Saturday, 20 December 2014
**የአንዱ ለቅሶ ለሌላው ደስታ እየሆነ ነው።**
ኢህአዴግ የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ ይበረግጋል። የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። ሲቃወሙት የበረሃ ወባው ይነሳበታል። ከድንጋጤው የተነሳ ይበረግጋል። ይደነብራል። ለምን? ቢባል በደም የተለወሰ ፓርቲ ስለሆነ ነው። ኢህአዴግ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ነፍስ ያላጠፋበት ስፍራ የለም። በመሀል አገር ክቡር የሰው ልጆችን ገሏል። የሚደመደም ነገር ባይኖርም በበላዮቹ ትዕዛዝ ኢህአዴግ ባፈሰሰው ደም መጠን ጠላት አፍርቷል። ወዳጁና አጋሩ ጠብመንጃና በደም የለወሳቸው አባላቱ ብቻ ናቸው። ሌላ ወዳጁ እንዳሻው የሚዘራው የአገሪቱ ሃብት ነው። የህዝብ ሃብት ህዝብን ለማፈን ማዋል!! ሌላው ስጋቱን ለመጥቀስ እንጂ ከዝርፊያ ጋር የተቆራኘውን ታሪኩን ለመዘርዘር አይደለም። ስለዚህ ህዝብ ሲቃወም ያጥወለውለዋል። ይጓጉጠዋል። አውሬ ይሆናል። ህግና ስርዓት አፍርሶ የጫካ ደንብ ይተገብራል። ባጭሩ ይገላል!!
ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ገዢ ነኝ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብን ያስቀየሙ፣ ያሳዘኑና፣ ያሳፈሩና ቂም ያስቋጠሩ ተግባራትን በግልጽና “በድብቅ ግን የሚታወቅ” አከናውኗል። በተለያዩ ጊዜያት በተግባሩ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን ሃይል ተጠቅሟል። አልሞ ተኳሾችን አሰማርቶ ዜጎችን ልባቸውና ግባራቸው አየተመታ እንዲገደሉ አድርጓል። የሚችለውን ያህል አስሯል። ገርፏል። ራሱ ክስ መስርቶ ራሱ እየፈረደ ወህኒ ወርውሯል። ነጻ ፕሬስን ሰቅሎታል። ሃሳብን በነጻ ማራመድን በህግና ህግ በማይጠቀስበት አግባብ አግቷል።
አሁን ጎንደር ላይ የተነሳውን የተቃውሞ አመጽ ተከትሎ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በጥበብ ከማስተናገድ ይልቅ ብረት አንስቶ መግደልን መርጧል። ኢህአዴግ በገደለ ቁጥር አገሪቱ ስጋቷ እየጨመረ፣ የህዝብ ስሜት እየተበላሸ ነው። ይህ እንደኢትዮጵያዊ ያስጨንቀናል። ኢህአዴግ የዘራው የቂም ዘር በየአቅጣጫው ፍሬው እየጎመራ መሄዱ ያሳዝነናል። ከሁሉም አቅጣጫ መፍትሔ የሚፈልግና ችግር የሚያረግብ አይታይም። አገሪቱ አስተዋይ በማጣቷ በስጋት ደመና እየነፈረች ነው። የአንዱ ለቅሶ ለሌላው ደስታ እየሆነ ነው። ከዚህ በላይ የሚያስጨንቅ ምን አለ? ኦሮሞው፣ አማራው፣ ደቡብ ክልል ያሉ ዜጎች፣ ኦጋዴን፣ ሶማሌ፣ ሁሉም ጋር ብሶት አለ። የኑሮ ችግር የጠበሳቸው የበይ ተመልካቾች መሯቸዋል። ያልመረራቸው ቢኖሩ ከቁጥር የማይገቡ ባለጊዜዎች ብቻ ናቸው። ይህም ታላቅ ስጋት ነው!!
ከሰብኣዊ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment