Monday, 15 December 2014

አየር መንገድ በፖለቲካ አመለካከት ሰራተኛውን አባረረ

አቶ ወረታው ዋሴ ከእስር ተፈተው ወደ ስራ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ አየርመንገድ የስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው፡፡
አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የስራአስፈጻሚ አባል እና የፋይናንስ ጉዳይ ኀላፊ ሲሆኑ መደበኛ ስራቸው በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ ነበር፡፡ ሆኖም ከ3 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ በዓባይ ጉዳይ ላይ በተደረገ ውይይት ሰራተኛውን ለማሳመፅ ሞክረኀል በሚል ለ2 ዓመታት ከስራቸው ታግደው የነበረ ሲሆን፤ እልህ አስጨራሽ በነበረ የፍርድ ቤት ክርክር ባለፈው ዓመት ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ይሄው አሁን ሰሞኑን ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች ድርጅቶች የጠሩትን ሰልፍ በማስተባበር እና በመምራት ተካፍለው ለቀናት በእስር ቤት ቆይተው ወደ ስራቸው ሲመለሱ ከታች ያለውን የስራ ኮንትራታቸው መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ ደራሳቸው፡፡ EAL letter
መስዋዕትነት ማለት እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን አለ? መብትህን በመጠየቅህ አስረውህ እና ደብድበውህ ነጻ ነህ ብለው ይፈቱህ እና ይሄ አልበቃ ብሏቸው ከስራ ያባርሩሀል፡፡ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ የሽዋስ አሰፋም በሚሰሩበት ቴሌ ኮሚኒኬሽን መስራቤት ተመሳሳይ ሰለባ እንደነበሩ አይረሳም፡፡ .. source,-thioforum.org/amharic/አየር-መንገድ-በፖለቲካ-አመለካከት-ሰራተ/

No comments:

Post a Comment