Wednesday, 10 December 2014
‹‹መንግሥት ባለበት አገር በጠራራ ፀሐይ ቤቴን ተቀማሁ›› ወ/ሮ ዘውዴ ወልደማርያም፣ የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ
የዛሬ ‹‹ምን እየሠሩ ነው?›› ዐምዳችን እንግዳ ወ/ሮ ዘውዴ ወልደማርያም ይባላሉ፡፡ ዕድሜያቸው 70 መሆኑን ይናገራሉ፡፡
የሚኖሩት በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 11/12 ወይም በአሁኑ ወረዳ ሰባት ውስጥ ነበር፡፡ ወ/ሮ ዘውዴ በ2001 ዓ.ም. በ1,700,000 ብር የገዙትን ቤት ላለፉት ስድስት ዓመታት የኖሩበት ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉም ባይሆን የተወሰነ ግንባታ አካሂደውበታል፡፡ በቆርቆሮና እንጨት ታጥሮ የነበረን ግቢ፣ በግንብ ዙሪያውን ከሠሩና ሰርቪስ ቤቶችን ካደሱ በኋላ፣ ዋናውን ቤት ለመሥራትም ዲዛይንና የግንባታ ፈቃድ አግኝተው ነበር፡፡ ቤቱን ሲገዙ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሕጋዊ ሰነዶችን ከመንግሥት ተቋማት ያገኙ ቢሆንም፣ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ‹‹የገዙት ቤት ይዞታነቱ የሌላ ሰው ነው፡፡ ከእርስዎ ቀደም ብሎ በ1985 ዓ.ም. ለሌላ ሰው ተሸጧል፡፡ በመሆኑም አስረክበው እንዲወጡ›› የሚል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይደርሳቸዋል፡፡ በሁኔታው የተደናገጡት ወ/ሮ ዘውዴ፣ ወደ ፍርድ ቤት ሄደው ቢያመለክቱም እንዲወጡ ይነገራቸዋል፡፡
‹‹በሕጋዊ መንገድ የገዛሁትን ቤቴንማ ዝም ብዬ አላስረክብም›› ያሉት ወ/ሮ ዘውዴ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ብለው ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ፡፡ እዚያም ይወሰንባቸዋል፡፡ ተስፋ ባለመቁረጥ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎትም ሄደዋል፡፡ ውሳኔው ግን ሊቀለበስ አልቻለም፡፡ የመጨረሻ ጉዟቸውን ወደ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ቢያደርጉም፣ ‹‹የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው አይደለም›› በሚል የሦስት መስመር ምላሽ ተስፋቸው ተሟጦ አለቀ፡፡ መንግሥትንና የመንግሥትን ተቋማት በማመን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያፈሩት ገንዘባቸው አግባብ ባልሆነ መንገድ እንደተነጠቁ የሚናገሩት ወ/ሮ ዘውዴ፣ እግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ ይላሉ፡፡ ታምሩ ጽጌ አነጋግሯቸዋል፡፡ . source,-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36992
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment