Tuesday, 9 December 2014

"ወያኔን ሽሽት የተቀጠፉ ነፍሳት"

"ወያኔን ሽሽት የተቀጠፉ ነፍሳት" ሞት አዲስ ነገር አደለም ያለ እና የሚኖር የፈጣሪ ስጦታ ነው ።አማሟቴን አሳምረው የሚባለውም ፈጣሪ በአዘዘልን መንገድ ይቺን ከንቱ አለም ለመሰናበት ነው።ወጥቶ መቅረት የሞትም ሞት ነው ለቤተሰብ ፀፀት ዛሬ የምንሰማው ነገር እጅግ ልብ ይሰብራል 70 የሚሆኑ ኢትዮጲያውያን የኑሮ ሸክም ቢያማራቸው ወያኔ መቆሚያ መቀመጪያ ቢያሳጣቸው የሰው ሀገር ጅብ ይብላኝ ብለው የመን ባህር ላይ እንደ ጨው ሟምተው ቀሩ ።ስንቱ ነው መንግስትን ሽሽት በበረሃ የቀረው ስንቱ ሙሁር ነው ያስተማረችውን ሀገሩን መርዳት ሲገባው ጥሎ የወጣው ጋዜጠኛው፣ዶክተሩ፣አርቲስቱ፣ተማሪው፣አስተማሪው፣,,,,,,, እስርን ሽሽት ድብደባን ሽሽት እንደ አሸዋ በእየቦታው ተበታትነን ቀረን ለዚህ ሁሉ ሰበብ ታዲያ ተጠያቂ ወያኔ ነው ።ዛሬ 70 ውም ስለሞቱ እና የሚዲያ ሽፋን ስላገኙ ተወራ እንጂ ከኢትዮጲያ ምድር ሰው ያልተሰደደበት ቀን እና ያልሞተበት ቀን የለም ።እስከመቼ ነው በሰው ደም የስልጣን ወንበራቸውን የሚያረዝሙት እስከመቼ ነው ህዝብ እየተበደለ ሀገር ደም እያነባች የምትኖረው ወያኔ ሆይ በቃክ የሚበላውን ያጣ ህዝብ አንድ ቀን መሪውን መብላቱ አይቀርም ።
አዘጋጅ ሳሙኤል አደም

No comments:

Post a Comment