Thursday, 4 December 2014
በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ ታወቀ
የፌደራል መንግስቱ የ2007 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው።
አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ ጽ/ቤትና ሌሎች ቁሳቁሶች ሰጥቷቸው ከመንግስት ጋር በመሆን ጸጥታን ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው በጉባኤው ላይ ተናግረዋል
ህገመንግስቱ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን ቢደነግግም፣ የመንግስት ባለስልጣናት በሚስጢር በሚያደርጉት ስብሰባ የሃይማኖት ተቋማት የመንግስትን የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከዚህ ቀደም ኢሳት በድምጽ አስድገፎ ማቅረቡ ይታወቃል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ የኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ በክልሉ የሚታየውን የዋቄ ፈታ እምነት ለማዳከም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ለተሰብሳቢው ሲናገሩ፣ ኦነግ በዋቄ ፈታዎች መጠቀም ይፈልጋል፤ የዋቄ ፈታ ድርጅት ተወካዮችን ስትራቴጂ ለመፈተሽ በስውርም በግልጽም ሰዎችን አሰማርተናል፤ እነሱ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ተነስተን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል። .
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment