳየሁት፡፡ በዚህ አይነት ምርመራ የሚያልፉ ሰዎች ምርመራቸው እስኪያልቅ (ለሳምንታት) ከቤተሰብ ጋር መገናኘት አይፈቀድላቸውም፡፡ በነገራችን ላይ በሰልፉ ወቅት የተያዝን እና በሦስተኛ የነበርን ወንድ እስረኞች በሙሉ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንድንገናኝ አይፈቀድልንም ነበር፡፡
በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ባለው ከባድ የማሰቃየት የምርመራ ዘዴ የተሰቃዩ ተጠርጣሪዎች አንዳንዶቹ ራሳቸውንም ለማጥፋት ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸውን አግኝቼ አናግሬያቸው ነበር፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ራሱን ለማጥፋት የገፋፋውን ምክንያት እንዲህ ሲል አስረዳኝ፣
‹‹ምርመራው እጅግ ኢሰብዓዊ ነው፡፡ ራስህን ትጠላለህ፡፡ በቃ በግድ እመን ነው የሚሉት፡፡ ወንጀሉን ሳትፈጽም እዚህ ተጠርጥረህ ብትገባ በግድ ወንጀለኛ ነኝ በል ትባላለህ፡፡ ድብደባው ፋታ የለውም፡፡ በየዕለቱ ማታ ማታ እየወሰዱ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ይቀጠቅጡሃል፡፡ ሰው አትመስላቸውም፡፡ በሀሰት የጠየቁህን አንድ ወንጀል ብታምንላቸው ሌላ ወንጀል ፈጥረው እመን ይሉሃል፡፡ በቃ መዝገቡ ክፍት ነው፤ አንተን ይጠብቃል እመን ይሉሃል፡፡ ከነገ ዛሬ ማሰቃየቱ ያበቃል ስትል ማብቂያ የለውም፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሁሉ ስቃይ ለምን አልገላገልም ብለህ ታስባለህ፡፡ በዚህ ጊዜ ትዝ የሚልህ ደግሞ ራስን ማጥፋት ነው፡፡››
ይህ የብዙ ሰዎች አንደበት የተናገረው እውነታ ነው፡፡ ድርጊቱ በህግ ያልተፈቀደ ቢሆንም ምርመራው ግን በዚህ መልኩ እንደሚከናወን ብዙዎች አስረዱኝ፡፡ የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 19 (5) ስለተያዙ ሰዎች እንዲህ ይላል፣ ‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡››
ሌላ ተጠርጣሪ በምርመራ ወቅት ያጋጠመውን ገጠመኝ የግዱን እየሳቀ አወጋኝ፡፡ ‹‹ለምርመራ በገባሁበት ክፍል ውስጥ መርማሪዎቼ በዱላ ተቀበሉኝ፡፡ ከጥያቄ በፊት ዱላ ይቀድማቸዋል፡፡ ደብድበው ደብድበው ሲደክማቸው እኔን እግሬን ከፍቼ እንድቆም በማዘዝ እነሱ ኮምፒተር ላይ ፊልም እያዩ መዝናናት ጀመሩ፡፡ ከሰዓታት በኋላ ሽንት ቤት እንዲወስዱኝ ለመንኳቸው፡፡ ተሳለቁብኝ፡፡ እየቆየሁ እየቆየሁ ስሄድ ሽንቴን መቆጣጠር እንዳልቻልኩ በመግለጽ ‹ስለወንድ ልጅ አምላክ› ስል በድጋሜ ተማጸንኳቸው፡፡ ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡ ከዚያ ‹በቃ እዚሁ እሸናለሁ› ብዬ ሽንቴን ለቀቅኩት፡፡ በጣም ታፍኜ ስለነበር ሽንቴ እጅግ መጥፎ ጠረን ፈጠረ፡፡ ይገርምሃል ለእኔ ሳይሆን ለቢሯቸው አዝነው እንደውሻ አባርረው ከቢሮ አስወጡኝ፡፡››
ለመሆኑ እነዚህን የስቃይ ድምጾች ሰሚያቸው ማን ይሆን?
source.-http://ethioforum.org/amharic/
Monday, 15 December 2014
አየር መንገድ በፖለቲካ አመለካከት ሰራተኛውን አባረረ
አቶ ወረታው ዋሴ ከእስር ተፈተው ወደ ስራ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ አየርመንገድ የስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው፡፡
አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የስራአስፈጻሚ አባል እና የፋይናንስ ጉዳይ ኀላፊ ሲሆኑ መደበኛ ስራቸው በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ ነበር፡፡ ሆኖም ከ3 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ በዓባይ ጉዳይ ላይ በተደረገ ውይይት ሰራተኛውን ለማሳመፅ ሞክረኀል በሚል ለ2 ዓመታት ከስራቸው ታግደው የነበረ ሲሆን፤ እልህ አስጨራሽ በነበረ የፍርድ ቤት ክርክር ባለፈው ዓመት ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰው ነበር፡፡
ይሄው አሁን ሰሞኑን ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች ድርጅቶች የጠሩትን ሰልፍ በማስተባበር እና በመምራት ተካፍለው ለቀናት በእስር ቤት ቆይተው ወደ ስራቸው ሲመለሱ ከታች ያለውን የስራ ኮንትራታቸው መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ ደራሳቸው፡፡
EAL letter
መስዋዕትነት ማለት እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን አለ? መብትህን በመጠየቅህ አስረውህ እና ደብድበውህ ነጻ ነህ ብለው ይፈቱህ እና ይሄ አልበቃ ብሏቸው ከስራ ያባርሩሀል፡፡ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ የሽዋስ አሰፋም በሚሰሩበት ቴሌ ኮሚኒኬሽን መስራቤት ተመሳሳይ ሰለባ እንደነበሩ አይረሳም፡፡
.. source,-thioforum.org/amharic/አየር-መንገድ-በፖለቲካ-አመለካከት-ሰራተ/
ለኢንተርኔት ነጻነት የማይመቹ ሀገሮች
ኢትዮጵያ እና ጋምቢያ የኢንተርኔት ነጻነት በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝባቸው ሀገራት መሆናቸውን አንድ ሪፖርት አመለከተ፡፡
ኢትዮጵያ ፣ ጋምቢያ እና ሱዳን ለኢንተርኔት ነጻነት የማይመቹ ሀገራት መሆናቸውን ፍሪደም ሀውስ የተሰኘ ድርጅት ያደረገው ትንተና አመልክቷል፡፡
ከዚህ በተቃራኒው ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ የኢንተርኔት ነጻነት ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ተብለዋል፡፡
በአፍሪካ በኢንተርኔት ነጻነት ዙሪያ ጥናት የተደረገባቸው ሀገራት ከባለፈው አመት በባሰ መልኩ የኢንተርኔት ነጻነታቸው ቀንሷል ብሏል ጥናቱ፡፡
ጥናቱ ከተካሄደባቸው 65 ሀገራት ውስጥ በ36ቱ መንግስት ለብሄራዊ ደህንነት እና በሌሎች ምክንያቶች የኢንተርኔት አገልግሎትን እንደሚከታተል፣ እንደሚቆጣጠርም ተመልክቷል..
Internet freedom in Africa: Ethiopia and The Gambia most repressive; South Africa and Kenya freest
source,-http://www.diretube.com/article_read.php?a=7670&mode=preview#.VI61mCuG9kZ
Saturday, 13 December 2014
ዶ/ር ነጋሶ ካሁን በኋላ መታሰር ያለብን እኛ ነን አባሎቻችን ሳይሆኑ
“ካሁን በኋላ አባሎቻችን ሳይሆኑ መታሰር ያለብን እኛ ነን…” ዶ/ር ነጋሶ ለዘ-ሐበሻ የሰጡት ቃለ ምልልስ
(ዘ-ሐበሻ) የአንድነት ፓርቲ መሪ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አባሎቻቸውን ለማስፈታት ሄደው ፖሊስ አልፈታም ሲል እነርሱን ካልፈታችሁ እኔም አብሬ እታሰራለሁ በሚል ለ4 ሰዓታት በፖሊስ ከቆዩ በኋላ ሁሉም አባሎቻቸው መፈታታቸውን ለዘ-ሐበሻ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታወቁ። ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ከዘ-ሐበሻ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ካሁን በኋላ አባሎቻችን ሳይሆን እኛ ነን መታሰር ያለብን” ያሉት ዶ/ር ነጋሶ አባሎቻቸው በታሰሩበት ቦታ ሁሉ በመሄድ እስከሚፈቱ ድረስ አብረው ለመታሰር መወሰናቸውን አስታውቀዋል። ከዘ-ሐበሻ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለ ምልልስ ያድምጡ፦
ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ
source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/7725
የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ውሎ ሁለት አጀንዳዎችን አፀደቀ፡፡
ትናንት አርብ ታህሳስ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) በጠራው ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሁለት አጀንዳዎችን በመወያየት ማፅደቁ ተሰማ፡፡ በመጀመሪያ አጀንዳነት የተነሳው የኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፍቃዳቸው ከፓርቲው ፕሬዘዳንትነት ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የሰየመውን ፕሬዝደንት ተወያይቶ ያፀደቀ ሲሆን፤ በሁለተኛ አጀንዳነት የተያዘው እና ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥራችሁን አሳውቁኝ ባለው መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥርን ወስኗል፡፡
ጠቅላላ ጉባኤው ከሁለቱ አጀንዳዎች በተጨማሪ በተጓደሉ የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላት ምክንያት የማሟያ ምርጫንም ማድረጉ ታውቋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ አሁንም በተለያዩ የፓርቲውና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መምከሩን እንቀጠለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከውይይቱ በኋላም የተለያዩ ተጨማሪ አጀንዳዎችን ከማፅደቅ በተጨማሪ አንገብጋቢ በሆኑ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ አባላትም ከአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው Addis media ጠቁሟል፡፡ . ... .source , -http://ethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/udj.jpg
Friday, 12 December 2014
11ዱ የማዕከላዊ ገራፊዎችን እወቋቸው
ከዳዊት ሰለሞን
በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ጋዜጠኞችን፣ፖለቲከኞችን፣የሀይማኖት ምሁራንና ያለ ምንም ተሳትፎ ኦሮሞዎች በመሆናቸው ብቻ በኦነግነት ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ መተኪያ አልባ ዜጎችን በማሰር ቃላት ሊገልጸውና የሰው ልጅ ሊሸከመው አይችልም ተብሎ የሚታሰብን ሰቅጣጭ ድርጊት በመፈጸም ረገድ ወደር የሌላቸው ገራፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡እነዚህ ሰዎች አሁንም በዚሁ ድርጊታቸው ጸንተው ወንድሞቻችንን እያሰቃዩ የሚገኙ በመሆናቸው ህዝብ ሊያውቃቸውና ቀን ሲወጣም ፍትህ ሊጠይቅባቸው ይገባዋል፡፡
ስማቸው የተጠቀሱትን ሰዎች የምታውቁ አልያም በእነዚህ ሰዎች በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት ስቃይ የደረሰባችሁ ዜጎች መረጃውን ልታዳብሩት ወይም ሊጨመሩ የሚገባቸውን ገራፊዎች ልታጋልጡ ትችላላችሁ፡፡
ገራፊዎቹ ነጭ ወረቀት በማቅረብ ተጠርጣሪዎች ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚያስገድዱ፣ገልብጠው የሚገርፉ፣በወንድ ብልት ላይ ውሃ የተሞላ ላስቲክ በማንጠልጠል የሚያሰቃዩ፣ሴት እስረኞችን ጡታቸውን በበትር የሚደበድቡ፣ሰውን ካልደበደቡ ስራ ያልሰሩ የሚመስላቸው ቃሉ ከገለጻቸው ‹‹አረመኔዎች››ናቸው፡፡ምናልባት የፍትህ ጸሀይ ወጥታ ህዝብ አሸናፊ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ይፈጽሙ የነበሩትን ግፍ በአደባባይ እንዲመሰክሩ ይደረጉ ይሆናል፡፡
ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ወዳጆቻቸውም ስማቸውን ተመልክተው የህሊና ዕዳ ይፈጥሩባቸው ይሆናልና ስማቸውን ይፋ ማድረጉ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል ባይ ነኝ፡፡ .
.1. ታደሰ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ...........
.2. ዩሀንስ ኢንስፔክተር.................
.3. ተዘራ ቦጋለ ኢንስፔክተር............
.4. ብርሃነ ኢንስፔክተር.............
.5. ከተማ ኢንስፔክተር.............
.6. ሰይድ አሊ ኢንስፔክተር........
.7. ገብረመድህን ኑር ኢንስፔክተር..............
.8. ሙልጌታ ኢንስፔክተር............
.9. አሰፋ ትኩት ምክትል ኢንስፔክተር............
.10. ታደሰ አያሌው ኢንስፔክተር............
.11. በለጠ ኢንስፔክተር.........................
..
. . .source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37067
“እስከመቼ ለመተማመን እንነጋገር!”
ባለፈው ዓመት ከሳዑዲ አረቢያ ከተባረሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 85ሺው ተመልሰው መሄዳቸው ተዘገበ
ባለፈው ዓመት ከሳውዲ አረብያ ከተባረሩት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን 50% (ከ 85ሺህ በላይ የሚሆኑት) ተመልሰው ሳውዲ አረብያ መግባታቸውን አዲስ አበባ ላይ ዛሬ በወጣ አዲስ የዳሰሳ ጥናት ተገለፀ:: (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)
ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ መክበድ፣የነፃነት ማጣት እና የስርዓቱን ማዋከብ፣እስር እና ግድያ እየሸሹ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ነው።ሰሞኑን በየመን የባህር ዳርቻ በቀይ ባሕር ውስጥ ከሰባ በላይ ኢትዮጵያውያን መስመጣቸው ይታወቃል።
ዛሬ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበር (CRDA) በሳውዲ ተመላሾች አሁን ያሉበት ጉዳይ ላይ የሚወያይ አውደ ጥናት አዲስ አበባ ላይ የቀረበ አንድ ጥናት ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ከተባረሩት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን 50% (ከ 85ሺህ በላይ የሚሆኑት) ተመልሰው ሳውዲ አረብያ መግባታቸውን ይገልፃል።ቪኦኤ የአሜሪካ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ አውደ ጥናቱን አስመልክቶ ባቀረበው ዘገባ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበር (CRDA) የስትራቴጂክ ቡድን መሪ እና በድርጅቱ ልዩ አማካሪ አቶ ክፍለ ማርያም ገ/ወልድን ባነጋገረበት ወቅት ”ሀቁን እንነጋገር ከተባለ ግማሾቹ ተመልሰው ሄደዋል” ብለዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙ የስደት ተመላሾች ውስጥ ለቪኦኤ ሃሳቧን የሰጠች ወጣት ”ከችግር የተነሳ ነው።እዚህ ሆኘ እራሴን ከማጠፋ ሄጄ ልሙት ከማለት ነው” ብላለች።ለወገኖቻችን በአራቱም ማዕዘን መውጣት የሀገራችን አጠቃላይ የፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ከዋና ምክንያትነት አያመልጡም።የችግሩ ዋና መንስኤ እየተተወ ስደቱን ብቻ ብናወጋው መፍትሄ አይሆንም።
የተመላሾቹንም ሆነ የአዲሱን ትውልድ በሀገሩ ተመክቶ እና ተማምኖ እንዲኖር አልተደረገም።ይልቁንም የኢህአዲግ አባል ካልሆነ እና ከካድሬዎች እግር ስር ካለወደቀ መኖር አይችልም።በሥራ ዓለም ያለው ባለሙያንም ብንመለከት የነፃነት ማጣቱ እና ሃሳቡን እና ችሎታውን ለሀገሩ ማበርከት አልቻለም።መሃንዲሱ፣የህክምና ዶክተሩ እና የአይሮፕላን አብራሪው በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ተደረገ።ሁሉ ሃገሩን ጥሎ ለመሄድ አኮበኮበ የቀረው ቆርጦ ከኢህአዴግ/ወያኔ ጋር ተጋፈጠ።ለእዚህ አብነት የሚሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ እና የዘጠኙ አጋሮቻቸው ድርጊት ተጠቃሽ ነው።
የኢትዮጵያ ጉዳይ በእንዲህ አይነት ሁኔታ እንደሀገር የመቀጠላችን አደጋ በራሱ በግልፅ ይታያል።ጥቂቶች በሙስና እና በጎሳቸው ብቻ በሀብት ሲናጥጡ ሌላው ዜጋ ሃገሩን በረሃ ለበረሃ እየተንከራተተ ሲወጣ አይኖርም።አንድ ቀን እዝያው ሀገር ውስጥ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ የመውጣታቸው አደጋ አይኖርም ማለት አይቻልም።የወገኖቻችን ሀገር ጥለው የመሄድ ጉዳይ የሚያመለክተው ይህንን ነው።ቁጥር ደግሞ ከሁሉ በላይ የሀገራችንን የፖለቲካ መድረክ መቀየር እንዳለበት አመላካች ነው።”ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ወገኖቻችን ተመልሰው መከራ ወደ አዩባት ሳውዲ ተመለሱ” የሚለው ዘገባ በእራሱ መጪውን አመላካች ነው።እናት ልጇ ተመልሳ እቤት ከገባች በኃላ ተመልሳ ስትሰደድ እንዴት ታዝን? ምን ያልደረሰብን አለ? ሱዳን ባቅሟ ኢትዮጵያውያንን አባረረች ስንባል፣የመን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መንገዶቿን ሞሉ ሲባል፣ጅቡቲ ኢትዮጵያንን ስታስር፣ እራሳችንን መጠየቅ ያሉብን ሶስት ጥያቄዎች አሉ እነሱም –
ኢትዮጵያ ክብሯ እና ማንነቷ አልተዋረደም ወይ?
ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር የፖለቲካው ችግር አለመስተካከል ዋነኛው ምክንያት አይደለም ወይ? እና
ለእዚህም ተጠያቂዎች የእያንዳንዳችን ለስርዓቱ መቀየር የአቅማችንን አለማድረግ አይደለም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች።
በመሆኑም ሰቆቃ ስንሰማ የምንኖርበት ዘመን እንዲቆም፣ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ፣በሙስና የተነከረው እና ክብሯን እና ማንነቷን ከሚመጥናት በታች የሆነ አስተሳስብ ያለው ኢህአዲግ/ወያኔ የበለጠ ሀገራችንን መቀመቅ ሳይከት የእያንዳንዳችንን ኃላፊነት እንወጣ።በዝምታችን ኢትዮጵያን ከሚገድሉ ጋር አንተባበር።
ከእዚህ በታች ያለው ማያያዣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ከጥቂት ወራት በፊት ከሳውዲ የተባረሩ ወገኖቻችን ተመልሰው ወደ ሳውዲ የመመለሳቸውን ሁኔታ አስመልክቶ በድምፅ ያቀረበው ዘገባ ነው።
Thursday, 11 December 2014
አንድ ኢትዮጵይዊ ወጣት በደቡብ አፍሪካ በድንጋይ ተደብድቦ ተገደለ ?
Ethiopian man stoned to death in Mayfair
JOHANNESBURG – Police have confirmed they are investigating a case of murder after an Ethiopian man was stoned to death in Mayfair, south of Johannesburg.
It's believed community members in the suburb accused the man and his three friends of robbing a business and started looking for him.
When they found him on Saturday, they allegedly began beating him and throwing rocks at him.
The police's Khensani Magoai says no one has been arrested.
The news has emerged as the South African Human Rights Commission hosts a business and human rights dialogue in Sandton, on issues affecting non-citizens including refugees and asylum seekers in the country.
Yesterday, the SAHRC said violence against foreigners in the country should now be referred to as “afrophobia” and not xenophobia with the latest research showing Africans are attacked and not Europeans.
SAHRC chair, advocate Mabedle Lawrence Mushwana said there is a difference between xenophobia and acts of violence committed against African foreigners living in South Africa.
He said the sad fact is that only those who come from African countries are being targeted.
“Only those from within Africa suffer the most.”
In 2008, the world watched with dismay as South African citizens violently attacked foreigners in communities across the country.
Tens of thousands of migrants were displaced and a number of them killed amid mass looting and destruction of foreign-owned homes, property and businesses.
The SAHRC says the shocking events of 2008 can never be allowed to happen again.
(Edited by Refilwe Pitjeng)
Masego Rahlaga . source,-http://www.diretube.com/articles/read-ethiopian-man-stoned-to-death-in-south-africa_7628.html#.VIn5JyuG-52
Wednesday, 10 December 2014
‹‹መንግሥት ባለበት አገር በጠራራ ፀሐይ ቤቴን ተቀማሁ›› ወ/ሮ ዘውዴ ወልደማርያም፣ የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ
የዛሬ ‹‹ምን እየሠሩ ነው?›› ዐምዳችን እንግዳ ወ/ሮ ዘውዴ ወልደማርያም ይባላሉ፡፡ ዕድሜያቸው 70 መሆኑን ይናገራሉ፡፡
የሚኖሩት በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 11/12 ወይም በአሁኑ ወረዳ ሰባት ውስጥ ነበር፡፡ ወ/ሮ ዘውዴ በ2001 ዓ.ም. በ1,700,000 ብር የገዙትን ቤት ላለፉት ስድስት ዓመታት የኖሩበት ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉም ባይሆን የተወሰነ ግንባታ አካሂደውበታል፡፡ በቆርቆሮና እንጨት ታጥሮ የነበረን ግቢ፣ በግንብ ዙሪያውን ከሠሩና ሰርቪስ ቤቶችን ካደሱ በኋላ፣ ዋናውን ቤት ለመሥራትም ዲዛይንና የግንባታ ፈቃድ አግኝተው ነበር፡፡ ቤቱን ሲገዙ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሕጋዊ ሰነዶችን ከመንግሥት ተቋማት ያገኙ ቢሆንም፣ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ‹‹የገዙት ቤት ይዞታነቱ የሌላ ሰው ነው፡፡ ከእርስዎ ቀደም ብሎ በ1985 ዓ.ም. ለሌላ ሰው ተሸጧል፡፡ በመሆኑም አስረክበው እንዲወጡ›› የሚል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይደርሳቸዋል፡፡ በሁኔታው የተደናገጡት ወ/ሮ ዘውዴ፣ ወደ ፍርድ ቤት ሄደው ቢያመለክቱም እንዲወጡ ይነገራቸዋል፡፡
‹‹በሕጋዊ መንገድ የገዛሁትን ቤቴንማ ዝም ብዬ አላስረክብም›› ያሉት ወ/ሮ ዘውዴ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ብለው ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ፡፡ እዚያም ይወሰንባቸዋል፡፡ ተስፋ ባለመቁረጥ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎትም ሄደዋል፡፡ ውሳኔው ግን ሊቀለበስ አልቻለም፡፡ የመጨረሻ ጉዟቸውን ወደ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ቢያደርጉም፣ ‹‹የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው አይደለም›› በሚል የሦስት መስመር ምላሽ ተስፋቸው ተሟጦ አለቀ፡፡ መንግሥትንና የመንግሥትን ተቋማት በማመን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያፈሩት ገንዘባቸው አግባብ ባልሆነ መንገድ እንደተነጠቁ የሚናገሩት ወ/ሮ ዘውዴ፣ እግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ ይላሉ፡፡ ታምሩ ጽጌ አነጋግሯቸዋል፡፡ . source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36992
ልማታዊ ሙስና?
ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት 305 ሺሕ ብር
ባለፈው ዓርብ በተከፈተው የመሬት ሊዝ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ቀረበ፡፡ ይህ ዋጋ በከተማው ታሪክ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የሊዝ ጨረታን የወቅቱ አነጋጋሪ ክስተት አድርጓል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ አካባቢ 449 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ በካሬ ሜትር የቀረበው ገንዘብ ሲሰላ ይህ አነስተኛ ቦታ 136.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሆኗል፡፡ 20 በመቶ ብቻ የተከፈለበት ይህ መሬት ከነወለዱ እስከ 300 ሚሊዮን ብር በ30 ዓመት ሊደርስ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ይህ ክስተት ለአዲስ አበባ ሊዝ ሥሪት ባለሙያዎች እንዲሁም በጨረታው ለታደሙ ባለሀብቶች የቀረበው ዋጋ ብዥታን ፈጥሯል፡፡ በጨረታው ላይ ሁለተኛ ሆኖ የቀረበው ዋጋም ከዚህ ቀደም ቀርቦ የማያውቅ ሲሆን፣ የቀረበውም በካሬ ሜትር 288 ሺሕ ከ90 ሳንቲም ነው፡፡ “በአዲስ አበባ የሊዝ ዋጋ ላይ ቆም ተብሎ ካልታሰበ አደገኛ ውጤት ሊኖረው ይችላል፤” ሲሉ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሊዝ ባለሙያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
መርካቶ በርበሬ ተራ ለሚገኘው ለዚህ 449 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ያቀረበው ዝዋይ ኢንተርናሽናል የተባለ ኩባንያ ነው፡፡ ይህ ኩባንያ ቀደም ሲል ከዚህ ቦታ አጠገብ መሬት በሊዝ ገዝቶ የንግድ ማዕከል ያቋቋመ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ለዚሁ ቦታ በካሬ ሜትር 288 ሺሕ ከ90 ሳንቲም ያቀረበው ደግሞ ኤንኤስኤ የተባለ ኩባንያ ነው፡፡ ይህ ኩባንያም ቦታውን ማሸነፍ ባይችልም ያቀረበው ገንዘብ ግን በከተማው ታሪክ ቀርቦ የማያውቅ ነው፡፡ በከተማው ታሪክ ክብረ ወሰን ሆኖ የቆየው ከወራት በፊት በስምንተኛው ዙር ሊዝ ጨረታ ቦሌ አካባቢ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ የሚገኝ ቦታ ነበር፡፡ ቦታው 158 ካሬ ሜትር ስፋት ሲኖረው፣ ለዚህ ቦታ በካሬ ሜትር 65 ሺሕ ብር ያቀረበው ኤስኤንአይ ትሬዲንግ ነው፡፡
በ11ኛው ሊዝ ጨረታ በካሬ ሜትር የቀረበው 305 ሺሕ ብር ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦ ከነበረው 65,000 ብር በ4,692 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ በርካታ የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች ይህ ዋጋ ምናልባት ለዓመታት ክብረ ወሰን ሆኖ ይቆያል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን በከተማው የሚገኙ አንዳንድ ነጋዴዎች የሚወስዱትን አደጋ መገመት የሚያስቸግር በመሆኑ በቅርቡ አይሻሻልም ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ገንዘብ በማንኛውም መመዘኛ ጤነኛ ኢኮኖሚያዊ አካሄድ አይደለም ካሉ በኋላ፣ ሁኔታው ቆም ተብሎ ሊታሰብበት የሚገባ ነው ይላሉ፡፡
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለጨረታ የቀረበው ይህ ቦታ ብቻ ነው፡፡ ቦሌ ክፍለ ከተማ ላይ ደግሞ 57 ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ ሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ የወጡ ሁለት ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ቀርቦላቸዋል፡፡
በዚህ ቦታ ለወጣ 400 ካሬ ሜትር ቦታ ቤተልሔም ብርሃን የተባሉ ባለሀብት፣ በካሬ ሜትር 55,244 ብር አቅርበዋል፡፡ ወ/ሮ መኪያ የተባሉ ባለሀብት ደግሞ ለ403 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር 51,111 ብር አቅርበዋል፡፡
ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ሁለት ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን፣ 12,000 እና 15,000 በካሬ ሜትር ቀርቦላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ክፍለ ከተማ በብዛት ኮንዶሚኒየም ቤቶች እየተገነቡበት ባለው ቀጠና በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ መኖሪያ ቤት እየገነባ ባለበት አካባቢ 52 ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ቦታዎች እስከ 15,000 ብር የቀረበላቸው ሲሆን፣ ራሕማ ጀማል የተባሉ ባለሀብት በዚህ አካባቢ በካሬ ሜትር 15,221 ብር ሲያቀርቡ ከዚሁ ቦታ አጠገብ ዘገየ ዘመዴ የተባሉ ባለሀብት 2,489 ብር አቅርበዋል፡፡
በዚህ አካባቢ ብዙም ጨረታ ወጥቶ የማያውቅ በመሆኑ የቦታውን ዋጋ ለመስጠት ባለሙያዎች ተቸግረው ነበር፡፡ በሁለቱ ባለሀብቶች መካከልም የቀረበው ዋጋ ልዩነቱ ከዚህ መነሻነት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ በዚሁ አካባቢ በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ዋጋ አቅርበው አሸናፊ የሆኑ አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ውብነሽ ሀብቴ በካሬ ሜትር 3,189 ብር፣ አሰፋ ታምሬ በካሬ 2,689 ብር፣ ብርቄ መለስ 1,805 ብር ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እንዲሁ የዋጋ መነሳት የታየበት ሲሆን፣ በካሬ ሜትር 18,000 ብር ቀርቧል፡፡
የአዲስ አበባ የመሬት ዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ሲሆን፣ ለዚህ ምክንያቱ አስተዳደሩ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ በቅርብ ከኢብኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ የመሬት ዋጋ እንዲንር መንግሥት እንደማይፈልግና አልሚዎች ያላቸውን ካፒታል መሬት በመግዛት ሳይሆን፣ ለልማቱ በማዋል ማደግ እንደሚኖርባቸው አስታውቀው ነበር፡፡ ነገር ግን የከተማው የመሬት ዋጋ በየጊዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ መገኘቱ ለበርካታ ኢኮኖሚያዊ ችግሮ ሊዳርግ እንደሚችል በመግለጽ ባለሙያዎች ማሳሰቢያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር). source,- http://www.goolgule.com/305-birr-for-a-meter-square-of-land/
Tuesday, 9 December 2014
"ወያኔን ሽሽት የተቀጠፉ ነፍሳት"
"ወያኔን ሽሽት የተቀጠፉ ነፍሳት"
ሞት አዲስ ነገር አደለም ያለ እና የሚኖር የፈጣሪ ስጦታ ነው ።አማሟቴን አሳምረው የሚባለውም ፈጣሪ በአዘዘልን መንገድ ይቺን ከንቱ አለም ለመሰናበት ነው።ወጥቶ መቅረት የሞትም ሞት ነው ለቤተሰብ ፀፀት ዛሬ የምንሰማው ነገር እጅግ ልብ ይሰብራል 70 የሚሆኑ ኢትዮጲያውያን የኑሮ ሸክም ቢያማራቸው ወያኔ መቆሚያ መቀመጪያ ቢያሳጣቸው የሰው ሀገር ጅብ ይብላኝ ብለው የመን ባህር ላይ እንደ ጨው ሟምተው ቀሩ ።ስንቱ ነው መንግስትን ሽሽት በበረሃ የቀረው ስንቱ ሙሁር ነው ያስተማረችውን ሀገሩን መርዳት ሲገባው ጥሎ የወጣው ጋዜጠኛው፣ዶክተሩ፣አርቲስቱ፣ተማሪው፣አስተማሪው፣,,,,,,, እስርን ሽሽት ድብደባን ሽሽት እንደ አሸዋ በእየቦታው ተበታትነን ቀረን ለዚህ ሁሉ ሰበብ ታዲያ ተጠያቂ ወያኔ ነው ።ዛሬ 70 ውም ስለሞቱ እና የሚዲያ ሽፋን ስላገኙ ተወራ እንጂ ከኢትዮጲያ ምድር ሰው ያልተሰደደበት ቀን እና ያልሞተበት ቀን የለም ።እስከመቼ ነው በሰው ደም የስልጣን ወንበራቸውን የሚያረዝሙት እስከመቼ ነው ህዝብ እየተበደለ ሀገር ደም እያነባች የምትኖረው ወያኔ ሆይ በቃክ የሚበላውን ያጣ ህዝብ አንድ ቀን መሪውን መብላቱ አይቀርም ። አዘጋጅ ሳሙኤል አደም
Monday, 8 December 2014
ተቃዉሞ ሠልፍ፤ ድብደባና እስራት በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ......
