Saturday, 6 December 2014

መስቀል አደባባይ የፌደራል ፖሊስ በጫኑ መኪናዎች ተሞልቷል

በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታፈሱት አመራሮች ጨርቆስ ፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ታወቀ 9ኙ ፓርቲዎች በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ የታፈሱት የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት እንደሚገኙ ታወቀ፡፡ ዛሬ ጠዋት መስቀል አደባባይ ከተያዙት ባሻገር ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ ሲያመራ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የሰማያዊና የሌሎች የ9ኙ ትብብር አባል ፓርቲ አማራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች በአሁኑ ወቅት ጨርቆስ ፖፖላሬ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ታሳታፊዎቹ ካሳንቺስ 6ኛ መምሪያ ተወስደው የነበር ሲሆን ጠያቂዎች በሄዱበት ወቅት ‹‹የሉም!›› እያሉ ሲመልሶ ቆይተዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ወደ ጨርቆስ ከተዛወሩ በኋላ የአካባቢው ህዝብ ሱቅ እንዲዘጋና እንቅስቃሴውን እንዲቀንስ እንደተደረጉ ታሳሪዎቹን ለመጠየቅ ወደ ቦታው ያቀኑ የፓርቲዎቹ አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ታሳሪዎቹን ለመጠየቅ የሄዱት ሰዎች ‹‹ምርመራ ላይ ስለሆንን አናሳይም፡፡›› እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ከሰማያዊ ጽ/ቤት ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ ሊያቀና በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የት እንዳሉ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ከ300 በላይ አመራሮችና አባላት እንደታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፍዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ . soyrce,-http://www.goolgule.com/9-parties-24-hours-demonstration/

No comments:

Post a Comment