Monday, 15 December 2014

ለኢንተርኔት ነጻነት የማይመቹ ሀገሮች

ኢትዮጵያ እና ጋምቢያ የኢንተርኔት ነጻነት በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝባቸው ሀገራት መሆናቸውን አንድ ሪፖርት አመለከተ፡፡ ኢትዮጵያ ፣ ጋምቢያ እና ሱዳን ለኢንተርኔት ነጻነት የማይመቹ ሀገራት መሆናቸውን ፍሪደም ሀውስ የተሰኘ ድርጅት ያደረገው ትንተና አመልክቷል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ የኢንተርኔት ነጻነት ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ተብለዋል፡፡ በአፍሪካ በኢንተርኔት ነጻነት ዙሪያ ጥናት የተደረገባቸው ሀገራት ከባለፈው አመት በባሰ መልኩ የኢንተርኔት ነጻነታቸው ቀንሷል ብሏል ጥናቱ፡፡ ጥናቱ ከተካሄደባቸው 65 ሀገራት ውስጥ በ36ቱ መንግስት ለብሄራዊ ደህንነት እና በሌሎች ምክንያቶች የኢንተርኔት አገልግሎትን እንደሚከታተል፣ እንደሚቆጣጠርም ተመልክቷል..
Internet freedom in Africa: Ethiopia and The Gambia most repressive; South Africa and Kenya freest source,-http://www.diretube.com/article_read.php?a=7670&mode=preview#.VI61mCuG9kZ

No comments:

Post a Comment