አሳካሪ-እና ግልፅ ያልሆነ ፖለቲካ።ለአዲስ አበባ በርግጥ እንግዳ አይደለም።ጥንት እንደ ቅዳሜዉ ነበረች።የዛሬ አርባ አመት የጥንት ሥርዓቷ መለወጡ በታወጀ፤ ያለምንም ደም የኢትዮጵያ እንከን እንዲወድም በተዘመረባት ማግስትም በደም ኩሬ ተነከረች።በ1983 ያቺ ጉደኛ ከተማ የሠላም፤ ዲሞክራሲን ጉዞ መጀመሯ ተነግሮባት ሳያበቃ በሌላ ደም ጨቀየች።
አዲስ አበባ እንደገና ሠላማዊ ሠልፍ በሐይል ተበተነ ወይም ታገደባት።ለሠላማዊ ሠልፍ አደባባይ የወጡ ሠላማዊ ነዋሪዎችዋ፤ ሠላማዊ ነዋሪዎችዋን ለሰላማዊ ሠልፍ የጠሩ የሠላማዊ ትግል አቀንቃኝ ፖለቲከኞችዋ በፖሊስ ቆመጥ ተቀጠቀጡ፤ተፈነከቱ፤ተሰባበሩባትም።የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር-አቶ ስለሺ ፈይሳ። መቶዎች ታሠፈሱ-ታሰሩባትም።አዲስ አበባ፤የአፍሪቃ መዲና።የቅዳሜዉን ክስተት አስታከን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ እዉነት ላፍታ እንቃኛለን አብራችሁኝ ቆዩ።
ዶክተር ደመቀ አጪሶ የፖለቲካ ሳይንስ አጥኚ።አሳካሪ-እና ግልፅ ያልሆነ ፖለቲካ።ለአዲስ አበባ በርግጥ እንግዳ አይደለም።ጥንት እንደ ቅዳሜዉ ነበረች።የዛሬ አርባ አመት የጥንት ሥርዓቷ መለወጡ በታወጀ፤ ያለምንም ደም የኢትዮጵያ እንከን እንዲወድም በተዘመረባት ማግስትም በደም ኩሬ ተነከረች።በ1983 ያቺ ጉደኛ ከተማ ድፍን ኢትዮጵያን ይዛ የ17 ዓመቱን የደም ኩሬ መሻገሯ፤የሠላም፤ ዲሞክራሲን ጉዞ መጀመሯ ተነግሮባት ሳያበቃ በሌላ ደም ጨቀየች።1997 ነፃ ምርጫ አስተናገደች።ወዲያዉ ግን አስከሬን ይለቀም፤ ቁስል ይጠቀለል፤ እስረኛ ይታፈስባት ገባ።ሐቻምና አምናም ብዙ የተለየ ታሪክ የላትም።ቅዳሜ ተደገመባት።ሮብ-በርሊን።የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፅሕፈት ቤታቸዉ ዉስጥ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝን ሲያነጋግሩ ፅሕፈት ቤቱ አጠገብ ተሰልፈዉ የነበሩት ኢትዮጵያዉያንየጮኹ፤ የፈከሩለት፤የተናገሩ ያወገዙበት ጉዳይ በርግጥ አዲስ አይደለም።
ከኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስከ ሐይማኖት መሪዎች፤ ከተራዉ ኢትዮጵያዊ እስከ ኢትዮጵያዉን፤ አንዳዴም የዉጪ ጋዜጠኞችና ምሑራን፤ ከዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች እስከ መያዶች ለተከታታይ ዓመታት የታገሉ፤ የጮኹ፤ የዘገቡ፤የተቹ፤ የመከሩ፤ ያሳሰቡበት ጉዳይ ነዉ።የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች-ያክብር፤ መብቶቹን እንዲያከብር ምዕራባዉያን መንግስታት ግፊት ያድርጉበት የሚል።
ሰሚ እንጂ አድማጭ ያጣ ጩኽት ግን የማያቋርጥ ደማቅ ጩኸት።የበርሊን ሰልፈኞችም የማያቋርጠዉን ጩኽት ጮሁ።ሮብ።ወይዘሮ እንጌላ ሜርክል የመብት ትግል፤ ጥያቄ ጩኸቱን ተደጋጋሚነት፤ ሰሚ እንጂ አድማጭ ያጣበትን ምክንያት፤ የማያቋርጥነቱንከአቶ ሐይለማርያም፤ ከበርሊን ሠልፈኞች ወይም ከኢትዮጵያዉያንና የኢትዮጵያን ጉዳይ ከሚከታተሉ ወገኖች እኩል ምናልባትም አቶ ሐይለማርምን ከመጋበዛቸዉ ከብዙ ዓመታት በፊት ያዉቁታል።
አቶ ሐይለ ማርያምን በርሊን ድረስ የጋበዙት የሚያዉቁትን ለማሳወቅ እንዳልሆነ ማወቁ በርግጥ የሌላዉ ፋንታ ነዉ።ይሁንና ሜርክል «ብዙዎች ብዙ ጊዜ የሚሉ ወይም የሚፈልጉትን በል፤ ግን አንተንና ወገኖችሕን የሚጠቅመዉን አድርግ» አይነት ፖለቲካዊ መርሕን በሚያቀነቅነዉ የምዕራባዉያን ፖለቲካዊ-ዲፕሎማሲያዊ ሥልት ባይካኑ ኖሩ የአዎሮጳን የምጣኔ-ሐብት መዘዉር ሐገርን ለዘኝ ዓመት ቀርቶ ለዘኝ ቀንምመምራት ባልቻሉ ነበር።
ሥለ ኢትዮጵያም ብዙዎች የሚሉ-የሚፈልጉትን እንደሚያዉቁ፤ አሳዉቀዉ-የሚፈልጉትንአደረጉ። «ፖለቲካዊ ግንኙነቶቻችን በጣም ጥልቅና ጥብቅ ናቸዉ።ሐሳብን በነፃነት (የመግለፅ መብትን)ና ሥለ መያዶች ሥራም ተነጋግረናል።ባጠቃላይ ግን አግባቢ የሐሳብ ልዉዉጥ ነዉ ያደረግነዉ-ማለት ይቻላል።»
አቶ ሐይለማርያ ሁሌም እንደሚያደርጉት በርሊን ድረስ የተከተላቸዉን ተቃዉሞ፤ ጥያቄና ጩኸት ማድመጥ አይደለም መስማት እንኳን አልፈለጉም።የሜርክል የግድምድሞሽ ጥቆማም «ካንገት እንጂ ካንጀት» እንዳልሆነ መረዳቱ አላቃተቸዉም።እና ተቃዉሞ ጩኸቱም፤ ተዘዋዋሪ-ጥያቄ ጥቆማዉም የሌለ ያክል ሐገራቸዉ አስተማማኝ ሠላም እና መረጋጋት የሠፈነባት መሆኗን አስታወቁ።
«ዛሬ እዚሕ የመጣሁት ተጨማሪ የጀርመን ኩባንዮች ወደ ሐገሬ እንዲመጡና ወረታቸዉን ሥራ ላይ እንዲያዉሉ ለመጋበዝ ነዉ።ምክንያቱም የጀርመን ኩባንዮች ሐገሬ ዉስጥ እንዲሰሩ የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎች አሉ።ኢትዮጵያ በጣም የተረጋጋች፤ ሠላማዊና የጀርመን ባለሐብቶች ከኛ ጋር ለመስራት የሚችሉባት ሐገር ናት።»
ጠቅላይ ሚንስትሩ በርሊን ላይ ኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት የሠፈነባት መሆኗን ደጋግመዉ ሲናገሩ እዚያዉ አዲስ አበባ ዉስጥ የመንግሥታቸዉና የተቃዋሚዎቹ ፖለቲከኞች በሠላማዊ ሠልፍ ማድረግ-ና መከልከል ሰበብ ይወዛገቡ ነበር።
ግጥምጥሞሹ።
የኮሚንስቱ ርዕዮተ-ዓለም የማረካቸዉ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ዘዉዳዊዉን ሥርዓት ለመቃወም አንድ ሁለት በሚሉበት ዘመን የኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት አፄ ሐይለ ሥላሴ ቦንን ጎብኝተዉ ነበር።«እኛ የኮሚንስት ሥጋት የለብንም።» አሉ (1954 እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር።) ዘፄ ሐይለ ሥላሴ የለም ያሉትን ኮሚንስታዊ ርዕዮተ-ዓለም የሚያቀነቅኑ ኢትዮጵያዉያን ጎራ ለይተዉ የሚጋደሉበት ዘመን አብቅቶ ወይም ማብቃቱ ተነግሮ በ1997 በአንፃራዊ መመዘኛ የመጀመሪያዉ ነፃ ምርጫ በተደረገ ማግሥት ዉጤቱ በቀሰቀሰዉ ግጭት፤ ኢትዮጵያ በተለይም አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዉ በሚገደል፤በሚታሰርባት መሐል የያኔዉ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለሥ ዜናዊ ወደ ቦን ምጥተዉ ነበር።ጥቅምት ማብቂያ 1998።«በእነዚሕ ሥራ አጥ ወጣቶች አምስት የጅ ቦምቦች ፖሊስ ላይ ተጥለዉ የተወሰኑ ፖሊሶች ተገድለዋል፤ ቆስለዋልም።ሁለት ጠመንጃዎች ከፖሊስ ተቀምተዉ ነበር።አንዱን ሐሙስ አገኘነዉ።ሐሙስ ነገሮች ተረጋግተዋል።በመሐሉ ግን ብዙ ኢትዮጵያዉን ሞተዋል።ሞቱ ያሳዝነኛል ግን የተለመደዉ አይነት ሠልፍ አልነበረም።»
በዚያ ግጭት መንግሥት እንዳመነዉ-197 ሰዎች ተገድለዋል።የሟች-ቁስለኛዉን ትክክለኛ ቁጥር በርግጥ ቤቱ ነዉ የሚያዉቀዉ።ሺዎች ታስረዋል።ከዚያ በኋላም የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃዉሞ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰባ፤ የሙስሊሞች ጥያቄ በተነሳ ቁጥር ሰዎች በጅምላ መደብደብ፤መታፈስ መታሰራቸዉ የአዲስ አበባ ፈሊጥ ሆኗል።
አዲስ አበባን የዉዝግብ፤ ግጭት ማዕከል ያደረገዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካን «የተሳከረ» የሚሉት የፖለቲካ አዋቂ ዶክተር ደመቀ አጪሶ ለመሳከሩ ከገዢዉ ፓርቲ እኩል ተቃዋሚዎችንም ይወቅሳሉ።ጥሩዉ ግን አልሆነም።በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ ለታቀደዉ ምርጫ የጋር ትብብር የመሠረቱት የዘጠኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብርና የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሮብ የገለፁት ዉዝግብ አጉዞ አጉዞ በቅዳሜዉ ድብደበና እስራት አሳረገ።በድብደባ-እስራቱ መሐል ሌላም ነገር ተፈፅሞ ነበር።
የሠማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ፖሊስ እና የሥለላ ባልደረቦች የዘጠኙን ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና አባላትን ማሰር-ማስፈራራት የተጀመሩት ከቅዳሜ በፊት ነዉ።ቢያንስ አምስት የሠማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ከሳምንት በፊት ታስረዋል።ለሠላማዊ ሠልፍ የሚደረገዉ ዝግጅት ግን አልተቋረጠም ነበር።
የዘጠኙ ፓርቲዎች ማስተባባሪያ ወይም የሠማዊ ፓርቲ ፅሕፈት ቤቱን ሁኔታ ደግሞ አቶ ስለሺ እንዲሕ ይገልጹታል።የታሰሩትም ሆነ የተደበደቡት ሰዎች ትትክክለኛ ቁጥር አይታወቅም።የጉዳቱ መጠንም እንዲሑ።የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ የፌደራል ፖሊስ፤ የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ፅሕፈት ቤት ባለሥልጣናትን በሥልክ ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራም አልተሳካልንም።
የታሰሩት ግን አቶ ሥለሺ እንደሚሉት በየሥፍራዉ ተከፋፍለዉ ነዉ።በዶክተር ደመቀ አገላለፅ «አሳካሪዉ» የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስከመቼ እንዳሳከረ ይቀጥላል ይሆን? ለዛሬ ይብቃን። ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።
ነጋሽ መሐመድ . . .
አርያም ተክሌ . . .source,-http://www.dw.de/
Subscribe to:
Posts (Atom)